Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ… አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ… የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ… እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ መጋቢት 28 ቀን 2007 ፕሮግራም
< ...የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ስልጣኑን በምርጫ ላሸነፈው ለተቃዋሚው ያስረከበው ተመራጩ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቡሪ በሰራዊቱ ውስጥ ድጋፍ ስላለው ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ፈርቶ ሊሆን ይችላል…. ብዙዎች የማይረዱት…..>ዶ/ር መራራ ጉዲና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ስለ ናይጀሪያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጠይቀናቸው ከሰጡን ማብራሪያ
<...በናይጀሪያ ሰራዊቱ እንደኢትዮጵያ በአንድ ጎሳ የበላይነት የተዋቀረ አይደለም። በኢትዮጵያ በናይጀሪያ የታየው ምርጫ እንዲመጣ ብዙ ትግል ያስፈልጋል….በኢትዮጵያ የህዝቡን ድምፅ የሚያስከብሩ ነፃ ተቋማት የሉም...>አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊና ለፓርቲው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እጩ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<...በሳውዲአረቢያ በወገኖቻችን ችግር በደረሰ ወቅት በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ተባብሮ በአንድ ላይ ድምጹን በማሰማቱ ውጤት ማምጣት ተችሏል። ዛሬም በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን የሚያስፈልገው በአንድ ተሰባስቦ ድምፃችንን ማሰማት እንጂ...>ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ ጅዳ
በኬኒያ የደረሰው የአልሸባብ የሽብር ጥቃት (ልዩ ዘገባ)
ባሻ ይገዙ (ልዩ ግጥም)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በጣሊያን የፋሽስት የግራዚያኒ ስም እንዲሰረዝ ታዘዘ
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ
የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ
አንድ አሜሪካዊ የመን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መገደሉ ታወቀ፣
በኬኒያ ዩኒቨርስቲ በተፈፀመው ጥቃት ላይ አንድ የአካባቢው የአገሪቱ ባለስልጣን ወንድ ልጅ ከአልሸባብ ጎን መሰለፉ ታወቀ
አረብ ኢሚሬትና እስራኤል ከአወዛጋቢው የኢትዮጵያው ህዳሴ ግድብ ጀርባ እጃቸው አለበት ሲል አንድ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገበ
እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን
ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም ብሏል
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ
ከአገር እንዳይወጡ የታገዱት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዋሽንግተንና ቦስተን ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት ንግግር አደረጉ
“ገዢዎቻችን ትግሉን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት መሰናክል ሁሉ ይበልጡን ያጠናክረናል” ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-040515_041215

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *