Hiber Radio: የሕዝቡ ተቃውሞ ሱናሚ ሆኖ የሕወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ ሊያስወግድ መቃረብ ፣የአሜሪካና ካናዳ በኢትዮጵያ ላይ ያወጡት ማስጠንቀቂያ፣የቴዲ አፍሮ አልበም ምርቃት መራዘም፣በሙገር ሲሚኒቶ ላይ ያንዣበበ አደጋ፣ጣሊያን በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ በወሰደችው እርምጃ መወገዟ፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንዳታባርር ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም መጠየቁ ፣የእነ ጄኔራል ክንፈ ዘረፋና የዓለም ባንክ ብድር እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 21 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በእነሱ ቴሌቪዥን ላይ የቀረበው የታላቋ ትግራይ ካርታ በኢንተርኔት ተገኝቶ በስህተት የቀረበ ሳይሆን የትግራዩ ነጻ አውጭ በ1967 በረሃ እያለ ወልቃይት ጠገዴን ጠለምትን ጭምር ወደ ትግራይ አካሎ የሳለውና እሱን ተግባራዊ ሊያደርጉ ይቃወመናል ያሉትን ወልቃይትን ዘር እያጠፉ መጥተዋል። ዛሬም ዓላማቸውን ተግባራዊ ሊያደርጉ እየሰሩ ነው…የእነሱ የቀረውን ሕዝብ እርስ በእርስ አጋጭተው የቃዡላትን ታላቋን ትግራይ የሚመሰርቱት ተቃዋሚው ባለመተባበር አንድ ላይ ባለመቆም በሰጣቸው እድል ካልሆነ በቀር እነዚህማ..> አቶ ቻላቸው አባይበሰሜን አሜሪካ የወልቃይት፣ጠገዴ፣ ጠለምት ልሳነ ግፉአን ኮሚቴ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ያደረጉት አጠር ያለ ቃለ ምልልስ(ቀሪውን አዳምጡት)

<…ይሄ ትግል የህዝብ ትግል ነው ወያኔ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ ትቶ ጃዋር ጃዋር የሚለው ሆን ብሎ ጥያቄውን ለማዳፈን ነው። ጃዋር የትግሉ ደጋፊ እንጂ ጥአቄው የሕዝቡ መሪውም ሕዝቤ ነው፤የተጠራው ተቃውሞ የመገንጠል ጥያቄ አይደለም። ሰሞኑን የተደረገው ተቃውሞ በተመሳሳይ ሆነ በሌላ መልኩ  ወደፊትም የህዝቡ ጥያቄ እስኪመለስ ሚቀጥል ይሆናል ። ተቃዋሚው ግን …> አቶ ነጌሳ ኦዶ ዱቤ የኦፌኮ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን ሊቀመንበር በወቅቱ ኦሮሚያ ተቃውሞና ተቃውሞውን ተከትሎ ስለነበሩት ሁኔታዎች ተጠይቀው ከሰጡን ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ሰሞነኛው  የአሜሪካ እና የግብጽ መንግስታት ወታደራዊ ተቃርኖ ሲቃኝ(ልዩ ዘገባ) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሕዝቡ ተቃውሞ ሱናሚ ሆኖ የሕወሃት/ኢህአዴግን አገዛዝ ሊያስወግድ ተቃርቧል ተቃዋሚዎች ይተባበሩ ተባለ

አሜሪካ እና ካናዳ ዜጒቻቸው ወደ ኢትዩጵያ ከመጓዛቸው በፊት እንዲያጤኑ አስጠነቀቁ፣ጅማ የእጅ ቦንብ ፍንዳታ አስተናገደች

በካናዳ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሶስት ታዳጊዎች ስርዓተ ቀብር ብዙ ሺህ ሕዝብ በተገኘበት በሲያትል ተፈጸመ

በቀብሩ ላይ ሁለት ጳጳሳት ተገኝተዋል

አንጋፋው የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የመዘጋት አደጋ አንጃብቦበታል ተባለ

በቴሌቪዝን ይፋ የሆነው የታላቋ ትግራይ ካርታ ተግባራዊነት  በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ዘር ማጥፋት እስካልቆመ መዘናጋት እንደማይገባ ተገለጸ

ጣሊያን ሰሞኑን  በዜጎቻችን ላይ የፈጸመችው ግፍ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ገጠመው

“ስደተኞች ማለት አሸባሪዎች ናቸው ማለት አይደሉም”ሮማ ላይ ለተቃውሞ የወጡ ካነገቡት መፈክር የተወሰደ

የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ አልበም ምርቃት ተራዘመ

ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን እንዳታባርር ተጠየቀች

ኩዌት ውስጥ ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ተጥላ የተረፈች ኢትዬጵያዊት ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቀለች

ሕወሃት በእሬቻ ላይ ለጨፈጨፋቸው ንጹሃን ሞት ራሱን ከተጠያቂነት ነጻ ያደረገበት ሐውልት በኦሮሞ ዋቄፈና ተቃውሞ ቀረበበት

የሜቴኩ ጄኔራል ክንፈና ሕወሃት አጋሮቻቸው አገሪቱን እአራቆቱ ማይነሱ ሆነው ቀጥለዋል ተባለ

የዓለም ባንክ ሙስና ለተነሰራፋባት ኢትዮጵያ ብድር መፍቀዱ ትርታሬ ፈጥራል

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *