<…ተቃዋሚዎች ጋር እንደራደራለን የሚሉት እነሱ ቀለብ ከሚሰፍሩላቸው የስም ተቃዋሚዎች ጋር አንዳንዶችም በስልክ እየተጠሩ ገና ለገና እንታሰራለን በሚል የሚደረግ ሕወሃት/ኢህአዴግ ለራሱ ፕፖፖጋንዳ የሚያደርገው እንጂ ዶ/ር መረራ፣በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ የተቃዋሚ መሪዎችና አባላት፣ጋዜጠኞች ታስረው ተቃዋሚ አጥፍተው ያው ለምዕራባውያን ፍጆታ ካልሆነ እንዲህ ያለው ማታለያ አይሰራም…> አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ ዱቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሊቀመንበር ሰሞኑን ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ከተቃዋሚዎች ጋር እያደረኩ ነው ስለሚለው ውይይትና ድርድር በተመለከተ ከህብር ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ያድምጡት)
<…የሕወሃት ባህሪ ከበረሃ ጀምሮ የሚከተለው ተመሳሳይ ስልት ነው። ሲጨንቀው እንደራደር ይላል በእውነተኛ ድርድር አያምንም። በረሃ ለድርድር የጠሯቸውን በተኙበት ገሏል። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሚከተሉት ያንኑ ነው። አሁን እነሱ ድርድር የሚሉትን ማጭበርበሪያ ማንም አይቀበለውም ይልቁን ራሳቸውን ነው የሚሸውዱት … ይሄ ሁሉ ተቃዋሚ ታስሮ ና ተደራደር ስትባል ከረቫት አስረህ መሄድ ክህደት ነው …> አክቲቪስት መስፍን አማን በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበርና ከቀድሞ የቅንጅት መሪዎች አንዱ ገዢው ፓርቲ እያደረኩ ነው ስለሚለው ድርድር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ያዳምጡት)
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 ፣ 5639993994 ወይም 563999-3988 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።