ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው
የዐማራው ተጋድሎ ከተቀጣጠለ ወዲህ የአገሪቱ ፖለቲካ ተመሰቃቅሏል፤ አሁን የምናየው የዐማራውን ተጋድሎ ጅማሬ ነው፡፡ ጅምር መሆኑን ወያኔም የዐማራ ሕዝብ ወዳጆችም ሊያውቁት ይገባል፡፡ መሬት አንቀጥቅጥ የዐማራ ተጋድሎዎችን ወደፊት የታሪክ ገጻችን ገና ይመዘግባል፡፡
ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ የማንነት ጥያቄ በድምጸ ውሳኔ እፈታለሁ እያለ ነው አሉ፤ በአንድ በኩል ደግሞ በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ወደ ብር ሸለቆ ካምፕ ወስዶ እያሰቃያቸው ነው፡፡ አሁንም በሌላ በኩል ደግሞ ከኦሮሞ ወንድሞቻችን ጋር ለማጣላት እየጣረ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ከንቱ ድካም ነው፡፡ የዐማራ ሕዝብ ትግል የትኛውንም ሕዝብ በጠላትነት አያይም፡፡ ቀንደኛ ጠላቱ ወያኔ የተባለው ከትግራይ የበቀለ ጥቁር ፋሽስት ብቻ ነው፡፡
ሕወሓት እንደፈለገ የሚጋልበውን ብአዴንን የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ በሕዝበ ውሳኔ እንፈተዋለን በሚል ባለ17 አንቀጽ ስምምነት እንደተፈራረሙ አውቀናል፡፡ የትኛው ሕዝብ ነው የሪፈረንደም ውሳኔ የሚሰጠው? ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ትግሬዎችን አስፍሮ ሕዝበ ውሳኔ ማድረግ እንደምን ያለ አሰራር ነው? የወልቃይት ጠገዴን ዐማሮች ብዙዎችን ገድሎ፤ ብዙዎችን አስሮ፣ ብዙዎችን ደግሞ እንዲሰደዱ አድርጎ በሰፋሪዎች ብቻ ድምጸ ውሳኔ ማድረግ አሁንም ሌላ ሞት መደገስ ነው፡፡ ሰፋሪዎችን ሳይጨምር ከሆነ ደግሞ ከዐማራ ውጭ ትግሬ በአካባቢው እንደሌለ ስለሚታወቅ የዐማራ አገር መሆኑ ሀቅ ነው፡፡
ያም ሆነ ይህ ወያኔ ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ አለ፤ ሲጀመር ጥያቄውን ያነሳው ብአዴን አይደለም፡፡ ጥያቄው የ40 ሚሊዮን የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ብቻስ ማን አደረገው? የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ በወልቃይት ጠገዴ መልስ ብቻ የሚቆም የሚመስላቸው ወያኔዎች አሁንም ለበለጠ ፍልሚያ ይዘጋጁ፤ በፍጹም አይደለም፡፡
የዐማራ እናቶች የማያሳድጉትን ልጅ ከዚህ በኋላ አይወልዱም፤ የዐማራ ተጋድሎ የትግሬን ጥቁር ፋሽስት ተከዜን በማሻገር ብቻ አይገደብም፡፡ ትግላችን እስከ ነጻነት ይቀጥላል፡፡ የዐማራ ሕዝብ የሚገባውን ክብር እስከሚያገኝ በአባቶቹ አገር ተከብሮ በእኩልነት እስከሚኖር ድረስ፣ የማይቀለብስ ነጻነትን እስኪጎናጸፍ ድረስ እንታገላለን፤ እንፋለማለን፤ አራት ነጥብ፡፡
የዐማራ ወጣቶች ሆይ፤ ቀጣይ ጊዜያት የከፉ እንደሆኑ እናውቃለን፤ ከድቅድቅ ጨለማ በፊት ብርሃን መጥቶ አያውቅም፤ ከክረምት በፊትም የጸዳይ ውበት ታይቶ አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የፍስሃውን ዘመን ከአድማስ ማዶ በተስፋ እያየን ተስፋውንም ለመጨበጥ በምንችለው ሁሉ ትግላችን አበርትተን እንቀጥል፡፡ ክንዶቻችን አይዛሉ፤ እንቅልፍም ዓይናችን አይጎብኘው፤ አእምሯችን ከነጻነት ውጭ አይስብ፡፡ ፍጥነታችን የሚፈጅብን ጊዜ ይወስናል፡፡
ወያኔ ጅብ ነው፤ ቂም አይረሳም፡፡ ወያኔ ጥቁር ፋሽስት ነው፤ የዐማራ ስቃይ ያስደስተዋል፡፡ እኛ ግን ለቂመኛ ጅብም ለፋሽስትም የማንበገር የአባቶቻችን ልጆች ነን!! የዐማራ አባቶች ምን አደረጉ? እያንዳንዱ ዐማራ ማታ ሲተኛ፣ ጠዋት ሲነሳ ስለ አርበኛ አባቶቻችን ገድል መጠየቅና ማንበብ አለበት፡፡ በላይ ዘለቀ ስለምንድን ነው አምስት ዓመት ሙሉ ድንጋይ ተንተርሶ ጤዛ ልሶ የታገለው? እነ ሽፈራው የማን እዳ ኖሮባቸው ነው? አበበ አረጋይ ከባንዳ አባቱ ጋር ስለምን ተፋለመ? የነ ኃይለ ማርያም ማሞን፣ የነ ራስ አሞራው ውብነህን፣ የጄኔራል ተፈራ ማሞን፣ የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ገድል ተላበስ፡፡ ያኔ አሻግረን የምንመለከተው ነጻነት በእጃችን እናስገበዋልን፡፡