የህብር ሬዲዮ የካቲት 19 ቀን 2009 ፕሮግራም
እንኳን ለ121ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን
<…የእነዶ/ር መረራም ሆነ የበቀለ ገርባ ፣የጋዜጠኞቹ የእነ እስክንድር ነጋ፣የተመሰገን ደሳለኝ እነ ኦልባና እና ሌሎችም ዛሬ በየእስር ቤቱ እየታሰሩ የሚገኙት ሁሉ ወንጀላቸው የሕዝቡን እውነት ያለውን ሙስናና የተበላሸ ስርዓት መቃወማቸው ነው። የሰሞኑም ክስ የተቃውሞ ድምጽን ሙሉ ለሙሉ ለማፈን የሄዱበትን የፍርሃት ደረጃ ያሳያል።ስርዓቱ ዘጠና ከመቶ ወድቋል ደካማነቱን እንጂ ይሄ የፈጠራ ክስ ጥንካሬውን አያሳይም…በዲያስፖራው መካከል እርስ በእርስ የሚያናቁሩ የወያኔ ሰዎች ተሰማርተዋል ። ዛሬ በትንሽ በትልቁ ወያኔን አስቀምጠን እርስ በእርስ የምንጨቃጨቀውን ወደ ጎን ማድረግና መተባበር ያስፈልግል። ይህ ካልሆነ አሁን እየተሰራ ያለው የወያኔን ስራ ነው …> አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ንቅናቄ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሊቀመንብር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በአሜሪካ ሲኖሩ የነበሩና ወደ ካናዳ ድንበር አቋርጠው የገቡትም ሆነ የሚገቡ ሊያውቋቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ የካናዳ ሕግ ከሌላ አገር በቀጥታ የሚመጡት ላይና ከአሜሪካ ከሚገቡት ላይ የተለያየ ነው። ካናዳ ለስደተኛ ብዙ ነገር ጥሩ ነው ጉዳይህ በሁለት ወር ያልቃል ።ነገር ግን ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችም አሉ። አንድ ሰው አሜሪካ እያለ የነበረው ማንነትና ካናዳ ሲገባ ደግሞ…> ጠበቃ ተክለሚካኤል አበበ (ልጅ ተክሌ) ከአሜሪካ ወደ ካናዳ በድንበር አቋርጠው አስቀድሞ በገቡና ወደፊትም በሚገቡ ላይ ያሉት ሕጋዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪአ(ክፍል አንድን ያድምጡት)
አድዋ ግጥም
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከአገሬው ጸረ-ስደተኛ ተቃዋሚዎች እየደረሰባቸው ያለው የጥቃት ዘመቻ እና ምላሾቹ ሲዳሰሱ(ልዩ ዘገባ)
<…ለአድዋ ድል ሌላው አስተዋጽዎ ያደረገው አስቀድሞ በተደረገው የዳግማዊ የአጼ ሚኒሊክ የዲፕሎማሲ ቡድን ወደ ጣሊያን ሄዶ አመጣው መሳሪያ ስለ ውጫሌ ውል ጉዳይ የጣሊአንን ተንኮል ያወቀው ያኔ ነው… ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን በዘርና በጎሳ ከፋፍሎ ነበር ለማሸነፍ አቅዶ የነበረው እሱ አልተሳካም ዛሬም ያ የሚሳካ አይመስልም።ትውልዱ ግን የአባቶቹን አኩሪ መስዋዕትነት በአግባቡ ማወቅ የተፈጸመበትን ግፍ መረዳትና ተገቢውን ተቆርቋሩነት ማሳየት አለበት…> አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ ተወሰደ(ሁለተኛ ክፍል ቀሪውን ያዳምጡት)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
የሕወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹም ሶማሊያ ውስጥ በተካሄደ ወታደራዊ ምክክር ላይ እንዳይገኙ ታገዱ
“እርሶ ከዚህ ስብስባ ላይ መገኘት ስለማይችሉ አዳራሹን በእስቸኳይ ለቀው ይውጡ”የሶማሌያው ጄ/ል ለኢህአዲጉ ሹም የስጡት ትእዛዝ
፣የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ ፕሬዝዳንት በዶ/ር መረራ ጉዲና እስር ላይ የኢትዮጵያው አገዛዝን ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቁ
፣አገዛዙ ተቃዋሚዎች ካላቸው ጋር ከሚያደርገው ድርድር የተለየ ውጤት እንደማይጠበቅ ተገለጸ
የታሰሩት ተፈተው በድርድሩ እንዲሳተፉ ለድርድር ተቀመጥን ያሉት ተቃዋሚዎች ሊጠይቁ እንደሚገባ ተገለጸ
፣ሱዳን በግዛቷ የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ና ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይሻገሩ ጥረት እያደርግሁ ነው አለች
የካርቱም የጸጥታ ሀይሎች 28 ስደተኞችን ከአጋቾቻቸው አስለቀቁ
፣በደ/አፍሪካ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደትኞች የንግድ ተቋማት ሰሞኑን የዘረኞች ጥቃት ሰለባ ሆኑ
ታንዛኒያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የምታደርገው አሰሳን አጠናክራለች
በእነ ዶ/ር መረራ ላይ የተመሰረተው ክስ ዓላማ ፈጠራና የስርዓቱ አፍኖ ለመግዛት የያዘውን ዓላማ ለማሳካት መሆኑ ተገለጸ
፣የዋሽንግተን ገቨርነር ሕገ ወጥ የተባሉ ስደተኞችን የሚያሳድደውን የትራምፕን ትዕዛዝ በግዛቱ ተግባራዊ እንዳይሆን በስልጣናቸው አገዱ
የፕ/ት ትራምፕ አስተዳደር በርካታ ታዋቂ ሚዲያዎች ወደ ዋይት ሀውስ ገብተው እንዳይዘግቡ አገደ፣ጋዜጠኞቹ እንደዚህ አይነት ፈተና ገጥሞን አያውቅም ይላሉ
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ምክንያት ህንድ ውስጥ ለማረፍ ተገደደ
የእስራኤል ዶክተሮች ፊቱ እና ጭንቅላቱ በጅብ የተቦጫጨቀ ኢትዩጵያዊ ጨቅላ ህይወትን ታደጉ
የህጻኑ ሕይወትን ለመታደግ የኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች ጣልቃ ገብተዋል
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።