የህብር ሬዲዮ ግንቦት 20 ቀን 2009 ፕሮግራም
<…የኢትዮጵያን ድንበር በምስጢራዊ ስምምነት ለሱዳን እየሰጡ ነው። በድንበር አካባቢ ገበሬዎች የአገራቸውን መሬት አርሰው ለሱዳን ግብር እንዲከፍሉ ተወስኗል። ስርዓቱ የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ስምምነት ያለ ሕዝብ እውቅና ማድረጉ አገር ማፍረስና ክህደትም ነው። ሁሉም ዜጋ እነዚህን አገር አጥፊዎች ድንበሩን አሳልፎ ሲሰጥ …> አቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሰሞኑን በምስጢራዊ ስብሰባ ለሱዳን ተቆርሶ ስለተሰጠው መሬት ይናገራሉ(ቀሪውን አድምጡት)
<…የጊዜ ገደቡ ሊያልቅ ከወር በታች ነው የቀረው ።በሳውዲ ያለን ዜጎች እየተጉላላን ነው።ለህጻናቱ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ አምጡ እየተባለ ያንን ሰጥተን የሚያናግረን የለም በተለይ አማራኛ ተናጋሪን ማንም ዞር ብሎ አያየንም ።ከቆንስላው ጋር ግንኙነት ያላቸው ደላሎች ጉቦ እየተቀበሉ በፍጥነት ይልካሉ ሌላው ግን እየተሰቃየ እየተጉላላ ነው..> አቶ ዋሱ ከሳውዲ አረቢያ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ
<…የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ማንንም የማያገል ነው።አማራውን ያገላል የሚባለው አግባብ ያልሆነ ነው። በቅርቡ በቶሮንቶ፣በሎስ አንለስ፣በኖርዌይና ስዊዘርላንድ በጠራናቸው ስብሰባ ላይ ሁሉ ኢትዮጵያውያን በጋራ መጥተው በጋራ መምከር አለብን የሚቀርቡ ቅሬታዎችንም ያኔ ማንሳት ይቻላል።አገራዊ ንቅናቄው ግን ሁሉንም ድርጅቶች …> አቶ ዘውዴ ጉደታ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በቅርቡ ንቅናቄው ስለጠራቸው ስብሰባዎችና በንቅናቄው ላይ ስለሚቀርቡት ወቀሳዎች አንስተን ተወያይተናል(ቀሪውን ያዳምጡት)
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የታላቁ የሮመዳን ጾምን እንዴት እንደሚያከብሩት የውጭ አገር ዘጋቢዎች ቅኝት
አደንዝዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን እና ሙሰኞችን ከእነ ህይወታችው ከሂሊኮፕተር ላይ ለመጣል የዛቱት የፊሊፒኑ ፕ/ት ዶርተርቴ ያስነሱት ድጋፍ እና ተቃርኖ ሲዳሰስ(ልዪ ጥንቅር)
ሌሎችም አሉን
ዜናዎቻችን
በሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የጊዜ ገደቡ ከማለቁ በፊት አገራቸው ለመግባት በቆንስላዎቹ የአድልዎና የጎቦ አሰራር እየተጉላሉ መሆኑን ገለጹ
በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ወደ አስከፊ ደረጃ እንዳይሸጋገር ተሰግቷል
አርብቶ አደሮች በድርቁ ሳቢያ ያጧቸው ከብቶቻቸውን ለመተካት ከአስር ዓመታት በላይ ይፈጃል ተባለ
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ተሸለመ
የኢትዮጵያን መሬት በድብቅ ስምምነት ለሱዳን አሳልፎ መሰጠቱን የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ተቃወመ
፣አንድ የሱዳን ሀገረ ገዢ ኢትዬጵያ ሰሞኑን ኩርማን መሬት ቆርሳ ሰታናለች ማለታቸው ተቃውሞ አስነሳ
“በኢትዮጵያ የተነጠቅነው መሬትን ለማስመለስ አለማቀፋዊ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገናል“የሱዳን ገበሬዎች እሮሮ
ኢትዮጵያዊው ነጋዴን ደ/አፍሪካ ውስጥ አፍነው ተጨማሪ ገንዘብ ከቤተሰቡ ለማግኘት የጣሩ የተደራጁ ወረበላዎች በቁጥጥ ስር ዋሉ
ኤርትራ እና ግብጽ በኢትዮጵያ እና በሱዳን ላይ ያላቸው አቋማቸውን በተናጥል ገለጹ
“በእኛ ላይ የሚቀርበው ውንጀላ ከብልሹ ጭንቅላት የሚመነጭ ነው“ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጋዜጠኞች ከሰጡት የተወሰደ
“ግብጽ ጎረቤቶቿን በተመለከተ የነጠረ አቋም ነው የምትከተለው“የግብ ጹ ፕ/ት አልሲሲ
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ግፊት እንዲያደርግ በድጋሚ ተጠየቀ
መምህር ግርማ ወንድሙን በተለያዩ ርእሰ አድባራት አካባቢ እንዳይገኙ ያሳገዱትና በእስር ቤት እንዲማቅቁ ያደረጉት (ዶ/ር) አባ ሃይለማርያም ሰሞኑን ታላቅ ሃይማኖታው ተቃውሞ ገጠማቸው
በፌስ ቡክ አስተያየት በመስጠታቸው የአገዛዙ ፍርድ ቤት የቀጣቸው እነ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተቃውሞ ገጥሞታል
የተባበሩት አረብ ኤሜሬት ተዎጊ ጄቶቿን በቅርቡ ከጎረቤት የበርበራ ወደብ ስማያት ላይ እንደምታበር ባለስልጣኗ አረጋገጡ
“የኤሜሬት ተዋጊ አውሮፕላኖች ቀደም ብለው በአሰብ ወደብ ላይ ስራ ስለ ጀመሩ ለቀጠናው አያሰጋም“የሶማሌላንዱ የው ጭ ጉ/ሚሩ ሳይድ አሊ
ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።