የህብር ሬዲዮ መስከረም 29 ቀን 2009 ፕሮግራም
< …የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አገሪቱን ሙሉ ለሙሉ በሕወሓት ጄኔራሎች ቁጥጥር ስር የሚያስገባ ቀደም ብለው ሲአደርጉት የነበረውን በይፋ በአዋጅ መልክ ተግባራዊ በማድረግ በስልታን ለመቀተል ነው …ሰራዊቱ ወገኖቹ እየተገደሉ ሲያይ አሁን ብዙ በአንዳንድ ቦታዎች ከነ ትጥቁ የሕዝቡን የእምቢታ ሰራዊት እየተቀላቀለ ነው።ይሄ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሰራዊቱ እኛ ከሌለን ትበተናለህ የሚሉት ሀሰተኛ ቅስቀሳ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው።ከጥቂት ዘረኛ የሕወሃት ጄኔራሎችና በቀጥታ በግድያ የተሳተፉት ካልሆነ በስተቀር ሰራዊቱ አይበተንም።ከለውጡ ጎን መሰለፍ አለበትም> ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የሰራዊቱ የቀድሞ የሰራዊቱ ጥናትና ምርምር ሀላፊ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
<…የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሚጥስ በሕዝቡ ላይ የታወጀ የጦርነት አዋጅ ልንለው እንችላለን :፡ በዓለም አቀፍ ሕግ አንድ አስቸኳይ አዋጅ ሲታወጅ መሙዋላት ያለበት የሕግ ግዴታ በዚህ አዋጅ አልተሙዋላ ነው…በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት መግደል አያስጠይቅም ኢሄን ባለፉት ጊዜያት ሲያደርጉት የነበረውን ነገር አጠናክሮ ለመቀተል ስለሆነ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት አባል ባትሆንም ጉዳዩ ወደዚአ ሊአመራ የሚችልበት አማራጭ ስላለ በሕዝቡ ላይ የሚያስተኩሱት በዓለም አቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት በሱዳን በአልበሽር ላይ እንደተደረገው የእስር ትዕዛዝ እንደወጣበት ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲወሰን ግፊት ማድረግ አለብን።እኛ የሕግ ባለሙያዎች የጀመርነው ጥረት …> የሕግ ባለሙያና መምህር ሔኖክ ጋቢሳ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰጠው ሕጋዊ ማብራሪያ (ቀሪውን አዳምጡት
የሟቹ የኢንጂነር ሀይሉ ሻውል የፓለቲካ ጉዞዎች እና ያስምዘገቡት ስኬቶች ሲዳስሱ(ልዩ ጥንቅር)
በአማራ ብሄርተኝነትና በኢትዮጵአ አንድነት ጉዳኢ ከሁለት ወጣት አክቲቪስቶች ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)
ዜናዎቻችን
በኢትዮጵያ ውስጥ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ግቡን እንዲመታ የመከላከያ ሀይሉ ከሕዝቡ ጎን መቆም አስፈላጊነት ተገለጸ
ሰራዊቱ ሕገወጡን አስቸኳይ አዋጅ ወደ ጎን በማድረግ ተግሉን ደግፎ እንዲቆም ተጠየቀ
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ወያኔ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ተጨማሪ ጥፋት ሳያደርስ በጋራ ተባብረው እንዲያስወግዱት ትሪ ቀረበ
በኦሮሚያ በአጋዚ ወታደሮች ላይ በተወሰደ ጥቃት ሰላሳ ሁለት ተገለው ሶስቱ ቆስለው በሕዝብ ቁጥጥር ስር ዋሉ
የሕወሓት/የኢሕ አዲግ አገዛዝ ዜጉችን ለማሽማቀቅ ሲል በአገሪቱ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳለፈ
በአ/አ የግብጽ አምባሳደር ከአገዝዛዙ ባለስልጣናት ለማብራሪያ ተጠሩ
ኢትዩጵያ ውስጥ ሰሞኑን ህይወቷን ያጣችው አሜሪካዊት ተመራማሪ የመታስቢያ ፕሮግራም ተካሔደላት
ከኢትዪጵያ ወደ እስራኤል ሊጎዝ የነበረ ቤተ እስራኤላዊ ጎንደር ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ተገለጸ
ዱባይ የ15 ሚልዪን ኢትዮጵያዊያን ህፅናትን ነፍስን ልትታደግ ነው
ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑን ለሕዝብ ያስረከብ ሲል መግለጫ አወተ
አዲስ የፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋን የቀድሞው ኢ/ር ይልቃል ባልተገኙበት ስብሰባ አስመረጥኩ አለ
በቬጋስነ በፊኒክስ ኢትዮጵአውያን በአገር ቤት የሚፈጸመውን ግፍ በመቃወም የተገደሉ ወገኖቻቸውን በማሰብ ሻማ ማብራት አካሄዱ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።