Hiber Radio: ሀብታሙ አያሌው ከሆስፒታል እንዲወጣ ተገደደ፣ ዶክተሮች ከአገር ወጥቶ እንዲታከም የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ሰጡ

Habtamu-ayalew-denaied-01

(ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ ) በጠና ሕመም ላይ የሚገኘውን ሀብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ እንዳይታከም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተጣለበት እገዳ እንዲነሳ በአሁኑ ወቅት ተኝቶ የሚገኝበት የካዲስኮ ሆስፒታል ሶስት አባላት አሉት የሐኪሞች ቦርድ አስቀድሞ በዶክተር አብርሃም የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ባለሙያ የተሰጠውን ማረጋጋጫ ሙሉ ለሙሉ ደግፈው ለተቅላይ ፍርድ ቤት የተላከውን የሕክምና ማስረጃ ማስደቃቸውን አቶ ዳንኤል ሺበሺ የቀድሞው አንድነት ም/የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ገለጹ።

የካዲስኮ ሆስፒታል በሕመም ማስታገሻ የቆውን ሀብታሙ አያሌውን ዶክተሮች “ከበሽታዉ መወሳሰብ አንፃር ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት በሀገር ዉስጥ ወደ እማይገኘዉ ኮሎ ሬክታል ሴንተር በመሄድ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና እንዲደረግለት ወስነን ሳለ ህመምተኛዉን በሆስፒታላችን ማቆየት አንችልም” በማለት ከሆስፒታሉ እንዲወጣ ትላንት ትዕዛዝ ሰጥተው የነበረ መሆኑን የገለጸው አቶ ዳንኤል ባለበት በዚያ ሁኔታ ሀብታሙን ወደ ቤቱ መውሰድ የ4 ኣመት ልጁን ማሳቀቅ መሆኑን በመግለጽ ፣ ታሞም ስለነበርና የግድ የሕክምና ድጋፍ ስለሚያስፈልገው ሌላ ሆስፒታል ለማስገባት ተጨማሪ አንድ ቀን ቢያሳድሩትም ሌሎችም ቦርድ ከአገር ወጥቶ ይታከም ያለውን በሽተኛ አንቀበልም በማለታቸው ዛሬ ከሆስፒታሉ እንድንወጣ ተገደናል ሲል በጽሑፍ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ሀብታሙ ሆስፒታል ሆኖ በሕመም ማስታገሻ ለመቆትም ባለመቻሉ በግለሰብ ቤት ተከራይተው ፈቃደኛ በሆኑ የግል ሐኪሞች አማካይነት የሕመም ማስታገሻ እንዲሰጠው እያደረግን ነው ብሏል። ዳንኤል በመጨረሻ<<ያ ሀገር የማይበቃዉ የህዝብ ልጅ እንዲህ ሆኖ ማየት በጅጉ ያማል፡፡ ቀጣዩን ተከታትዬ አሳውቃለሁ…>>  ሲል ሐዘኑን ጽፏል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ከማንኛውም ሐኪም ማስረጃ ከመጣልኝ ፈቃድ እሰጣለሁ ካለ በሁዋላ በቀጠሮው በፍርድ ቤቱ ግቢ የነበረውን ዳኛ ዳኜ መላኩ <<ዳኛ የለም>> በሚል ውሳኔውን አዘግይቶ በመጨረሳ የሆስፒታሉ ሜዲካል ቦርድ ይጻፍልኝ ማለቱ አይዘነጋም።

አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ የቦርድ ውሳኔ የሚጠየቀው ለህክምና የውጭ ምንዛሪ ለሚፈልጉ ወይ በመንግስት ወጪ ለሚታከሙ መሆኑን በማስታወስ ሀብታሙ ሁለቱንም አለመጠየቁን አስታውሶ ጤናው እንዲመለስ ነገሩን ላለማጓተት ሲባል የጠጠየቀውን ሁሉ ለማማዐላት የሆስፒታሉ ቦርድ እንዲጽፍ ጠይቀው አስቀድሞ ሁለቱ ሐኪሞች ጽፈው አንደናው መንገድ ሔዷል ተብሎ እየተጠበቀ ቆይቶ አሁን ጽፈዋል።

የሀብታሙ አያሌው የጤንነት ሁኔታ እአሽቆለቆለ የሄደ ሲሆን ተገቢውን ሕክምና ውች ሔዶ እንዳያገኝ የሚአደርገው መንግስት ለሚደርሰው ጭግር ተጠያቂ መሆኑን አስቀድሞ መገለጹ ይታወሳል።

ሀብታሙ አያሌው በእስር ቤት የደረሰበት ስቃይ ለዛሬው የከፋ የጤና ችግር እንዳጋለጠው ለህብር ሬዲዮ አስቀድሞ ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል። የሀብታሙን ቃለ መጠይቅ አያይዘነዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *