<… ዛሬ ዛሬ ትላንት ሲደረግ እንደነበረው ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ጉዳይ በአንድ ድምጽ በማህበራዊ ሚዲያው ትኩረት አድርገው በመግባባት የሚያደርጉት የጋራ ትግል እየተዳከመ እንደውም መግባባት እየቸገረ የሄደበት መንገድ በአግባቡ ሊፈተሽ ይገባል..> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚያደርጋቸው ውይይቶችን በተመለከተ በህብር ሬዲዮ ውይይት ላይ ተጋብዞ ከሰጠው ምልሽ(ቀሪውን ተከታተሉ)
<…በማህበራዊ ሚዲያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምታየው ንትርክ አለመግባባት ችግር ትኩረት ዋናው ጠላት ላይ ያለማድረግ ነው። መወያት መነጋገር መልካም ሆኖ ለውጥ ፈላጊው ሀይል ግን ትኩረቱን ዋናው ጠላቱ ላይ ማድረግ እየተወ እንደውም በአንድ ጉዳይ መግባባትና ተመሳሳይ አቋም መውሰድ የማይችል እየሆነ የሄደ ይመስላል ። እናን መስለው በእኛ ቁስል የሀሰት ስም እያወጡ የእኛኑ ትንንሽ ልዩነት የሚያጋግሉም እንዳሉ መዘንጋት የለብንም እነዚህን እንዳሰማራ ራሱ ስርዓቱም አምኗል ነገር ግን…> እሸቱ ሆማ ቀኖ በማህበራዊ ሚዲያው የአገዛዙን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማስረጃ በማጋለጥ የሚታወቀውና የማህበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊ በወቅታዊው የለውጥ ፈላጊው ሀይል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታዩ ንትርኮች ላይ በህብር ሬዲዮ በተደረገው ውይይት ላይ ተሳትፎ ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
<… በማህበራዊ ሚዲያ ዋናው ትኩረታችንን ጠላታችን ወያኔ ላይ እንዳናደርግ አንዳንዶች በየዋህነት አንዳንዶች ደግሞ ሆን ብለው የሀሰት ስም ታጥቀው እርስ በእርስ እንዳንግባባ የሚፈልጉ አሉ ።ከሱ በላይ ይሄ ጭቃውን፣እሾሁን ስድቡን ፈርቶ በዝምታ የሚያየው አብዛኛውም ሀላፊነት አለበት ዝምታ አያዋጣም…ዛሬ በጎንደር እየተደረገ ያለው ትግል እየሞተ ያለው ገበሬ በሌላውም ወገኑ ትግሉ መደገፍ አለበት። ወያኔን አስቀምጦ ነገ ምን አይነት መንግስት ነው የሚመሰረተው የሚለው አይደለም የዛሬው ትኩረት ተባብሮ ዌአኔን መታገል ጭምር ነው የትጥቅ ትግሉን የቀረውም ኢትዮጵያዊ ሊቀላቀለው ይገባል…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሀንስ https://www.youtube.com/watch?v=KdOJ3D8bERAበወቅታዊው የለውጥ ፈላጊው ሀይል በማህበራዊ ሚዲያ የሚታዩ ንትርኮች ላይ በህብር ሬዲዮ በተደረገው ውይይት ላይ ተሳትፎ ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)