አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በቬጋስ ነዋሪና ማህበረሰባችን በግዛቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን በማሳደግ ተሰሚነት ማግኘት አለበት ብሎ መንቀሳቀስ ጀምሯል። በከተማዋ በተለይ በሰፊው የትራንስፖርትና የሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ በብዛት ለሚሰሩ ወገኖቼ ድምጻቸው እንዲሰማ እሰራለሁ ብሎ ተነስቷል። አሽከርካሪዎችን የሚመለከቱ አዲስ አሰራር መዘርጋት የሚቻልባቸውን ሁኔታዎችንና ሌሎቹንም ጥያቆዎቻችንን ለማስመለስ አስቀድሞ ራሳችንን ማደራጀት አለብን ይላል። በመጪው ረቡዕ ማርች 22/2017 በክላርክ ካውንቲ ዲሞክራቲክ ቢሮ ከ5 ፒኤም ጀምሮ ስብሰባ ጠርቷል። ከሁለት ሳምንት በፊት ከአቶ አሌክሳንደር ጋር ስንወያይ ስብሰባው የተጠራው ለማርች 15 የነበረ ሲሆን በሁኔታዎች አለመመቻቸች ወደ ማርች 22 የፊታችን ረቡዕ ተዛውሯል።ለመሆኑ አሌክሳንደር አሰፋ ማነው? እና ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተናል። ውይይቱን ያድምጡት::
የስብሰባው ዕለት ማርች 22/2017
ክላርክ ካውንቲ ዲሞክራቲክ ቢሮ
አድራሻ 6233 Dean Martin Dr. Las Vegas,NV 89118
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።