የህብር ሬዲዮ ሰኔ 25 ቀን 2009 ፕሮግራም
<…ሕወሃት አስቀድሞ በማስተር ፕላኑ ማስፋፊያ ስም ኦሮሞን መሬት ለመዝረፍ ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው አንዱን ከአንዱ ለማጋቸት ሆን ብሎ ያቀደበት የኦሮሞ ልዩ ጥቅም ተከበረ አስመስሎ ያጭበረበረበት እንጂ በአዋጁ የኦሮሞም ሆነ የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥቅም አልተከበረም…አፋን ኦሮሞ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከአማርና ጋር ስራ ቋንቋ እንዳይሆን የሚቃወመው ሕወሓት ብቻ ነው ይሄ በአዲስ አበባ በኦሮሚና መማር በሕገ መንግስት ለዜጎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ የተፈቀደ መብትን ልዩ አስመስሎ ማቅረብ ማጭበርበሪያ ነው…> አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲአ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ስለ አዲሱ አዋጅ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን አድምጡት)
<…የዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን 34ተኛው የሲያትል መክፈቻ ከወትሮው በመክፈቻ ካየሁዋቸው ደማቅ ነው።ኢትዮጵአውያን በአገራቸው ባንዲራ ደምቀው በጋራ ኢትዮጵያ እያሉ ሲዘፍኑ ማየት አስደስታል። በፌዴሬሽኑ በኩሉ ዘንድሮም የሚስተዋሉት በተለይ መግቢያው ጉዳይ ግን…>
ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ ከሲያትል የመክፈቻ ስነ ስርዓቱን በተመለከተ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
ሕወሓት አንዱን በአንዱ ላይ ለማነሳሳት እየሞከረበት ያለው የአዲስ አበባ የሰሞኑ አጀንዳ እውነት እንደሚባለው ለኦሮሞ የተለየ ጥቅም ተከብሮለታል ወይስ የለመዱትን የመሬት ዘረፋ ተግባራዊ ለማድረግ የተወጠነ ሴራ ? ለሁሉም ሙሉ የሕግ ረቂቁን በድምጽ አዘጋጅተነዋል አድምጡት
የቀድሞው የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤቶች ፕ/ት አቶ ክቡር ገና ኢህአዲግ የመዲናይቲን ነዋሪዎችን ለማፋጀት ያውጣው ሰሞነኛው ረቂቅ አዋጅን በመቃወም ለነዋሪው ህዝብ እና ለአገዛዙ ያቀረቡት ጥሪ በከፊል ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)
<…ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ዛሬ በዓለም ላይ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎችን ስጋት ላይ የጣለው የመኪና ለአደጋ የሚያጋልጥ የኤር ባግ ጉዳይ በአሜሪካ ብዙው ተሽከርካሪዎች ስለሚገኙ ደውለን የምናሽከረክረው መኪና ኤር ባግ ችግር አለባቸው ከተባለው መሆን አለመሆኑን ማጣራት አለብን…> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ታካታ የተሰነውና ለሆንዳና ለቶዮታ ጨምሮ ለበርካታ ተሽከርካሪዎች ኤር ባግ አምራች የደህነት ስጋት ስለሆነው ምርቱና ስላስከተለው አደጋ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ቀሪውን አዳምጡት)
በኢትዩጵያ እና በህዝቧ ፍቅር የተለከፈው እውቁ የአለማችን ፎቶግራፈር ዛሬም ስለ ኢትዬጵያኖች ማንነት ይሰብካል(ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የተባለው አዋጅ ሕወሃት ህዝብን ከሕዝብ አጋጭቶ መሬት ለመዝረፍ ያቀደውን የማስተር ፕላን ማስፋፊያ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገለጸ
ኢትዬጵያ እና ህዝቧ በሕወሓት/ኢህአዲግ የጭቆና በትር ሲቀጠቀጡ ምእራባዊያኖች ችላ ማለታቸው አሳፋሪ ነው ተባለ
“ምእራባዊያኖች ከዘለቄታ ወዳጅነት ይልቅ ጊዜያዊ ጥቅም ላይ ያተኩራሉ”የኦክላንድ ጥናት ማእከል ሰሞነኛው አቤቱታ
የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ኢትዮጵያውያን ሊከፋፍላቸው ባቀደው ሼህ አላሙዲን ላይ ድል በመቀዳጀታቸው አመሰገነ
በኢትዩጵያ ውስጥ ያለው የቡና ማሳ በግማሽ ሊሟጠጥ እንደሚችል ሳይንስሲስቶች አስጠነቀቁ
ከቤንሻንጉል ከአራት ኣመት በፊት የተፈናቀሉ የአማራ ገበሬዎችን ጨምሮ በባህር ዳርና በጎንደር አመጽ አስነሱ በሚል በሀሰተኛ የሽብር ክስ ተከሰሱ
ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞ ፈርንሳይ ውስጥ የተካረረ የቡድን ግጭት አደረጉ
በርካቶች ቆስለዋል፣ታስረዋል ተብሏል
“አካባቢው ላለፉት አስራ ሁለት ሰዓታት ውጥረት እና ሁካታ ነግሶበት ነበር”የካሊስ ከተማ ም/ል ከንቲባው ፊሊፕ ማግቦት ለዜና ሰዎች ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ
በሰሜን ጎንደር በዳባት ወጣቶችን ከሚአሳፍነውና ከሚያስገድለው የቀድሞ የሀሰት አርበኛ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅ ጥሪ ቀረበ
መሳሪያ አስገብሩ በሚል አዲስ የመሳሪአ ገፈፋ እቅድ ተጀመረ
ኢትዩጵያዊው ባለሀብት የህዋት ባለስልጣናት ሕዝቤን እንዳልረዳ እንቅፋት ሆኑብኝ ይላሉ
“ከዚህ የከፋ የመንግስት ሽፍትነት ይኖራል ብዬ አላምንም፣በእድሜዬ ኢትዮጵያ በጎጥ የተከፋፈለችው በዚህ ዘመን ብቻ ነው።”ትውልደ ትግራዩ ባለሀብት አቶ ዳዊት ገ/እግዚአብሔር በአገዛዙ ላይ ያደረባቸውን ቅሬታን ልብን በሚነካ መልኩ ሰሞኑን እንደገለጹት
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጨምሮ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችና የህሊና እስረኞች በማህበራዊ ሚዲያው በዘመቻ ታሰቡ
በስደት ላይ የምትገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከገበያ ላይ ጠፍቶ የነበረው 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስን ለምእመናኑ ልታዳርስ ነው፣አሜሪካ ውስጥ 10ቱ ትእዛዛት የተጻፉበት ሃውልትን ያፈረስ ግለሰብ ተያዘ
እና ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።