የህብር ሬዲዮ መጋቢት 17 ቀን 2009 ፕሮግራም
<… በአዲስ አበባ ውስጥ ማዕከላዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቪላዎች ስም የሌላቸው እስር ቤቶች ሆነው ማሰቃያ ይፈጸምባቸዋል።ሀብታሙ አያሌው የደረሰበትን ሰቆቃ ሲናገር ስሰማ በጣም አዝኜያለሁ ነገር ግን ሀብታሙም ከባህሉ ከሀይማኖቱና ለአድማጭ ጭምር በመጠንቀቁ ሙሉ ለሙሉ የተፈጸመበትን ግፍ የተናገረ አይመስለኝም ።ትላንትም እንደ ሀብታሙ ያለ እና በሀብታሙ ላይ ከደረሰውም በላይ ስም ባላቸውና በሌላቸው እስር ቤቶች ብዙ ግፎች ተፈጽመዋል ዛሬም ያ አልቆመም። ችግሩ ይሄን ሰቆቃ ለአንድ ሰሞን ሰምተን እናዝናለን እንቆጫለን ቆይተን ትኩረታችን ሌላ ነው ።እነዚህን ግፍ ፈጻሚዎች በዓለም አቀፍ የተለያዩ ቦታዎች ለመፋረድ ይቻላል ይሄን ግን ማድረግ አልቻልንም ።አሁንም ግን እነሱን ለመፋረድ ስራውን የሚሰራ ተቋም ያስፈልገናል …> የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂየም በወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድን ያዳምጡት)
<…ኦባማ ኬር የአገሪተ ሕግ ሆኗል ሪፐብሊካንም ሽንፈታቸውን በጸጋ ተቀብለዋል እኛ ከዚህ ብዙ የምንማረው ነገር አለ መብትህን ለማስከበር ድምጽህን ማሰማት ዋጋ አለው ሪፐብሊካኑ የፈሩት ከሕዝቡ እያደገ የመታውን ያልተጠበቀ ተቃውሞ ሳይወዱ በግድ እንደዛቱት የኦባማ ኬርን መሳር አልቻሉም..> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ በኦባማ ኬር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረግነው ውይይት (ቀሪውን አድምጡት)
ባእዳን አገሮች በኢትዮጵያ አጓራባቾች እየቆረቆሩ ያለው ግዙፍ ወታደራዊ ማዕከላት እና ስጋቱ ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)
<…በአዲስ አበባ በስርዓቱ በማን አለብኝነት የባለሙያ ምክር ባለመስማቱ ደረጃቸውን ሳይጠብቁ የተሰሩ ህንጻዎች፣በወቅቱ መታደስ ሲገባቸው ወደ መሬትነት ጭምር የተለወጡ ድልድዮች አሉ። በከተማዋ አነስተኛ የሚባል እንኳ መሬት መንቀጥቀጥ ቢነሳ ብዙዎቹ ህንጻዎች ይደረመሳሉ ድልድዮች ይፈርሳሉ የዚህ ሁሉ መነሻው የስርዓቱ ለሕዝብ ሕይወትና ደህንነት ግዴለሽ መሆን ነው ።የሚጠብቀን ችግር በቆሼ ብቻ አያበቃም…> ዶ/ር ግዛቸው ተፈራ ቴሶ የቀድሞ የአዲስ አበባ መስተዳድር መዘጋጃ ቤት የከተማ ልማት ባለሙያና የዩኒቨርስቲ መምህር ስለ ቆሼው እና ወደፊት በከተማዋ ላይ ስለተደቀኑ አደጋዎች ከሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ የተወሰደ (ክፍል ሁለትን ያዳምጡት)
<…በላስ ቬጋስ ከተማ የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በአሽከርካሪው ላይ ሲያደርስ የቆየውን በደል የሚያስቀር ሙሉ ለሙሉ ቲኤን በሌላ የሚለውጥ የህግ ረቂቅ ነው ።በዚህ ላይ አሽከርካሪዎች አደባባይ ወጥተው ለሕጉ ያላቸውን ድጋፍ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ማሳየት አለባቸው።ይሄ ካልሆነ ግን …>
አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በቬጋስ በዲሞክራቲክ ፓርቲ የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጉዳይ የሚያስተባብረው ቡድን ጊዜያዊ ሊቀመንበር ከሰጠን ማብራሪያ የተሰደ(ቀሪውን አድምጡት)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች የተባሉ እየታፈኑ ወደ ማዕከላዊ ጭምር እንደተወሰዱ መሆኑን ገለጹ
በአገሪቱ እስርና ማሳደድ ስለበዛባቸው በውጭ ያሉ ወገኖቻቸው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጠየቁ
በኢትዮጵያ ውስጥ በእስረኞች ላይ የሚፈጸሙ ኢሰብዓዊ ግፎችን በዓለም አቀፍ መድረክ ለመፋረድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ተጠየቀ
የአ/አበባው ቆሼን ወደ ስንዳፋ አካባቢ ዳግም የማዛወር ወጥን ከማህበረስቡ ተቃውሞ ገጥሞታል
የአገዛዙ የኮምንኬሽን ጉዳይ ሹሙ ዶ/ር ነገሪ ሊንጮ በቆሼው አደጋ ምክንያት ዙሪያ ስሜ ጠፍቷል አሉ
የእስራኤል መንግስት በኢትዩጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤሎችን ካልተቀበለ ብርቱ ዘመቻ እንደሚጠብቀው ተነገረ
“ወገኖቻችንን ያለእስራኤል መንግስት ጣልቃገብነት ማም ጣታችን አይቀሬ ነው“በእስራኤል የቤተእስራኤላዊያን ተወካይ
በርካታ ሶማሌያውያን ረሀብ እና ሞትን ለማምለ ጥ ወደ ኢትዩጵያ እየጒረፉ ናቸው
“ልጆቼን በሞት ከምነጠቅ ባለቤቴን እና ወላጆቼን ጥዩ መስደድን መርጫለሁ“ሶማሌያዊቷ ስደተኛ
በወልቃይት ውጥረት ነግሷል ቁጥጥሩ ጠብቋል ተባለ
የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት የሚባለው ዋናውን የሕዝባዊ ተቃውሞውን ጥያቄ ያልመለሰና ዘላቂ ውጤት ሊያመጣ እንደማይችል ተገለጸ
ኢትዮጵያዊያኖች ለኤርትራዊያን እና ለቻይናዊያን” መልካም አመለካከት የላቸውም” ሲሉ አንድ የታሪክ ምሁር ተናገሩ
“ኢትዪጵያዊያን በአሜሪካ ፍቅር የታወሩ መሆናቸውን ታዝቤያለሁ“አሜሪካዊው የታሪክ ምሁር ዶ/ር ስቱአርት ግሮቨር
ግምቱ 5 ሚሊዪን ዶላር የሚያወጣ የአውራሪስ ቀንድ ከኢትዪጵያ ወጥቶ ታይላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።