Hiber Radio: የሕወሃት -ኢህአዲግ አገዛዝ የመከላከያ ጦሩን ኤርትራን እና ጅቡቲን ወደ አወዛገበው ኮረብታ አጓጓዘ፣ፈረንሳይ ተዋጊ አውሮፕላኖቿን ለቅኝት አሰማርታለች፣ኢትዩጵያዊያን ሙስሊሞች የታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓልን በጸሎት እና በምስጋና አከበሩ፣በልማት ስም እንዲፈርስ ከተደረገው እውቁ የነጻነት ታጋይ የፕ/ር አስራት ወ/የስ መቃብር የወጣ አጽማቸው በክብር በስላሴ አረፈ፣በሳውዲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ወገኖቻቸው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቀ፣የእንግሊዟ ጠ/ሚ/ር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ ዳግም ተጠየቁ፣የኢትቪው ጋዜጠኛ ሙስናን በመዋጋ ቱ ባለስልጣኑ ሽጉጥ እንደመዘዙበት ገለጸ፣አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከለንደን ሻምፖዮና ቡድን አላግባብ መገለል ፣በአዲስ አበባ የጠፋው ኮንደሚኒየም በኢዲት ጉዳዩ እንዲጣራ ታዘዘ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሰኔ 18 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በአሰሪዎቼ ከሚደርስብኝ ስቃይ አንጻር ኤምባሲ ደውዬ ምን ላድርግ ስል ምንም ሳትይዢ እጅሽን ለፖሊስ ስጪ አሉኝ እጄን ለፖሊስ ሰጠሁ ።ድረሱልኝ ብዬ ይሄው አስር ወር ሙሉ ከእስር ቤት እጮሃለሁ ማንም ዞር ብሎ ያየኝ የለም…ለወገን ደራሽ ወገን ነው ስደት በእኛ ይብቃ ወገኖቼ ድረሱልኝ።የሚወራውና የሚሰራው የተለያየ ነው… > አበባ ስመኘው ከሳውዲ እስር ቤት ስላለችበት ሁኔታ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠችው ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…በሳውዲ ከወጣው ሰው ያልወጣው ይበልጣል።የምህረት አዋጁ አልቋል።በኣል ስለሆነም ሊሆን ይችላል ወታደሮች ሲያስሩም ሆነ ሲያሳድዱ አይታይም።ጊዜው እንዲራዘም በሌሎች አገራት ተጠይቋልም የሚል ጭምጭምታ አለ ሆኖም ነገ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን መገመት ይከብዳል ሆኖም በየቦታው ያሉ ኢትዮጵያውያን ትላንት እንዳደረጉት ለወገኖቻቸው ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባል…> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ በወቅታዊው የኢትዮጵአውያን ጉዳይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

<…የአገልግሎት ሰጪው ላይ የሚገኘው ሕዝብ የኢኮኖሚው ሁኔታ እየተቀዛቀዘ ይመስላል ።በዚህ ብዙ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ።የቤት ዕዳ የብድር ማስተካከያ የመጣው በኦባማ አይደለም። በኢኮኖሚው ምክንያት በሱ ጊዜ የበዛ ስለነበር እን የሞርጊጅ የብድር ማስተካከያ ሁል ጊዜም አለ የተወሰነ ፋታ ማግኘት ይቻላል…> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ጋር ካደረግነው ውይይት ተወሰደ (ቀሪውን አድምጡት)

በኤርትራ እና በጅቡቲ መካከል የተፈጠረው ሰሞነኛው ፍጥጫ እና በኢትዩጵያ ላይ የሚያስከትለው ስጋት ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

 ዜናዎቻችን

ኢህአዲግ የመከላከያ ጦሩን ኤርትራን እና ጅቡቲን ወደ አወዛገበው ኮረብታ አጓጓዘ፣ውጥረቱ ኢትዪጵያኖችን አስግቷል፣ፈረንሳይ ተዋጊ አውሮፕላኖቿን ለቅኝት አሰማርታለች

በርካታ ኢትዩጵያዊያን ሙስሊሞች የታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓልን በጸሎት እና በምስጋና አከበሩ፣የታላቁ የመካ መዲና መስጊድን በቦምብ ለማጋየት የወጠነ አሸባሪ የገዛ እራሱ ህይወትን ቀጠፈ

የኢትቪው ጋዜጠኛ ሙስናን በመዋጋ ቱ ባለስልጣኑ ሽጉጥ እንደመዘዙበት ገለጸ

“ጭንቅላቴ ላይ ሽጉጥ ደግነው አርፈህ ካልተቀመጥክ እገልሃለሁ አሉኝ”ስደተኛውጋዜጠኛ ሱራፌል አሰፋ ለደ/ኮሪያ ሚዲያዎች ከስጠው እማኝነት የተወሰደ

በኢትዪጵያ ውስጥ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ ያፈሰሱት አፍሪካዊው ቱጀር ፋብሪካቸውን እንደሚዘጉ አስጠነቀቁ

“ባለሃብት ሊመጣ ይችላል፣ጓዙንም ጠቅልሎ ሊሄድ ይችላል”የኦሮሚያው ሹም ለባለሀብቱ አቤቱታ የሰጡት ምላሽ

የእንግሊዟ ጠ/ሚ/ር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ ዳግም ተጠየቁ

“ለልጆቼ አባታቸው ለምን ወደ ቤቱ መመለስ እንዳልቻለ ማሳመን ይከብደኛል”የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ምሬት እና ቁጭት አዘል ደብዳቤ በከፊል

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *