በቅርቡ ከኤርትራ ለሕክምና የወጣው ታጋይ ዘመነ ካሴን ለመርዳት አስቀድሞ በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው አማካኝነት ተከፍቶ የነበረው የጎ ፈንድ ሚ ዕርዳታ ማሰባሰቢያ በአሁኑ ወቅት ተመልሶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ታውቋል።
ታጋይ ዘመነ ካሴን ለመርዳት የተጀመረው ጥረት በራሱ ፈቃድ መደረጉ ከተገለጸም በሁዋላ ለጥቂት ቀናት የ ጎ ፈንድ ሚ አካውንቱ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው አስቀድሞ እንደገለጸው ከድርጅቱ ጋር ተጻጽፈን ይከፈታል ባለው መሰረት ተከፍቶ ዕርዳታ ማሰባሰቡ ቀጥሏል።
ታጋይ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ በእነ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው አማካኝነት በአሜሪካ፣በስዊዘርላንድና በካናዳ የሚገኙ በስም የጠቀሳቸውና ስማቸውን ያልጠቀሰው ግለሰቦች በፋይናንስ ባደረጉለት ድጋፍ እና በኤርትራ መንግስት ለሕክምና መውጣቱን መግለጹ ይታወሳል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የዕርዳታ ማሰባሰቡን አካውንት ተከፍቶ መዘጋት እና ተከትሎ የመጡትን ክሶች በተመለከተ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው መግለጫ አካውንቱ እንዲከፈት እየተጻጻፈ መሆኑንና ይከፈታል ማለታቸውን አሰኢቀድሞ ገልጾ ነበር። ከመጀመሪያም ዘመነን ለመርዳት ሲነሳ ጀምሮ ይቀርቡ የነበሩ የተለያዩ ክሶችን ትኩረት ሰጥቶ መከታተል እንደማይገባ ገልጾ ታጋይ ዘመነ ካሴን በተቻለው ሁሉ መርዳት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
ለታጋይ ዘመነ ካሴ በጎ ፈንድ ሚ አካውንት የሚደረገው የዕርዳታ አሰባሰብ ላይ ለመሳተፍ በሚከተለው አድራሻ ሊንኩን በመጫን በቀጥታ መርዳት ይቻላል። ክፍያው በዩሮ ስለሚፈጸም ከአውሮፓ ውጭ ያሉ በጎ አድራጊዎች ባሉበት አገር የሚፈጽሙት ክፍያ በዩሮ ስሌት ስለሚቀመጥ በዩሮ በቀላሉ መለገስ ይችላሉ። ሊንኩን በመጠቀም መርዳት ይቻላል።