Hiber Radio: በመተማ ሰፍረው የነበሩ 35 ወታደሮች የሕዝቡን ትግል ተቀላቀሉ፣ አርብ በተደረገ ውጊያ በወገራና በመተማ ዮሐንስ 11 የሕወሓት ወታደሮች ተገደሉ፣የተማረኩ ትግሉን ተቀላቅለዋል ፣ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአገሪቱ ውስጥ ፍትህ ካልስፈነ አገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እንደምትሄድ አስጠነቀቀ

habtamu-assefa-hiber

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 8 ቀን 2009 ፕሮግራም

< … መምህሩ ለመንግስት ደጋግሞ ተናግሯል።የሚሰማ የለም ።ለማይሰማኝ አካል እንዴት ደግሜ እናገራለሁ ብሎ በዝምታ ተቃውሞውን ገልጿል። ዝምታው ውጤት ያመጣል ወይ…ሁኔታዎች ወደ ተረጋጉ የሕዝቡ ጥያቄ ተገቢ መልስ የሚያገኝበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ።ለውጥ መደረግ አለበት ይህ ካልሆነ ግን…> የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመ ከህብር ሬዲዮ በወቅታዊው የመምህራን ውይይት እና የዝምታ ተቃውሞ ላይ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…በሚኒሶታ በኮንቬንሽን ሴንተር ለጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ኢትዮጵያውአን ታላቅ አቀባበል አድርገውለታል። የኦሮሞ ኮሚኒቲ ስብሰባውን በዋናነት ይጥራ እንጂ ሁሉም እንዲገኙ አድርጎ ሁሉም ኢትዮጵያውአን በጋራ ተገኝተው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካይ፣የኦጋዴን ተወካይ እና ሌሎችም ተናጋሪ ነበሩ አትሌቱም ለሕዝቡ ምስጋናውን አቅርቧል…> የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ በሚኒሶታ ለጀግናው አትሌት ፈይሳ የተደረገውን ታላቅ አቀባበል በተመለከተ ከሰጠን ማብራሪያ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ስርዓቱን ለመጣል ብቻ ሳይሆን ከወደቀ በሁዋላ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ይሄው እየተነጋገርን ነው። ብዙዎቹ የነጻነት ታጋዮች ለውጡ ላይ እንጂ ከለውጡ በሁዋላ ያለው ሁኔታ ቀድሞ አያሳስባቸውም ነበር።አሁን እና እያደረግን ያለውን ውይይት ጨምሮ ምሁራን ከስርዓቱ ለውጥ በሁዋላ ስላለው ሁኔታ ስራ መስራት አለባቸው…> አክቲቪስት እና የኦሚኔ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ ኢትዮ ቲዩብ የማህበራዊ ሚዲያው አክቲቪዝም በኢትዮጵያ በሚለው ውይይት ላይ ተገኝቶ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

አቶ ጁነዲን ሳዶ የሕወሃት ቡድን በአማራና በኦሮሞ ባለስልጣናት ላይ ያደርገውን ተጽዕኖ፣ከምርቻ 97 በሁዋላ የተከተለውን ዘረና እርምጃና የሌላውን ብሔር ነጋዴ ከገበያ ያወጣበትንና በስርዓቱ ደጋፊ የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች የተካበትን ሂደትና ለምን ሐይለማሪያምን እንደሾሙና ሌላውንም ያብራሩበትን ጽሑፍ ዳሰነዋል (ልዩ ጥንቅር)

አንጋፋው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ ሲታወስ (ቃለ መጠይቅ)

ለአትሌት ፈይሳ ለሊሳ አቀባበል በተደረገው ዝግጅት ላይ አቶ መላኩ በቀለ የሚኒሶታ የኢትዮጵአ ኮሚቲ ተወካይ አኢና አቶ መሐመድ አባስ የኦጋዴን ኮሚኒቲ ተወካይ ያደረጉትን ንግግር (አዳምጡት)

የመብት ተሞጋቹ ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት በኢትዩጵያ ውስጥ ለውጥ ካስፈለገ ብቸኛው ወቅት አሁን ብቻ ነው ሲል ጥሪ አቀረበ

ዜናዎቻችን

በመተማ ሰፍረው የነበሩ 35 ወታደሮች የሕዝቡን ትግል ተቀላቀሉ፣ አርብ በተደረገ ውጊያ በወገራና በመተማ ዮሐንስ 11 የሕወሓት ወታደሮች ተገደሉ፣የተማረኩ ትግሉን ተቀላቅለዋል ፣ ጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በአገሪቱ ውስጥ ፍትህ ካልስፈነ አገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እንደምትሄድ አስጠነቀቀ

ሕወሓት ዩኒቨርስቲዎች ሲከፈቱ በአማራና በኦሮሞ ተማሪዎች መካከል የጎሳ ግጭት እንዲቀሰቅሱ ላዘጋጃቸው ሽሬ ላይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ

የአሜሪካው ፕ/ታዊ እጩ ትራምፕ የተፎካ ካሪያቸው ሔለሪ ጠባቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱሀሳብ ማቅረባቸው ተቃውሞ አስነሳ

“አንድ የአሜሪካ መከላከያ ሀይል የበላይ ጠባቂ ለመሆን የሚጥር ስው እንዲህ ማለቱ ያሳፍራል”ተቀናቃኞቻቸው

እስራኤል በቤተእስራኤሎች ላይ የሚደርስው ዘርኝንትን አስቆማለሁ አለች፣ለዘመቻውም ከፍተኛ። ገንዘብ መድባለች

ትውልደ ኢትዩጵያኖች አሜሪካ በበሕወሓት/ኢህ አዲግ አገዛዝ ላይ ጫና እንድታርግ በፊርማ ማስባስብ ዘመቻ እንዲግፉ ተጠየቀ

አንጋፋው ጋዜጠኛ አበራ ወጊ በሳንዲያጎ በድገተና የመኪና አደጋ ሕይወቱ አለፈ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *