በአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነውና በማህበራዊ ሚዲያው በሚያወጣቸው ጽሁፎቹ የሚታወቀው ስዩም ተሾመ በሕወሓት አገዛዝ ደህነቶች ዛሬ ታፍኖ መወሰዱን ለማወቅ ተቻለ።
ስዩም ተሾመ በማህበራዊ ገጽ በሚያወጣቸው ጽፉፎች ሳቢያ በአገዛዙ ጥርስ ውስጥ መግባቱን የሚናገሩ ወገኖች በተለይ በቅርቡ የዩኒቨርስቲ መምህራንን ለማወያየት በሚል የአገዛዙ ከድሬዎች በዩኒቨርስቲው፡የደረሰባቸውን የዝምታ ተቃውሞ በግልጽ በመጻፍ ያለውን እውነታ ይፋ ያደረገ ሲሆን ያንን መሰረት አድርጎ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ዜጎች ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው ሊታፈኑና ሊታሰሩ እንደማይገባ የሰማአዊ ፓርቲውን ዮናታን ተስፋዬ፣ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጠቅሶ እሱም ቃለ መጠይቅ በመስጠቱ ጭምረ ጥቃት ሊደርስበት ወይም ሊታሰር እንደሚችል ቢያውቅም በአገር ጉዳይ ሀሳቡን በነጻነት መግለጽ እንደሚቀጥል መግለጹ አይዘነጋም:፡በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ሀሳባቸውን በነጻ የገለጹና ስርዓቱን የተቹ ጋዜጠኞችን፣ጦማሪያንን ፣የተቃዋሚ መሪዎችን ማሰርና ማሰቃየት የቀጠለ ሲሆን በሌላ በኩል ተሀድሶ አድርጌ እለወጣለሁ በሚል በኦሮሞ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በኮንሶ የደረሰበትን ተቃውሞ እና የፈጸመውን የንጹሃን ግድአ ለማድበስበስ ይሞክራል፡ ፡ መምህር ስዩም ተሾመ የራሱ ብሎግ በመክፈት ለረጅም ጊዜ ሲጽፍ የቆየ ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ በሚያሻቸው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመጻፍ ፣ለራሱ ለገዢው ፓርቲ መፍትዬ ያላቸውን ጭምር ሲጠቁም የቆየ ሲሆን በቅርቡ የሕዝቡን መሰረታዊ የተቃውሞ ጥያቄ በማንሳት <<ኢህአዴግ መለወጥ አለበት ካልተለወጠ ሕዝቡ ይለውተዋል …>> በሚል ጭምር ስርኣቱ የሕዝቡን ጥያቄ መፍታት የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጭምር ለህብር ሬዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ ጭምር መግለጹ ይታወሳል። ስዩም ተሾመ ከመታፈኑ ቀደም ብሎ ሁለት አስተያቶችን ጽፎ ነበር።በገጹ ላይ መስከረም 17 ቀን 2008 በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በመምህራን የዝምታ ተቃውሞ የቀረበበትን የአገዛዙ ውይይት አጀንዳ መምህራን ለተማሪዎች እንዲያወያዩ ዕቅድ መያዙን አጋልጦ ይሄም ውድቀት መሆኑን ገልጾ ነበር። ስዩም መስከረም 19 ከመታፈኑ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባወጣው ጽሁፍ <<አመፅና ተቃውሞ በራሱ ልማትና ዴሞክራሲ ነው>> በሚል ርዕስ በወቅታዊው ሕዝባዊ ተቃውሞ በስርኣቱ የጉልበት እርምጃ ላይ ሰፋ አለ ትንታኔ ጽፎ ነበር። ስዩም ተሾመ ስለ መምህራን የዝምታ ተቃውሞ ለህብር የሰጠው ቃለ መጠይቅ እነሆ:-