Hiber Radio: ሰራዊቱ ጠመንጃውን በዘረኛ አዛዦቹ ላይ እንዲያዞር ሕዝብን መግደሉን እንዲያቆም ብ/ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋና ኮ/ል ደረሰ ተክሌ በጋራ ጥሪ አስተላለፉ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የጀመረው አጥፍቶ መጥፋት እንደማያዋጣው ገለጹ፣ ፣የአጋዚ የቀድሞ ኮማንደር አዛዥ ኮ/ል አለበል አማረ ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ ተኩስ ባሉት ላይ ጠመንጃውን እንዲያዞር ጠይቀዋል፣በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሁለት ቀናት ብቻ ከ140 በላይ ንጹሃን በአገዛዙ ታጣቂዎች ተገደሉ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 1 ቀን 2008 ፕሮግራም

< …ይሄ የኢትዮጵያ ሰራዊት አይደለም ወያኔ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ያደራጀው ሰራዊት ነው።በአንዳንድ ቦታዎች የሰራዊቱ አባላት ከወገናቸው ጎን መሰለፋቸውን እያየን ነው ይሄ መበረታታት አለበት ።በህግ የማይተዳደር የወያኔ አስተዳደር አዞኝ ነው አያዋጣም። በሕዝቡ ላይ ተኩስ የሚሉት የወያኔ የጦር አበጋዞች እነሱ የዘረፉት ሀብት የሚቀርባቸው ስለሚመስላቸው ነው ሰራዊቱ በነሱ ላይ ጠመንጃውን ማዞር አለበት ከእኛ ትምህርት መውሰድ አለበት…> ብርጋዴር ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ(መጀመሪያ ክፍል)

<…የአጋዚ ክፍለ ጦር ብቻ ሳይሆን በሰራዊቱ ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች እስካሉት በአስር አለቃ ጭምር የሚመራ ቡድንም የትግራይ ተወላጆች ናቸው የሚያዙት ዛሬም በሕዝብ ላይ የሚያስተኩሱት እነሱ ናቸው። ሰራዊቱ ከሕዝብ ጎን መቆምና ጠመንጃውን ወደነሱ ማዞር አለበት ወገኑን ገሎ የነሱን ስልጣን ማስቀጠል የለበትም…>

/ ደረሰ ተክሌ በጋራ ከብ//ሀይሉ  ጎንፋ ጋር ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለሰራዊቱ ካስተላለፉት መልዕክት የተቀነጨበ(ክፍል አንድያዳምጡት)

<…ኢህአዴግ የጀመረው አጥፍቶ መጥፋት ለሱና ለመሪዎቹ የሚአዋጣ አይደለም ለቀደሙትም ገዢዎችና ልጆቻቸው አልጠቀመምየኢትዮጵያ ሁኔታ እንደ ሩዋንዳና ሱማሌ እንዳይሆን ብቸኛው አማራጭ ተባብሮ መታገል በጋራ መቆም ነው ይህ ካልሆነ ግን የእኛ ሁኔታ ከሶማሊያም እንዳይከፋበውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ምግብ ሲበላ ቲፕ ይሰጣል ለሚፈልገው ለውጥ ለሚያምነውና ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ለሚለው ስራ ለሚሰራ ለእውነተኛ ተቃዋሚ መርዳት አለበት ለትግሉ በቀን አንድ ዶላር ቢረዳ በአገር ቤት ይህን ሕዝብ ላይ የሚተኩስ ስርዓት ለማንበርከክ አስገድዶ ወደ ድርድር ጠረ{ ለማምጣት እና…> / መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር የኢትኦጵያ የጋራ ትግል ሸንጎ ዛሬ በዋሽንግተን ባካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ላይ ከተናገሩት(ቀሪውን አዳምጡ)

<…የህዝቡ ጥያቄ ወልቃይት የአማራ ማንነት ደግሞ ማረጋገጥ  ብቻ አይደለም፣የማስተር ፕላኑን መቃወም ጥያቄ ብቻ አይደለም የሙስሊሙን ሰላማዊ ጥያቄ መደገፍ ብቻ አይደለም ጥያቄው ኢህአዴግ በቃህ!  በቃኝ ነው።በባህር ዳርም የተደረገው ሰልፍ ላይ በኦሮሚአም ያየነው ሕዝቡ ኢህአዴግን በቃኝ ነው …> / ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሸንጎ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ከተናገሩት

<…የትግራይ ልሂቃን ንጹሃን እየተገደሉ ዝምታችሁ ይብቃ ከሕዝ ጎን መቆም እና ሕወሓትን ማውገዝ አለባችሁ…> አቶ ኦባንግ ሜቶ በሸንጎ ጉባዔ ካስተላለፉት ጥሪ

ለአንድ ሳምንት በሚኒሶታ የተካሄደው የኦሮሞ ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ የስፖርት  ውድድር መዝጊያ እና በዝግጅቱ ላይ የሁሉም ወገኖች መሳተፍ ተስተውሏል (ቆይታ ከዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ ጋር ስለ ዝግጅቱ ቆይታ አድርገናል ያድምጡት)

 

በአገር ቤት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተካሄደውን ሰላማዊ ተቃውሞና የአገዛዙን የጥይት ምላሽ አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)

ዜናዎቻችን

/ጄኔራል ሀይሉ ጎንፋና / ደረሰ ተክሌ ሰራዊቱ ጠመንጃውን በዘረኛ አዛዦቹ ላይ እንዲያዞር ሕዝብን መግደሉን እንዲያቆም ጠየቁ

የአጋዚ የቀድሞ አዛዥ / አለበል አማረም ሰራዊቱ ሕዝብ ግደል ባሉት መሪዎቹ ላይ ጠመንጃውን እንዲያዞር ጥሪ አቀረቡ

/ መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የጀመረው አጥፍቶ መጥፋት እንደማያዋጣው ገለጹ

በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሁለት ቀናት ብቻ 140 በላይ ንጹሃን በአገዛዙ ታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ በተካሄደው ተቃውሞ በርካታዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች ተገደሉ

አያሌዎች ታስረዋል፣አገዛዙ ጣቱን በተቃዎሚዎች ላይ ቀስሯል

የተቃዋሚዎች የተባበረ ትግልና አመራር ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ያስቀራል አሉ

/ ይልቃል የሕዝቡ ጥያቄ ኢህአዴግ በቃኝ ነው ሲሉ ገለጹ

በኢትዬኬኔያ ድንበር ላይ ሰሞኑን ውጥረት አይሎ የአዲስ አበባ ገዢዎች ለናይሮቢ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

እስራኤል በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጌቾ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቁያ አወጣች

በአራቱም አቅጣጫ ስትዘዋወሩ ተጠንቀቁየእስራኤል ውጭ //

የአሜሪካው ፕሬዜደንታዊ ተፎካካሪ ትራምፕ አገራቸው ጥገኝነት በሰጠቻቸው ዜግች ላይ ጥርጣሬ እንድታደርግ መከሩ

ሙስሊም የሚለውን ቃል ከዚህ በሁዋላ አልጠቀምምበማለት ቃል ገቡ

በቬጋስ ኢትዮጵአዊው ሆን ብሎ አስነስቶታል በተባለው እሳት ሳቢያ ሕይወት ጠፋ ለእስር ተዳረገ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-080716

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *