Hiber Radio: አስደናቂው የዋሽንግቶን ዲ.ሲ. ሰላማዊ ሰልፍ ምን ያመለክታል? አክሎግ ቢራራ (ዶር)

great-protest-001-dc-hiber

በትላንቱ (September 19, 2016) ቀን በዋሺንግተን ከተማ የተካሄደው ሕዝባዊ ትእይንት (ሰላማዊ ሰልፍ) ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ፤ የኢትዮጵያን የሕዝብ፤ የኃይማኖት፤ የጾታ፤ የእድሜ እና ሌሎች ስርጭቶች የሚያንጸባርቅ ነበር። ከቴክሳስ፤ ከጅወርጅያ፤ ከኦሃዮ፤ ከንውዮርክ፤ ከማሳቹሴትስ፤ ከፔንሰልባንያና ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች በአውቶቡስና ሌሎች መጓጓዣዎች የመጡት ወገኖቻችን ድምጽን ለማሰማት ለተደረገው አስደናቂ ሰል ድምቀትና ውበት ሰጥተውታል።

ይህን ሰላማዊ ሰልፍ የተለየ የሚያደጋቸው መስፈርቶች ብዙ ናቸው። እኔ ትኩረት የምሰጠው ለሚከተሉት ነው፤

  1. ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መለያው ማድረጉ፤
  2. ሰልፉን ለማቀናበር ያስቻለው ቡድን ስፋትና ጥራት ያለው መሆኑ፤ ከቡድን ባሻገር ለአገርና ለወገን ተባብሮና ተናቦ ለመስራት መቻሉ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የሚለውን ብሂል በተግባር ማሳየቱ፤ የዚህ አይነት የመተባበር መንፈስና ተግባር ልምድ እንዲሆን ከሕዝብ ድምጽ መሰማቱ፤
  3. ኦሮሞው፤ አማራው፤ ጉራጌው፤ አኟኩ፤ ሶማሌው፤ ወላይታው፤ ትግራዩ እና ሌላው ከብሄር፤ ከኃይማኖት፤ ከጾታ፤ ከእድሜና ሌላ መለያ ባሻገር ለአገርና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት፤ እኩልነት፤ ፍትህ እና ተቆርቋሪነት ማሳየቱ፤ የደመቀ ድምጽ ማሰማቱ፤
  4. የሴቶች፤ የወጣቶች፤ የባላሞያዎች እና ሌሎች ተሳትፎ ከመቸውም የላቀ መሆኑ፤
  5. የሕዝቡ ብዛትና የመፈክሮቹ አግባብነት ለአሜሪካ መዲና የተለየ ድምቀት መስጠቱ፤ መንገዶች ሁሉ ስለተዘጉ ተመልካቹ ሕዝብ ትእይንቱ ለምን እንደሆነ መጠየቁ፤ ትምህርትና ግንዛቤ ማግኘቱ፤ በቤቱ የሚነጋገርበት መሆኑ፤
  6. አዘጋጆቹ ባወጡት እቅድ መሰረት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ ለሆኑት ለሴክረተሪ ጆን ኬሪ ጸሃፊ የተዘጋጀው ደብዳቤ በእጅ መሰጠቱ እና መመዝገቡ፤
  7. የአሜርካ ምክር ቤት (ኮንግሬስ) በውሳኔ ላይ ከፍተኛ ሚና ስላለው H.R. 861 ሕጋዊ የሚሆንበትን ለማጠናከር በምክር ቤቱ ፊት ለፊት የደመቀ ንግግር እና መፈክር መሰማቱ፤ ለኢትዮጵና ለሕዝቧ ትኩረት ለሰጡት ለሴናተር ኮርከር፤ ሴናተር ካርደን፤ ለምክር ቤት አባላት ሮይስ፤ ኤንግል፤ ስሚዝ፤ ኮፍማንና ኤሊሰን የተጻፉት ደብዳቢዎች እንዲደርሷቸው መደረጉ፤
  8. የተሳታፊዎች ድምጽና ለወገን ተቆርቋሪነት ስር እንደሰደደ፤ እና
  9. ሰልፈኛው ከአሁን በኋላ በያለበት ተከታታይ ስራዎችን ተባብሮ ለመስራት ቃል ኪዳን መግባቱ ሕዝባዊ ትእይንቱን የተለየ ያደርገዋል።

በዚህ አጋጣሚ ይህን አስደናቂ ሕዝባዊ ትእይንት ስኬታማ ያደረጉትን የአስተባባሪ ቡድን አባልትና ድጋፍ የሰጡትን ሃያ አራት ድርጅቶች እንድታመሰግኗቸው ስማቸውን ከዚህ አጭር ዘገባ ጋር አያይዣለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት በእኩልነት!

List of Protest Organizers and Signatories

DC Area Ethiopian Community Joint Task Force

Ethiopian Dialogue Forum (EDF)

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Leaders

Ethiopian Muslim Religious Leaders (First Hijrah)

Ethiopian Protestant Religious Leaders

United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group

United Oromo Liberation Front

All Amhara People’s Organization

Moresh Wegene Amhara Organization

Patriotic Ginbot 7

Ethiopian People’s Revolutionary Party

Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo)

Gonder Hibret

Oromo Democratic Front

Bete Amhara

Ethiopian National Transitional Council

Solidarity Movement for a New Ethiopia

All Ethiopia Unity Party Support Group

Mahbere Ethiopia

Addis Dimits Radio

Netsanet Radio

Solidarity Committee for Ethiopian Political Prisoners

International Ethiopian Women Organization

Former Ethiopian Defense and Police Force Veterans Association

Ethiopian Constitutional Monarchy

Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights

Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *