Hiber Radio: በመተማ የሕወሓት የደህነት ወኪል ተገደለ ፣የሕወሓት/ኢህአዴግ የሰሞኑ የሙስና ዘመቻ ዋነኛ ሌቦቹን እነ አባይ ጸሐዬን ካላሰረ ከፕሮፖጋንዳ ፍጆታ አያልፍም ተባለ ፣አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለኦሮሞ ሕዝብ መገንጠል መፍትሄ አለመሆኑን ገለጹ፣ኤርትራ የአሰብን ወደብ ለአረቦች አላከራየሁም ስትል ዳግም አስተባበለች፣አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በጸረ ግብጽ አመለካከታቸው ዙሪያ የተሳከረ አቋም እንዳላቸው ተገለጸ፣በኦባማ ስም መንገድ ሊሰየም ነውና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ታህሳስ 23 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ይሄ ሁሉ መስዋዕትነት ተከፍሎ ሕዝባዊ ትግሉ በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞና ተጋድሎው ለምን እንደ ሌሎች አገሮች መንግስት አልለወጠም ? የሚለውን ማየት ያለብን በሌሎች አገሮች በተወሰነም ደረጃ ወታደሩ ምንም ስርዓቱ አምባገነን ቢሆን በወታደራዊ ዲሲፕሊን የታነጸ፣አገሩን የሚወድ ነው ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ዘረኛ ሽፍታ ነው ለአገርም ለሕዝብም ግድ የሌለው ከዚህ ስርዓት ጋር የሚደረገው ትግልን ከሌሎቹ ጋር ማነጻጸር ይከብዳል ሌላውበስርዓቱ አፈና የተጀመረው ተቃውሞና ተጋድሎ ይዳከማል ወይ ቢባል ተቃውሞው በተለያዩ ምክንያት ሊዳከም ይችል ይሆናል ተጋድሎው ግን የአማራን ተጋድሎ ብታይ እየተጠናከረ የማይመለስበት ደረጃ ላይ ደርሷል …> አክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ(ክፍል አንድን ያድምጡት)

የቀድሞው የኢራቁ ፕ/ት ሳዳም ሁሴን ለአሜሪካኖች የስጡት ምክር እና እውነታው ሲገጣጠሙ

“ፕ/ት ሳዳም በህይወት ኖረው ኢራቅን ዛሬ ቢገዙ እመርጣለሁ”ሳዳም ሁሴንን ለመጀመሪያ ጊዜ የመረመረው የሲአይ ኤው ሹም ሰሞኑን ከሰጠው እማኝነት የተወሰደ(ልዩ ዘገባ)

<…የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ እውነተኛ የዘር ግንድ በጥናቴ እንዳሳየሁት ቤተሰብ ናቸው ።ኦሮሞ ለአማራ አጎቱ ነው። ልዩነትን እየፈጠሩ በሀሰት ማስረጃ መለያየቱን ትተን የሚያዋጣን ኢትዮጵያዊነት ነው ኦሮሞ አማራ ብቻ ሳይሆን ሱማሌው፣ሲዳማው ሌላውም ኢትዮጵያው የዘር ሐረግን በግልጽ ማየት የሚቻለው ከዚሁ ነው አንድ ነን ደማችን አንድ ነው። እንበልና እኔ ጀርመን አገር ሳለሁ አንድ ወንድ ልጅ ወልጃለሁ እዚህ አሜሪካ ሌላ ልጅ አለኝ ጀርመን ያለው በጀርመንኛ ስለተናገረ አሜሪካ ያለው በእንግሊዝኛ ስለተናገረ የእኔ ልጆች መሆናቸው ይቀራል? ቋንቋን መለያያ ማድረግ አደረኛ ነው። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ የመለያያ ምክንአት ሊሆን አይገባም። ትውልዱ እውነተኛውን ታሪክ ማወቅ መመርመር አለበት…> ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ በቬጋስ ተገኝተው መጽሐፋቸውን በተመለከተ  ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ክፍል ያድምጡት)

<…ምዕራባውያን የሚመለከቱት በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ቢወድቅ ማነው የሚተካው የሚለውን የሚመልስ ይፈልጋሉ።በአካባቢው አገር የሚፈልጉትን መረጋጋት ማስቀጠል ዓላማቸው ነው።ተቃዋሚው ያንን ክፍተት መሙላት ሲገባው ተበታትኖ መታየቱ እነሱ መንግስት ለሚፈጽመው የሰብኣዊ መብት በመግለጫ አንዳንዴ እያስፈራሩ ሌላ ጊዜ እየተለማመጡ ማስቀጠል ነው ተቃዋሚው ግን ለዚህ በቂ መልስ የሚሰጥ ስራ ለምን አልሰራም የሚለውን ካየን …> ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ በእንግሊዝ የኪል ዩኒቨርስቲ መምህር በወቅታዊ ጉዳይ ለህብር ከሰጠው መግለጫ የተወሰደ(የመጨረሻ ክፍል ያድምጡት) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በመተማ የሕወሓት የደህነት ወኪል ተገደለ

እርምጃው ለስርዓቱ መረጃ ለሚያቀብሉት ማስጠንቀቂያ ነው ተብሏል

የሕወሓት/ኢህአዴግ የሙስና ዘመቻው ዋነኛ ሌቦቹን እነ አባይ ጸሐዬን ካላሰረ ከፕሮፖጋንዳ ፍጆታ አያልፍም ተባለ

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በጸረ ግብጽ አመለካከታቸው ዙሪያ የተሳከረ አቋም እንዳላቸው ተገለጸ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ለኦሮሞ ሕዝብ መገንጠል መፍትሄ አለመሆኑን ገለጹ

አቶ በቀለ ገርባም ሆኑ / መረራ ሊታሰሩ እንደማይገባ ለአገር አሳቢዎች እንጂ አሸባሪዎች አለመሆናቸው ተናገሩ

ኤርትራ የአሰብን ወደብ ለአረቦች አላከራየሁም ስትል ዳግም አስተባበለች

“የአረብ ጋዜ ጦች እና ጸሀፊዎች አፍቃሪ ኢህአዲግ መሆን አሳፋሪ ነው” የኤርትራ መንግስት መግለጫ

/ መረራ ጉዲና በአገዛዙ የተፈጠረ ወንጀል በእስር ላይ መቆየታቸውን ተቃውመው በዋስ ለመፈታት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መሆኑ ተገለጸ

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ቀርቦበት በነበረው የሽብርተኝነት ክስ የጠራቸው ምስክሮች ሳይሰሙ ክሱ ተሻሻለ ተባለ

የሕወሓት የደህነት ቢሮ የአማራ ገበሬዎች የጎበዝ አለቆችን  ለመግደል ወይም ለማፈን እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ

በተሰናባቹ የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ በስማቸው መንገድ ሊስየምላቸው ነው

“ለ3ኛ ዙር ብወዳደር ኖሮ ትራምፕን በቀላሉ አሽንፋቸው ነበር”ፕ/ት ኦባማ

“ዝም ብለው ቤተመንግስቱን ይልቀቁ፥ሲያምሮት ይቅር” ትራምፕ ሌሎችም

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *