Hiber Radio: አሜሪካና ሸሪኮቿ ዜጎቹን የሚያሸብረውን የሕወሓት ኢህአዲግን ልዩ ሀይል እንዳይደጉሙ ጥሪ ቀረበ፣ሀብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ ከታከመ ይድናል የሚል ተስፋ መኖሩ ተገለጸ፣ ሐኪሞች በጫና ከዚህ ቀደም ከእስር ከወጣ በሁዋላ ታሞ ጤነኛ ነህ የሚል ሪፖርት ነግረውት ነበር፣ኢትዮጵያዊው የኡበር ታክሲ አሽከረካሪ በስርቆት እና በድብደባ ወንጀል ተጠርጥሮ ታሰረ

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 26  ቀን 2008 ፕሮግራም

<… የሀብታሙ አያሌው ጤና አልተሻሻለም ። ጤናው አሳሳቢ ነው። ዶክተሮቹ ሁለት ቀን አይተነው ሰኞ ውሳኔ እንሰጣለን ብለዋል።አሁን ከህመም ማስታገሻ በስተቀር የሚያገኘው ህክምና የለም ። ከአገር ወጥቶ እንዲታከም ከተፈቀደለት ይድናል የሚል ተስፋ አለኝ። ይፈቀድለት ሲሆን መንግስት ራሱ ነበር ማሳከም ያለበት ያንን ይቅር አናንሳው ቢያንስ በእስር ቤት ስቃይ ደርሶበት ታሞ በዚህ ስቃይ ውስጥ እያለ መፍቀድ ማንንም አይጎዳም። …ነገ ሺህ ሀብታሞዎች ይወጣሉ ፣ይነሳሉ ሕዝቡ አንድነቱ ተቆርቋሪነቱን ዛሬም …> አቶ ዳንኤል ሺበሺ የወቅቱን የሀብታሙ አያሌው የጤና ሁኔታን በተመከለተ ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን 33ተኛ ዓመት የመክፈቻ በዓልን በተመለከተ (ውይትት ከአክቲቪስትና የሕግ ባለሙያው ተክለሚካኤል አበበ (ልጅ ተክሌ) ጋር(ሙሉውን ያድምጡት)

<…በሀብታሙ ላይ በእስር ቤትም ሆነ ዛሬ ታሞ ከአገር በጊዜ ወጥቶ ተገቢውን ሕክምና እንዳያገኝ ማድረግ ይሄ ሰቆቃ መፈጸም ነው። ትላንትም ዛሬም በእስር ቤት ውስጥና ውጭ የሚፈጸምበት ሰቆቃ ነው…የዘንድሮ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወሳኝ ነው። በአገር ቤት ያለውን የሕወሓት አገዛዝ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠርም ፣በዚህ አገር ያለ ሕይወታችንንም የሚመለከት ወሳኝ ወቅት ነው ።…> ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ያድምጡት)

በኢትዮጵያ የተከሰተው እና ከ10.2 ሚሊዮን በላይ ህዝብን ተረጂ ያድረገው ረሃብ ኣና ድርቅ ዛሬም “የወገን ያለህ” ጥሪን ጋብዟል ።የድርቁ ተጎጂዎች ኣለታዊ ኑሯቸው በከፊል ምን ይመሰላል?(ልዩ ጥንቅር)

<…የአዲስ አበባ የጽዳት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ።አደገኛም ነው። ዛሬ ኮሌራ ትላለህ ነገ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞቱ፣ከነገ ወዲያ ኦሮሚያ ውስጥ ንጹሃን ተገደሉ ደግሞ …መሰረታዊ ለውጥ ካልመጣ መፍትሄ የለም በእኔ እምነት የዛሬይቷን ኢትዮጵያ ኢህአዴግ መምራት አልቻለም ለውጥ ያስፈልጋል ኢትዮጵያ ከዚህ አገዛዝ የተሻለ ይገባታል…>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

አሜሪካና ሸሪኮቿ ዜጎቹን የሚያሸብረውን የሕወሓት ኢህአዲግን ልዩ ሀይል እንዳይደጉሙ ጥሪ ቀረበ

ሀብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ ከታከመ ይድናል የሚል ተስፋ መኖሩ ተገለጸ

ሐኪሞች በጫና ከዚህ ቀደም ከእስር ከወጣ በሁዋላ ታሞ ጤነኛ ነህ የሚል ሪፖርት ነግረውት ነበር

ሰሞኑን በኢትዮ-ሶማሊያ  ድንበር ላይ የተካደውን የዜጎች ጨፈጨፋን የዘገበ ሶማሊያዊ ጋዜጠኛ በኢሕአዲግ ታጣቂዎች ታፍኖ የገባበት መጥፋቱ ስጋት ፈጠረ

ኢትዮጵያዊው የኡበር ታክሲ አሽከረካሪ ከደንበኛው ጋር በተፈጠረ አምባጓሮ በስርቆት እና በድብደባ  ወንጀል ተጠርጥሮ ታሰረ

አ/አበባ ውስጥ አንድ የጥበቃ ሰራተኛ በወረወረው የእጅ ቦንብ  አንዲት ጨቅላ ሕጻንን ገደለ ሁለት ጉደኞቿን አቆሰለ

ኤርትራ ምእራባዊያን ኢንቨስትሮችን ለማማለል አዲስ  የዲፕሎማሲ ዘመቻ  ጀመረች

በእስራኤል ወስጥ የሚደረገው ዘርኝነትን  የተቃወሙ ቤተ እስራኤላዊያኖች  ከፖሊስ ጋር ተጋጩ፣በርካታዎችም ለእስራት ተዳረጉ

ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር የጠራውን ስብሰባ በጫና መሰረዙን አስታወቀ

በአወዳይ የተደረገውን ግድያ ሕዝብ በተቃውሞ ሰልፍ አወገዘ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤታቸው ፈርሶ ሚዳ ላይ የተጣሉ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው

ተጨማሪ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ይቀጥላል ተብሏል

 እና  ሌሎችም  ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-070316

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *