Hiber Radio: የቅሊንጦ እስር ቤት እሳት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሁኔታ በአገዛዙ እንዲነሳ መደረጉን አንድ የእስር ቤቱ ጠባቂ አጋለጠ፣የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባ በላይ ደርሷል፣የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባ በላይ ደርሷል፣የካናዳ መንግስት እና ሽሪኮቹ በኢትዮጵያ እየደረስ ያለው የስብዓዊ መብት ረገጣን ችላ ማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 29 ቀን 2008 ፕሮግራም

 <…በሕዝቡ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ተቃውሞ በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶየሕዝቡን ትግል የተቀላቀለውን ከሁለት ሻምበል በላይ ጦር ሰራዊት የዕምቢታ ጦርየሕዝቡ አጋር ነው ይሄ እርምጃ ማደግ አለበት ነገ ከነገ ወዲያ በክፍለ ጦር ደረጃተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ  ከሕዝቡ ጎን መቆሙን እንዲቀጥል ሕዝቡ ተገቢውን መረጃመስጠት አለበትሰራዊቱ ራሱ በሕወሓት ዘረኛ የጦር አዛዦች የተንገፈገፈ ነው።አሁንም ለመላው የሰራዊት አባላት ጥሪ አለኝ…> / ደረሰ ተክሌ የቀድሞ የሰራዊቱየጥናትና ምርምር ሀላፊ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶየሕዝቡት ትግል ስለተቀላቀለው ሁለት ሻምበል ጦር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡትማብራሪያ(ያድምጡት)

< …  አሁን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግድያና አፈና ሌላው ቀርቶ እስረኞችበታሰሩበት እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ይሄን ሕገ ወጥ ድርጊት ነው ተብሎ የሚታለፍአይደለም።ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገሮች አደገኛ አለመረጋጋት የሚያመጣእርምጃ ስለሆነ ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት የሳዳም መንግስት ኩርዶችንሲጨፈጭፍ የወሰደውን አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላልየኦሮሞም ሆነ የአማራሕዝብ ሌላውም ኢትዮጵያዊ ጭምር በጋራ በትግሉ ወቅት ያነሳቸውን አብይ ጉዳዮችያካተተ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት ለውጡን በጋራ ማፋጠን በጋራ ጠላት ላይ ማተኮርያስፈልጋል ከዚህ በሁዋላ… >    ሔኖክ ጋቢሳ የህግ ባለሙያና መምህር ስለወቅታዊው ሁኔታ ለህብር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡ)

የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ሁኔታ በተመለከተ የስጡትአስተያየት አዲሱ የእንግሊዝ መንግስት በአቶ  አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስራት መለቀቅሙከራ  ዙሪያ የሰጠው ምላሽ እና የመብት ተሞጋቾች እና የአቶ እንዳርጋቸው ባለቤትምላሽ(ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ በመጪው ረቡዕ 10 ጊዜ የኢትዮጵያውያን ቀን ይከበራል በአገር ቤት ባለውወቅታዊ ሁኔታ ሳቢያ በዕለቱ የሙዚቃ ዝግጅት አይቀርብም (የኮሚኒቲው /ሊቀመንበር የሰጡትን ማብራሪያ ይዘናል)

ወታደሩ ወገኔ ሕዝብ ላይ አተኩስ(ግጥም)

ዜናዎቻችን

የቅሊንጦ እስር ቤት እሳት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሁኔታ በአገዛዙ እንዲነሳ መደረጉንአንድ የእስር ቤቱ ጠባቂ አጋለጠ

 እሳቱን ጭምር ለማጥፋት በሚሞክሩ እስረኞች ላይ በቀጥታ ሲተኮስ ነበር

የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባበላይ ደርሷል

በወሎ ከሁለት መቶ በላይ የመንግስት ሰራተኞች አገዛዙ በአማራ ላይ ለከፈተው ጦርነት ማብራሪያ የጠራውን ስብሰባ ተቃውመው ረግጠ ወጡ

ደሴ የቤት ውስጥ አድማ ቀጠለ

የቅሊንጦ የማጎሪያ ቤቱ ጠባቂዎች በልዪ የፖሊስ ሃይላት ተተኩ

የአትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ዘመድ በአገዛዙ ታጣቂዎች ጥርሱእንደረገፈ፣እግሩ በጥይት እንደ ተመታ ተናገረ

አትሌት ፈይሳ ወደ አገሩ ከተመለሰ ሞት ይጠብቀዋልየፈይሳ ዘመድ እማኝንነት

የካናዳ መንግስት እና ሽሪኮቹ በኢትዮጵያ እየደረስ ያለው የስብዓዊ መብት ረገጣን ችላማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይን በቅርበት እየተከታተልነው ነውካናዳ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችበአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ ቀረበ

*አገዛዙ ግን ዛሬም በሩን ለውጭ ታዛቢዎች አልከፍትም እንዳለ ይገኛል

/ መረራ ጉዲና ተቃዋሚዎች በመንግስት ለውጥ ላይ ብቻ ሳይሆን  ከለውጡበሁዋላ ባለ ሁኔታ በፍጥነት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብርሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድበአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነውበእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻእንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *