የህብር ሬዲዮ የካቲት 12 ቀን 2009 ፕሮግራም
<…የየካቲት 12 ሰማዕታትን ስናስብ ያ በወኖቻችን ላይ በግራዚያኒ የተፈጸመ ግፍ ፈጽሞ ሊረሳ አይገባም። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችን በመርዝ ጋዝ፣በመሳሪያ፣በቦንብ ጨፍጭፏል ለዚያ የጦር ወንጀል እና ከኢትዮጵያ በጦርነቱ የተዘረፈው ንብረት ዛሬም በቫቲካን ይገኛል። ሌሎች አገሮች ተገቢውን ካሳና የቶር ወንጀሉም በተገቢው እንዲመዘገብ እያደረጉ ነው …የአባቶቻችንን ታሪክ መዘከር ብቻ ሳይሆን እንዴት ዛሬ እኛ እያለን ወገኖቻችንን ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ ሐውልት ቆሞ ይህን ለመቃወም ፊርማ ሲሰባሰብ አራት ሺህ ሰው ብቻ ይፈርማል? የኢትዮጵያ ምሁራን ለዚህ ትኩረት መስጠት አለባቸው። የዚህ ሐውልት መቆም… > አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር የየቲት 12 የሰማዕታትን መታሰቢያ በተመለከተ ከህብር ተጠይቆው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ቀሪውን ያድምጡት)
የዘንድሮ የታክስን በተመለከተ የተለያዩ ታክስን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተን ውይይት ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ አቶ ተካ ከለለ ጋር የተደረገ ቆይታ (ልዩ ቃለ ምልልስ)
መላው ቤተስባቸው በኢትዩጵያ እና በህዝቧ ፍቅር የተለከፈው የታሪክ ተመራማሪው እና የመብት ተሟጋቹ የ አንጋፋው ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስትገድል እና ዝክር(ልዩ ዘገባ)
ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ በእውቁ ባለቅኔ አንደበት (የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ስንዘክር )
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከቤተስቦቼ ጋር ዳግም ብቀላቀልም የጀመርኩትን ስላማዊ ትግል እገፋበታለሁ አለ
“የትም ብኖር የአገዛዙ የእስራት እና የግድያ ስለባ የሆኑት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቼን አልረሳም“አትሌት ፈይሳ
የሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ አመራሮች አገዛዙ ለሌላ ሰጥቶ ያፈረሰባቸውን ፓርቲ ዳግም ለመታደግ አስተባባሪ ኮሚቴ መረጡ
በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት የአማራ ሰላማዊ ታጋዮች አንዱ በመርዝ ሌላው በመኪና ተገደሉ
በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ጎሳዎች መካከል የተቀሰቀስው ውጥረትአልበረደም፣ግጭቱ የስው እና የንብረት ጥፋት አስከትሏል፣ለግጭቱ መባባስ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተጠያቂዎች ሆነዋል
የሕወሓት ኮማንድ ፖስት ሕገመንግስቱን የሚጥስ መሆኑን ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ገለጹ
የፕ/ት ትራምፕ አስተዳደር በመቶ የሚቆጠሩ ስደተኞችን አስረ
ከሰላሳ ዓመት በላይ በአሜሪካ የኖረው ኤርትራዊው የመብት ተሟጋች ወደ አገሬ እንዳልባረር ስጋት ገብቶኛል አለ
ስገጋት የገባቸው ስደተኞች ከአሜሪካ ወደ ካናዳ በእግራቸው ድንበር እያቀቋረጡ እየገቡ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ላልተበደሩት ማዳበሪያ ታስረው እንዲከፍሉ መገደዳቸው ተዘገበ
የሙሴ ጽላት በእየሩሳሌም አቅራቢያ ተቀብሯል ያሉ የእስራኤልና ፈረንሳይ አጥኒዎች ቁፋሮ ሊጀምሩ መሆኑን ገለጹ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።