የህብር ሬዲዮ ግንቦት 13 ቀን 2009 ፕሮግራም
<…ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የምንቃወመው በአገር ቤት በፈሙት ወንጀል እሳቸውና ስርዓቱ የሰሩትን ኢሰብዓዊ ድርጊት እንጂ ዘረኛ ደጋፊዎቻቸው እንደሚሉት ከትግራይ ስለሆኑ አይደለም ። ብቃት ባይኖራቸውም ለታላላቅ ኩባንያዎች ዓላማ ማስፈጸሚያ ተመረጡም አልተመረጡም በሳቸውና በስርዓቱ ላይ የሚደረገው ተቃውሞ ይቀጥላል…> አክቲቪስት ዘላለም ተሰማ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብትና የፍትሕ ግብረ ሀይል ለኢትዮጵያ አስተባባሪ ኮሚቴ አንዱ በስዊዘርላንድ የተቃውሞ ሰልፉን አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)
<…ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወንጀላቸው አይነሳ ብለው የሚደግፉዋቸው ዘረኞች ስለሆኑ ነው።ዛሬ የአፍሪካዊነት ተቆርቋሪ የሚሆኑት ትላንት የአፍሪካ አባት የሆኑትን አጼ ሀይለስላሴ ሐውልት በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እንዳይቆም ማድረጋቸውን ረስተው ነው? አፍሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ዶክተሩ አይወክልም …> አክቲቪስት ናትናኤል አስመላሽ ከኦክላሆማ ስበወቅታዊ ጉዳይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡት)
<… ዶክተር ቴዎድሮስ ብቃት እንደሌላቸው የተሾሙት በፖለቲካ ታማኝነታቸው እንደሆነ አሁንም ቅስቀሳ የሚያደርጉላቸው የደበቁትን ኮሌራ ሽፋን የሰጡላቸው ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ግድ የሌላቸው የመድሃኒት እነ ቢል ጌትን ጨምሮ ከጀርባ ይደግፉዋቸዋል። ለእኛ ይሄ ሰውዬው በወንጀል ሊጠየቁ የሚገባቸው ብቃት የሌላቸው መሆናቸውን መቃወም ይገባናል ዘረኛ ደፋፊዎቻቸውን ግን በተመለከተ…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ (ቀሪውን ያዳምጡት)
እውቁ አርቲስት ቴዲ አፍሮን በነጋገር ማግስት የስነልቦና እና የሙያ ስነምግባር ጫና ተፈጥሮበት ስራውን የለቀቀው የኢቲቪው ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ በደጋፊዎቹ እና በተቺዎቹ እይታ ሲቃኝ
በሱዳን እና በግብጽ መካከል ስሞኑን የተቀሰቀሰው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ያስነሳው አካባቢያው ውጥረት ሲፈተሽ(ልዩጥንቅር)
ለአለም የጤና ጥበቃ መቀመጫ የሚወዳደሩት የኢህአዲጉ ዶ/ር ቴድሮስ አድህኖም በመጨርሻው ደቂቃ ላይ እንደ ተሽናፊዋ የአሜሪካ ተወዳዳሪ ሂላሪ ክሊንተን አይነት ዘመቻ ተከፈተብኝ አሉ
“በአገዛዙ ላለፉት አስር አመታት የመብት ረገጣ ሲፈጸም ዶ/ር ቴድሮስ ቆመው ተመልካች ነበሩ”የሪዮው ጀግና አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ለአል ጃዚራ እንደተናገረው (ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
ከስድስት ሚሊዮን በላይ ዜጎቹ በኢትዮጵያ በርሀብ እየማቀቁ የኢህአዴግ መንግስት ብዛት ያለው የበቆሎ ምርት ለኬኒያ ለመሸጥ ተስማማ
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለማግኘት ሲሉ ሌሎች ባለሙያዎች የሰሩትን ጥናት የራሳቸው አድርገው ማቅረባቸው ተጋለጠ
ዶክተሩን የሚደግፉት በሕዝብ ላይ የፈጸሙት ወንጀል የማይታያቸው ዘረኞች መሆናቸው ተገለጸ
በጎንደር የተጠራው ታላቁ ሩጫን ሕዝቡ በተቃውሞ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተገለጸ
የናይጂሪያ መንግስት የኢትዬጵያ አየር መንገድን ከህገወጥ የገንዘብ ገፈፋ ተግባሩ እንዲታቀብ አስጠነቀቀ
የማላዊ የህዝብ ተወካይም አገሪቱ ከኢትዮጵያው አየር መንገድ ጋር ያደረገችው ስምምነት እንዲፈተሽ ጠየቁ
በኢቢሲ የታገደውን የቴዲ አፍሮ ቃለ መጠይቅ ተከትሎ በጣቢያው ውዝግቡና መወነጃጀሉ ቀጥሏል
ማሰልጠኛ እንሰራለን በሚል ገበሬዎችን አፈናቅለው ከኦሮሚያ የወሰዱትን መሬት ሸንሽነው ቤት ሊሰሩበት መሆኑ የተጋለጠባቸው የደህነት ባለስልጣናት ቁጣቸውን ገለጹና ሌሎችም
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ዘገባውን አስተባብሉ ተብለው በደብዳቤ ተጠይቀዋል
የኢህአዲግ መንግስት የአልሽባብ አባላት ባላቸው 23 ስዎች ላይ ከባድ ቅጣት ጣለ፣5ኪሎግራም ስኳር የሰረቀ ኡጋንዳዊ ለወራት ታሰረ
ኢህአዲግ በአወዛጋቢው የሱዳን እና የግብ ጽ የመሬት ይገባኛል ፍጥጫ ላይ ከሱዳን ጒራ ተሰለፈ
የግብጹ ፕ/ት አልሲሲ እና የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ ሪያድ ላይ እርስ በርስ ተወደዳሱ
“ትራምፕ ማለት የማይቻለውን ነገርን የሚተገብሩ ታላቅ መሪ ናቸው”አልሲሲ ስለትራምፕ የተናገሩት፣”በቅርቡ ካይሮን እጎበኛለሁ”ትራምፕ ለአልሲሲ የሰጡት ተስፋ
የዜጎቹን ኮምፒውተሮችን በመሰለል አለማቀፍ ክስ የቀረበበት የኢህአዲግ መንግስት ሰሞኑን የሳይበር ጥቃት ሰለባ ሆንኩላችሁ አለ
በአፍሪካ አህጉር ውስጥ 11 አገሮች የሳይበር ወርበላዎች ተጠቂዎች ሆነዋል
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።