Hiber Radio: አቶ ምሕረት ዓለሙን ለመርዳት ጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፈተ፣ ለዚህ በጎ ሰው የበኩላችንን አስተዋጽዎ እናድርግ

በላስ ቬጋስ ለረጅም ጊዜ ነዋሪነቱና በጎ አድራጊነቱ የሚጣወቀው ብዙዎች በፎቶ ግራፍ ባለሙአነቱ ችምር የሚአውቁት አቶ ምሕረት ዓለሙ ከዚህ ቀደም በደረሰበት የመኪና አደጋ ሳቢያ ለዓመታት ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ  በደረሰበት ከፍተኛ የጀርባ አጥንት መጎዳት ምክንያት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት እንደቀድሞ በእግሮቹ ያለ ክራንች የማይራመድ ሲሆን እሱን ለመርዳት በስሙ ጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፍቶ ለሁሉም ወገኖች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ብዙዎቻችን እንደምናውቀው በዚህ በላስ ቬጋስ ነዋሪ የሆነው ወንድማችን አቶ  ምኅረት ዓለሙ ለማያውቃቸው ሰዎች ሁሉ እጅግ የሚያስገርም በጎ ምግባራትን ሲሰራ የኖረ ነው። ለአብነት ያክልም የማያውቃቸውንና ከ 13 ቤተሰቦች በላይ የሆኑ ሰዎችን ከተለያዩ ሃገራት አጠቃላይ ወጪያቸውን በመሸፈን ሙሉ እስፖንሰር  በመሆን  ከማስመጣት አልፎ ባለ ሁለትና ሦስት ክፍል አፓርትመንት በመከራየት፤ የሚያስፈለጋቸውንም ወጪ ሁሉ በራሱ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እየሸፈነ  እራሳቸውን እንዲችሉ የረዳቸው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ይገኛሉ። አንዳንድ ሰዎች  ሆስፒታል ተኝተው ደም ሲያስፈልጋቸው ባያውቃቸውም ደሙን በነጻ ለግሷል። አንዲት የልጆች እናት እህታችን ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት ባቆሙበት ጊዜ በአካል ሳያውቃት አንድ ኩላሊቱን ለመስጠት አጠገቧ ተገኝቷል። ሰውን ለመርዳት ገንዘብ ባጠረው ጊዜ እንኳ መኪናውን እስከ መስጠት ደየደረሰው አቶ ምህረት ባለው የቪዲዮና የፎቶ ግራፍ ሙያ ያላገለገለው ግለሰብና ማኅበረሰብ የለም። በአገር ቤትም በርካታ ወላጅ አልባ ህጻናትንና እንዲሁም ጧሪና ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያን ለበርካታ ዓመታት ሲረዳና ሲደጉም የኖረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በደረሰበት የጤና ዕክል ሳቢአ ከፍተና ችግር ውስጥበቀላሉ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዎ ማድረግ እንዲችል የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፍቷል።

ዛሬ ላይ ግን ወንድማችን ምኅረት  በደረሰበት ከፍተኛ የጀርባ አጥንት መጎዳት ምክንያት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል።እነዚህ ለጋሽ እጆች አጥረውት ለራሱ መሆን ተስኖታል። እነዚያ ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይመርጡና ሳይሰለቹ ሰውን ሁሉ ለመርዳት የሚሮጡ እግሮቹ ዛሬ መንቀሳቀስ ተስኗቸዋል።አልጋው ላይ እንኳን መገላበጥ ተስኖታል። ስለዚህ በአካል ተገኝታችሁ መርዳት ያልቻላችሁ ሁሉ በዚሁ ድህረ ገጽ ላይ ይህንን ወንድማችንን ትረዱት ዘንድ መልዕክቱንም ታስተላልፉልን ዘንድ በአክብሮት የተጠየቀ ሲሆን በቀጣዩ የ ጎ ፈንድ ሚ ሊንክ በመጫን በቀላል ዘዴ መደገፍ ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ  በ 702-622-0265 ,  ይደውሉ።

የጎ ፈንድ ሚ ሊንክ https://www.gofundme.com/chsv8-volunteer-trip

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *