የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 23 ቀን 2009 ፕሮግራም
<…በሕወሃት ሙስና ወንጀል አይደለም። በጋራ ዘርፈው የኢኮኖሚ የበላይነት ለማግኘት ወስነው ነው ሲዘርፉ የኖሩት።የሰሞኑ የይስሙላ የሙስና ዘመቻ ዋናዎቹን ሙሰኞች የሕወሓት ባለስልጣናት፣ጄኔራሎች ፣የእነሱን ኢንቨስተሮች አይነካም …በአዲስ አበባና በናዝሬት ሐሰተኛ የብር ኖቶች የሚያትሙና የሚያከፋፍሉ ሁለት የትግራይተወላጆችን እኔና አንድ ሌላ የደህነት አባል ስንደርስባቸው በቃ ምርመረራን አቁሙ ጥቆማው ጥሪ ነው ነው የተባልነው። እነዛ ሰዎች ማንም ዞር ብሎ ያያቸው የለም። ከብሔራዊ ባንክ ወርቁን በመዳብ በቀየሩበትም ሒደት…> አቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የደህነት መ/ቤት ሹም ስለሰሞኑ የሕወሓት/ኢህአዴግ ሙስና ዘመቻ በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያድምጡት)
<…የኬኒያ ምርጫ ላይ የተቃዋሚው መሪ በምርጫ ምዝገባ ወቅት ኢትዮጵያውያን እና ዩጋንዳውያን ለምርጫ ተመዘግበዋል ብለው ወንጅለዋል..ምርጫውን ተከትሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስጋት አለን…> ጋዜጠኛ ታዲዮስ ጌታሁን የቀድሞ የሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር በኬኒያ በቅርቡ ስለሚደረገው ምርቻን ተከትሎ ስላለባቸው ስጋት ከሰጠን ማብራሪያ(ቀሪውን ያድምጡት)
<…በኬኒያ ያለው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ስደተናው ምርጫውን ተከትሎ ላለበት ስጋት ሀላፊነት መውሰድ አልፈለገም። ፖሊሶች በፊትም ስደተኛ እአስቆሙ ገንዘብ መቀበል የተለመደ ነው…በኬኒያ ላሉ ወገኖቻችን ምርቻውን ተከትሎ ችግር እንዳይደርስባቸው በጋራ ጥሪ ማድረግ አለብን የማህበራዊ ሚዲያም ዘመቻ ለመጀመር አስበናል..> ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው የቀድሞ የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በኬኒያ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ከሰጠን ማብራሪአ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)
<…በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ የጸደቀው ኤች አር 128 በኮንግረሱ እንዲጸድቅ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት የሚያሳስበን ወገኖች አሁን የበለጠ ሰፊ ጥረት ማድረግና በየአካባቢያችን ለሉ የኮንግረስ አባላት ማሳሰብ አለብን።ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል ። የወያኔ ባለስልታናት እነሱ ሕጉ እንዳይጸድቅ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው…> አቶ ተመስገን መንግስቱ የአማራ ማህበር በአሜሪካ ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጠን ማብራሪአ ተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያንጃበበው ርሃብ እና ድርቅ የአለማቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ ሲገመገም(ልዩ ጥንቅር)
ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ቀሪ ክፍል
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ስብሃት ነጋን ጨምሮ የሕወሓት ባለስልጣናት ሙስና ያጋለጡ ዜጎችን ያስገድሉ እንደነበር የደህነት ሹሙ ገለጹ
ከኦነጉ መሪ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር “ግንኙንት አለህ”ተብሎ እስራት እና ድብደባ የደረሰበት ወጣት አስክሬን ከአ/አ ተወስዶ ወለጋ ውስጥ ተቀበረ
“የሟቹ ጓደኛዩ አየለ በየነ እጣ እንዳይደርስኝ እስጋለሁ”የቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ታሳሪው ሰሞነኛው ለፍርድ ቤት በእንባ የታጀበ ተማጽኖ የተወሰደ
በአማራ ሕዝብ ስም ትግራይ የሄዱ የሕወሓት ሽማግሌዎች አንዳንዶቹ ጥቃት እንዳይደርስባቸው መመሪያ መሰጠቱ ተገለጸ
ሰሞኑን በጉጂ እና በኮሬ ጎሳዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ዜጎች ህይወትን ቀጠፈ
አገዛዙ ከግጭቱ ጀርባ አሉ ያላቸውን ማሰሩን ይናገራል
የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ 81ኛ ዓመት መታሰቢያ እንዳይዘከር በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ አገደ
በኢትዮጵያውያን ወላጅ አልባ ህጻናት ሁናቴ ልባቸው የተነካ ሁለት ምእራባዊያን ጥንዶች ጓዛቸውን ጠቅልለው ኢትዮጵያ ውስጥ ገቡ
የሰማያዊ ፓርቲ በሙስና የበሰበሰ አገዛዝ ሙስናን ሊታገል አይችልም አለ
በአገር ውስጥ ተቃውሞ የደረሰበት የሕወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ ከጓረቤት አገሮች ጋር ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረመ
የደ/ሱዳን ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ገዢ መሬትን ያዙ
የአቶ አባይ ጸሔን ሚስትጨምሮ በሙስና የተከሰሱት ላይ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠየቆ ተፈቀደለት
የዙምባብዌው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ”ስልጣኔን በቀላሉ አልለቅም፣አልሞትም”ሲሉ ተቺዎቻቸውን አሳፈሩ
ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ድል ተቀዳጀ
አሰልጣኙን ደብድቦ የተሰወረው ኢትዮጵያዊው አትሌት የአለም መገናኛ ብዙሃንትን ትኩረት ሳበ፣አትሌቱ በፓሊስ እየታደነ ይገኛል
እና ሌሎችም
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።