Hiber Radio: ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ አማራጭ መንግስት ተባብረው እንዲመሰርቱ አቶ ሌንጮ ለታ ጥሪ አቀረቡ፣ፋሺስት ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ላደረሰው የመርዝ ጋዝ ጭፍጨፋ የእንግሊዞች ድጋፍ እንደነበረው ተጋለጠ፣በአማራ ስም ትግራይ በሽማግሌ ስም ከሔዱት ብዙዎቹ ሕዝቡን ሲያስገድሉና ሲገሉ የነበሩ መሆናቸው ተገለጸ፣አንድ ምእራባዊያን አገር ጎብኚ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባለቤታቸው ፊት በዝሆን ተጨፍልቀው ሞቱ፣በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዛሬም አሳሳቢ ነው የምህረት አዋጁ ዳግም እንዲራዘም ተጠየቀ፣ከቁርጥ ግብር ጋር የተነሣው ተቃውሞ ብሔራዊ አቅጣጫ ሊይዝ እንደሚችል ባለስልጣናቱ ስጋታቸውን ገለጹ አገዛዙ ሽንፈት ደርሶበታል ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 16 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም። በአስቸኳይ ከኢህአዴግ ተቃራኒ የሆነ ሀይል መፍጠር አለብን። እነሱ ስልጣን ላይ ሲወጡ ሁለት ስትራቴጂ ነድፈው ነው። ከቻሉ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻሉ እስር በእርስ አጋጭተው አገሪቱን በትነው ወደ መጡበት መሄድ ነው። በአስቸኳይ አማራውም ሌላውም ብሄር የተወከለበት …ሁል ጊዜ ከወያኔ የሚመጣ ነገር መጠራጠር አለብን። እነሱ በሚሰጡን አጀንዳ መነታረክ የለብንም የአዲስ አበባም ጉዳይ ቢሆን እነሱ አማራና ኦሮሞውን ለማጣላት ያመጡት ነው። ያ ባይሆን እና የተሻለ ነገር ቢያስቡ ኖሮ ከተማዋን …> አቶ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኦዴግ) ሊቀመንበርና የኢትዮጵአ አገራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራር ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያድምጡት)

<…እነሱም በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለውን ወንጀል በሰሞኑ በሽማግሌ ስም በሚሰሩት ማጭበርበሪያ የሚወጡት አለመሆኑን ያውቃሉ። ሌላው ቀርቶ በህወሓት ፕሮግራም ላይ ያሰፈሩት ጸረ አማራ አቋማቸው መቼ ተቀየረ? የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በየትኛውም ቦታ በሕግ ፊት ወደፊት ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ነው…ዋናው ነገር ለውጥ ፈላጊው ሀይል በልዩ ልዩ ምክንያት መከፋፈሉን ማቆም አለበት።በሚያግባባው ጉዳይ አንድ ላይ መቆም አለመቻሉ ነው ለእነሱ ዕድል የሰጣቸው…> ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ኢንዲኮት ኮሌጅ የሰብዓዊ መብትና የዓለም አቀፍ ሕግ መምህር በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

<…የሳውዲ የምህረት አዋጅ የአንድ ወር ማራዘሚያ ሊያበቃ ጥቂት ቀናት ቀረው። ዛሬም በመንግስት መረጃ መሰረት እንኳን ከ34ኦ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በሕገወጥነት ሳውዶ ውስጥ አሉ። መውጣት እየፈለጉ ያልወጡ ዜጎች አሉ፤የተጓተተ አሰራር ነበር የትኬት ውድነትም ሌላው ተጠቃሽ ምክንያት ነው…መንግስት ሕገወጥ ስደተኞች በተሰጠው ቀነ ገደብ ካልወጡ አስራለሁ በገንዘብ እቀጣለሁ ብሏል። ሰሞኑን የሚታይ ግር ግር ባይኖርም ግን ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይቻልም…> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በሳውዲ ስላሉ ዜጎች ወቅታዊ ሁኔታ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያድምጡት)

በኢትዮጵያ ውስጥ ጅቦች እንኳን ከሰዎች ጋር ሲፋቀሩ ባለስልጣናቱ ግን ከሕዝቡ ጋር ሆድና ጀርባ ለምን ሆኑ?(ልዩ ጥንቅር)

የአጼ ሀይለስላሴ125ተኛ ዓመት የልደት በኣል ሲታወስ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

 አቶ ሌንጮ ለታ ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ አማራጭ መንግስት ተባብረው እንዲመሰርቱ ጥሪ አቀረቡ

ፋሺስት ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ላደረሰው የመርዝ ጋዝ ጭፍጨፋ የእንግሊዞች ድጋፍ እንደ ነበረው ተጋለጠ

የጣሊያን ልጆች ቅድም አያቶቻቸው በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት በደል አይማሩም ተባለ

በአማራ ስም ትግራይ በሽማግሌ ስም ከሔዱት ብዙዎቹ ሕዝቡን ሲአስገድሉና ሲገሉ የነበሩ መሆናቸው ተገለጸ

ስብሃት ነጋ በብአዴን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀ

በኢትዩጵያ እና ኤርትራ የጋራ ድንበር ላይ ሰሞኑን የከባድ መሳሪያዎች ልውውጥ መደረጉ ተዘገበ

አፍቃሪ ኢህአዲግ ድህረገጾች ስለግጭቱ ሲዘግቡ የአስመራ እና የአ/አ ገዢዎች ግን ዝምታን መርጠዋል

የአዲስ አበባን መሬት የቸበቸቡ የሕወሓት ነጋዴዎች የደብረ ብርሃንን ከተማ መሬት መቀራመት መጀመራቸው ተገለጸ

አንድ ምእራባዊያን አገር ጎብኚ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባለቤታቸው ፊት በዝሆን ተጨፍልቀው ሞቱ

በሳውዲ የሚገኙ በመቶ ሺህ ሚቆጠሩ ኢትዮጵአውያን ጉዳይ ዛሬም አሳሳቢ ነው

የምህረት አዋጁ ዳግም እንዲራዘም ተጠየቀ

ለአስር አመታት በቁም እስረኝነት የከረሙት የቀድሞው የኢርትራ። ፓትሪያርክ ሰሞኑን ከምእመናኖች ጋር መገናኘታቸው አነጋገረ

ቻይና በአወዛጋቢው የኤርትራ እና የጅቡቲ ድንበር ላይ ጦሯን ልታስማራ ነው

የኢህአዲግ መንግስት በርካታ ሶማሌዎችን ለሞቋደሾ ባለስልጣናት አሳልፎ ሰጠ

በጉልበት ግብር እሰበስባለሁ ያለው አገዛዝ የነጋዴዎችን አድማ ተከትሎ አነስተና ነጋዴዎች ያመኑትን ይክፈሉ አለ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከቁርጥ ግብር ጋር የተነሣው ተቃውሞ ብሔራዊ አቅጣጫ ሊይዝ እንደሚችል ባለስልጣናቱ ስጋታቸውን ገለጹ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *