በሜዲትራንያን ባህር ላይ የምትገኘው ሰፊዋ ደሴት ሲሲሊ የብዙ ሺህ አመታት ባለ ታሪክ የጥንታዊ ስነ ሰእል ስነ ህንጻ እና የዘርፈ ብዙ ባህል ባለቤት ናት፡፡ ጥንታዊቷ ሲሲሊ በ1860 በጣልያን ስር እስክትካተት ድረስ በተለያዩ ቅኝ ገዥዎች ስር ተዳድራለች፡፡
የዚህ ጽሑፍ አላማ የሲሲሊን ታሪክ ማስተዋወቅ ሳይሆን የወያኔው ማፍያ ክሲሲሊው ማፍያ ጋር ያለውን መመሳሰል ከእኔ እይታ አንጻር ለማሳየት ነው፡፡
የሲሲሊው ማፍያ በ19ነኛው ክ/ዘመን መጀመርያ ላይ እንደ አስፈላጊ የህብረተሰብ መዋቅር የተዋቀረ ሲሆን መሰረተ ውቅረቱም የሲሲሊ ጭቁን ገበሬዎች ከአስተዳዳሪዎቻቸው የሚደርስባቸውን በደል ለመታገል እና ለአስተዳደር የሚቀርብ ግጭት በመካከላቸው ሲከሰት ወደ ተመረጡት አለቆች [ካፖዎች] በመቅረብ መፍትሄ በቀላሉ ለመስጠት ነበር፡፡
ሲሲሊያውያን አለቆች [ካፖዎች]በየአካባቢያቸው ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ህዝቡን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ህዝቡም ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ ለትግል ይጠቀሙበት የነበረውን ለገዥዎች መረጃ ያለመስጠት አይቶ እና ሰምቶ ዝም ማለት [ኦሜርታ]የተባለውን ጥንታዊ ህጋቸውን አክብረው ኖረዋል፡፡ዛሬም የሲሲሊያውያን መገለጫ ሆኖ ይነገራል፡፡
በዚህ መልክ ለማህበረሰቡ በሚስጢር ዳኝነት ለመስጠት የተቋቋመው መዋቅር ቀስ በቀስ ወደተደራጀ ወንጀለኝነት ተለውጦ ዛሬ ለአለም ጠንቅ የሆነውን ማፍያ ለመፍጠር ብቃ ፡፡
የአይቶ እና ሰምቶ ዝም ማለት[ኦሜርታ] ህግ እና ከአብራኳ በወጡ ጥቂት ማፍያዎች ምክንያት ሲሲሊ በሌሎች የጣልያን ግዛቶች በሚኖሩ ዜጎች ዘንድ የተጠላች ሆነች ፡፡በአለም ህዝብ ዘንድም እንደ ወንጀለኞች እናት ተቆጠረች ፡፡ ሌላው ቀርቶ ከአብራኳ የተገኙ ድንቅ እግር ኳስ ተጫዋቾች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀሩ፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ጣልያን ባሰናዳችው የ1990 የአለም ዋንጫ 6 ጎሎችን አስቆጥሮ ኮኮብ ግብ አግቢ የሆነው ሳልቫቶሬ ስኪላቺ በሲሲሊ ተወላጅነቱ ብቻ የሚገባውን አድናቆት አለማግኘቱ እና የእግር ኳስ ህይወቱ መበላሸቱ የሚታወስ ነው፡፡
ሲሲሊን እና ትግራይን የሲሲሊ ማፍያን እና የወያኔ ባለስልጣናትን የሚያመሳስላቸው ነገር በእኔ እይታ የሚከተሉት ይመስሉኛል፡፡
1-ለትግራይ ጭቁን ህዝብ ነጻነት ተደራጀሁ ያለው ወያኔ ከጅምሩ ራሱን ወደለየለት ወንጀለኝነት
መቀየሩ፡፡
2-በጥቂት ወንጀለኞች ምክንያት የትግራይ ህዝብ በሌላው ህዝብ እየደረሰበት ያለው ዘመገለል
አደጋ[ምንም ልንሸፋፍነው ብንሞክርም እንኳን]
3-የትግራይ ህዝብ ከአብራኩ የተገኙ ወንጀለኞች በፊት አውራሪነት በሃገሪቱ ላይ ያሉትን ከልክ ያለፈ መከራ እያዩ እና እየሰሙ ዝምታን መምረጣቸው፡፡ እና …. ሌሎችም ፡፡
የትግራይ ህዝብ እና የሲሲሊ ህዝብ በብዙ ነገር የሚመሳሰሉ ቢሆንም ወያኔን ግን ከሲሲሊ ማፍያ የከፋ ከሚያደርገው ጥቂቱ የሚከተለው ነው፡፡
ይኽውም የሲሲሊው ማፍያ በህቡ የተደራጀ ሲሆን ወያኔ ግን በህቡ እና በግልጽ መደራጀቱ ነው፡፡
ወያኔ በህቡ ከፍተኛ ሃብት የሚያግበሰብስ ሲሆን በግልጽም ወደመንግስት ካዝና በፈለገው ጊዜ እና ሁኔታ እጁን መሰንዘር መቻሉ፣ የሚቃወሙትን እስር ቤት ምጎር መቻሉ [ሃይለማርያም ደሳለኝ እስር ቤት ያለው ባለሃብት ያሉን ወያኔን ይሆን] የጦር ሰራዊቱን እንደ ግል ጠባቂው መጠቀሙ እና ህዝብን ከህዝብ እስከማጋጨት የሚደርሰው ጨካኝ ሴራው ከማፍያዎች ሁሉ የከፋ ያደርገዋል፡፡
ወያኔ በህቡ እና በግልጽ በአሻንጉሊት ባለስልጣናት እየተረዳ መቀጠሉ እንደ ካንሰር ለመድሃኒት ያስቸገረ አድርጎታል፡፡
በመጨረሻም ይህን ሃገሪቱ ላይ የተንሰራፋ ካንሰር ለማጥፋት መድሃኒት አለን የሚሉ ቡድኖች እና ግለሰቦች በተናጠል የቀመሙት መድሃኒት ውጤት አልባ ስለሆነ በጋራ በመሰባሰብ ኢትዮጵያን የሚያድን መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል፡፡ ጊዜውም አሁን ነው!!!
አንበሳው( ከ22 ማዞርያ በቅኝ ግዛት ከተያዘው ሰፈር)
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።