የህብር ሬዲዮ መጋቢት 24 ቀን 2009 ፕሮግራም
<… የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም የስርዓቱን ደካማነት ነው የሚያሳየው።የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ መመለስ ስለሚፈራ ያለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስተዳደር አልቻለም ።የታሰሩትን እስካልፈታ የሕዝቡን ጥያቄ እስካልመለሰ የእነሱ አዋጅ ኖረም አልኖረም ትግሉን አያቆሙትም።እስርና ሕገ ወጥግድአው ከአዋጁ በፊትም ነበር እነሱ እስካሉ ይኖራል …ሕዝቡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም የበለጠ ሲታፈን በውጭ ያለው ለውጥ ፈላጊ ወገኑ ከበፊቱ የበለጠ ነበር በአንድ ላኢ መነሳት የነበረበት ያ ሳይሆን መከፋፈል ተስተውሏል አሁን ግን ዲያስፖራው ያንን ማቆም አለበት …> አክቲቪስት ነጌሳ ኦዶ የኦፌኮ ዓለም አቀፍ ቡድን ሊቀመንበርና አክቲቪስት ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን አድምጡት)
<…በቆሼ ወገኖቻችን ላይ የተፈመው ግፍ በአግባቡ መጣራት አለበት። ይሄን ስርዓት ለመታገል የሚደረገው እንቅስቃሴ በጋራ መቀጠል አለበት የሚደረገው የጎንዮሽ ትግል ቆሞ ትኩረታችን ሁሉ ረ ወያኔ ትግሉ ላይ መሆን አለበት ለማለት ጭምር ነው በፕሬዝዳንት ኦባማ ዘመን እንደምናደርገው ዛሬም ሑዋይት ሐውስ መጥተን የተሰለፍነው ይሄ ጉዳያችን ትኩረት እንዲያገኝ ነው…> አክቲቪስት መኮንን ጌታቸው በሑዋይት ሐውስ ደጃፍ የቆሼ ተጎጂዎችን በማሰብ ስለተጠራው የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ገለጻ የተወሰደ(ቀሪውን አድምጡት)
ሳውዲ አረቢያ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ዳግም ጠራርጋ ለማባረር ያወጣችው ሰሞነኛ አዋጅ እና አንድምታው ሲቃኝ(ልዩ ሪፓርታዥ)
በቬጋስ በመጪው ረቡዕ ስለሚቀርበውና የአሽከርካሪዎችን ቅሬታ በከፊል የሚቀርፈው የዋና ተቆጣጣሪ ባለስልጣንን ስለሚያቋቁመው የህግ ረቂቅ የቀረበው ጥሪ
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
በደባርቅ ሕዝቡ የተጠራውን ታላቁ ሩጫን ጎንደር አይሮጥም ብሎ በተቃውሞ ባለመገኘቱ ሳይካሄድ ቀረ
እነ አቶ ማሙሸት አማረ በማዕከላዊ ስቃይ እየተፈጸመባቸው ነው ተባለ፣
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም የስርዓቱን ደካማነት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ
ዲያስፖራው በራሱ ላይ ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳያራዝምና ለጸረ ወያኔ ትግሉ ድጋፍ በጋራ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ
የኢትዮጵያ የቱንም ያህል ብርቱ ፈተናዎች ቢበዙባትም ትንሳዔዋ የማይቀር መሆኑን አንድ የውጭ የመረጃ ተቋም ተነበየ
“ደርግን ለመፋለም ከኤርትራ አማጺያን ጎን የተሰለፉት የወቅቱ ገዥዎች አገሪቱን የባሕር በር አልባ አደርገዋታል” የአሜሪካው የመረጃ ተቋም ትንታኔ
፣የኢህአዲግ መንግስት ለታንዛኒያ የኤለክትሪክ ኃይል ለመሽጥ መዘጋጀቱን የአገሪቱ ፕ/ት አረጋገጡ
ህዝቡ ግን ኢህአዲግ በኤሌክትሪክ ማቋረት እየቀጣን ነው ይላል
ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ስትወድቅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ ሁኔታውን ስትቀርጽ የነበረች ኩዌታዊት ቀጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች
“እባካችሁ አድኑኝ ፣አድኑኝ“የኢትዮጵያዊቷ እህታችን የሲቃ ጥሪ ነበር፤“እባክሽ ቀልድሽን አቁሚና ተመለሺ !”የቀጣሪዋ ምጸታዊ ምላሽ
የኢህአዲግ አገዛዝ ሰሞኑን ያራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቃዋሚዋችን ለመጨፍለቅ እንጂ አንጻራዊ ሰላም እንደማያመጣ ተገለጸ
የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ ጎረቤት ሶማሌያ ከአየር ላይ እንድትደበደብ መመሪያ መስጠታቸው ስጋት ፈጠረ
መድረክ አስቀድሞ ሕዝቡ ለስርዓቱ ጊዜ መግዣ ካለው የተቃዋሚዎችና የስርዓቱ የይስሙላ ድርድር ዘግይቶ ራሱን አገለለ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።