የህብር ሬዲዮ የካቲት 26 ቀን 2009 ፕሮግራም
<… ስርዓቱ ዛሬም ድረስ ስልጣን ላይ የቆየው ሕዝቡን እርስ በእርሱ በማጋጨት በተለይ የአገሪቱ ምሰሶዎች የሆኑትን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብን በማጋጨት ነው ።እነሱ እሳትና ጭድ እንደሚሉት ሳይሆን የኦሮሞና የአማራ ሕዝቦች አንድ ላይ የኖሩ በጋራ የሚያስተሳስራቸው ብዙ ነገር አለ።…በአገር ቤት በሕዝቦች መካከል የሚታየው አንድነት ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል በውጭ የሚታዩት እርስ በእርስ የመራራቅ ነገሮችን ለማቀራረብ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በአንዳንድ ቦታዎች የጋራ ፎረም በማድረግ አየተንቀሳቀሱ ያሉ አሉ ።እዚህ ያለው ሁኔታ ግን አገር ቤት ባለው ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ የለውም። ለወደፊቱም ቢሆን…> ዶ/ር ዲማ ነጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)
<…በምንኖርበት አገር የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ መብታችንን ተጠቅመን መሳተፍ የእኛ ፍላጎቶችን የሚወክሉ ስለእኛ የሚናገሩ የሕዝብ ወኪሎችን መምረጥ መሳተፍ አለብን። ቁጥራችን ብዙ ነው የፖለቲካው ተሳትፏችን ስለሌለ እኛ ላይ ተጽዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን እንኳ ማስለወጥ አንችልም። አሁንም አሽከርካሪዎችን ሊጠቅም የሚችል የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣንን አደረጃጀት የሚቀይር ህግ ተግባራዊ ሊሆን ነው ።ካልደገፍንና ካልተሳተፍን ግን…> አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በቬጋስ በዲሞክራቲክ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን ተሳትፏቸውን በማሳደግ ለመብታቸው እንዲቆሙ ስለሚያደርጉት ጥረት ከሰጡን ገለጻ(ቀሪውን ያዳምጡት)
<…አድዋን የሚያጥላሉት ብቅ ብቅ ያሉት እውነተኞቹ የታሪክ ምሁራን ዝምታን መርጠው የፈጠራውን የፖለቲካ ታሪክ ማጋለጥ ስላልቻሉ ነው… ሻዕቢያና መሰሎቹ አድዋን የሚያጥላሉት የራሳቸውን አገር ለመመስረት ድሉ የፈጠረው ስሜትና አንድነት እንቅፋት ይሆንብናል ብለው ስለሚፈሩ ነው… ብዙዎቹ አገሮች ወይ ቅኝ ግዛት ገዝተዋል አሊያም በቅኝ ተገዝተዋል የእኛ አለመገዛት ምልክቱ ታላቁ የአድዋ ድል ነው… >
የአድዋን ድል ማጥላላት ለምን ተፈለገ ልዩ ቃለ መጠይቅ ከአክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩና ከዶ/ር ተሾመ ሞገሴ ጋር (አድምጡት)
በኢትዪጵያ የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች እየደረስባቸው ያለው የስራ እድል ተጽእኖ እና ያስከተለው ቀውስ ሲዳስስ (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
የኢትዮጵያው አገዛዝ የመከላከያ ሰራዊት በስምንት ተሽከርካሪዎች ታጅቦ ለውጊያ ከጅቡቲ ግዛት ሰፈረ
አርበኞች ግንቦት ሰባት ትግሉም ስልጠናውም አገር ቤት ገብቷል ከዚህ በሁዋላ በኤርትራ ስልጠና አይሰጥም አለ
ትግሉን መቀላቀል የፈለገ ወደ ኤርትራ ሳይሆን የአገር ቤቱን ትግል ይቀላቀል ሲል ጥሪ አቀረበ
በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ስዎች በጭንቀት ህመም እንደሚስቃዩ አለማቀፍ ጥናት ይፋ አደረገ
ዶ/ር ዲማ ነጎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኖረም አልኖረ በአገር ቤት ትግሉ እንደሚቀጥል ገለጹ
በሕዝቦች መካከል የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል
የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ የቀድሞው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ስልኬን ሲጠልፉ ነበር ማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ አስነሳ
በዶላር ዕጥረት ሳቢያ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ዋጋ እስከመቀነስ ሄደዋል
የህዳሴው ግድብን ለማጥቃት ኤርትራ ታጣቂዎችን አስታጥቃ ላከችብኝ ለሚለው የኢህአዲግ ስሞነኛ ውንጀላ የአስመራ መንግስት ምላሽ ስጠ
የኡጋንዳው ፕ/ት ሙሴቭኔ የአባይን ውሃ በጋራ ያለመጠቀሙ እንቆቅልሽ አልገባኝም ሲሉ ጠየቁ
በኢትዮጵያ ሁሉንም ያሳተፈ ከፍርሃት የሚያላቅቅ ቅንጅት ያስፈልጋል ተባለ
የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ሌሎችንም በንቅናቄው ለማካተት እየሰራ መሆኑን ገለጹ
በኢትዮጵያ የሚገኙ ስድስት የሙስሊም ትምህርት ቤቶች በፓለቲካ ጫና ተሸጡ
በኢህአዲግ ማጎሪያ ቤት ውስጥ ለሚማቅቁት ለግንቦት 7ቱ ለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ እማካሪ ማመቻቸት ጠቀሜታ እንደሌለው አንድ ከፍተኛ የእንግሊዝ የህግ ባለሙያ አስጠነቀቁ
“እንግሊዝ በአንዳርጋቸው ዙሪያ ከኢህአዲግ ጋር ፊት ለፊት መነጋገር አለባት”የህግ ባለሙያው ኬን ዶምኒክ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።