የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ዛሬ የተነጠቁትን ፓስፖርት መመለሱ ታወቀ-ከአገር እንዲወጡ ይፈቀድ አይፈቀድ አልታወቀም

Yilkal  2የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ባለፈው ሳምንት ፓስፖርታቸው ተነጥቆ ከቦሌ ከአገር እንዳይወጡ የተመሰለሱ ቢሆንም ዛሬ በአገዛዙ የደህንነት ባለስልጣናት ፈቃድ ኢሚግሬሽን ተጠርተው ፓስፖርታቸው እንደተሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለምን ፓስፖርታቸው እንደተነጠቀ ምክንያቱን ጠይቀው እንዳልተገለጸላቸው እና ከዚያ ቀደም ብለው በተደጋጋሚ ለጠየቁትም ምላሽ አልተሰጣቸውም።
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ከዚህ ቀደም ከአገር ሊወጡ ሲሉ የፓስፖርታቸው ገጽ ተቀዶ ተመለሱ መሆኑ ይታወሳል። ከሰሞኑ ከአገር እንዳይወጡ ከተከለከሉ በሁዋላ ዛሬ ፓስፖርታቸው ተጠርተው ቢሰጣቸውም ከአገር እንዲወጡ ይፈቀድ አይፈቀድ የሚታወቅ ነገር የለም።
የሰሜን አሜሪካ የሰማያዊና የእውነተኛው የአንድነት ፓርቲ የድጋፍ ኮሚቴዎች በጋራ ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከኢትዮጵያውያን ጋር ለመነጋገር የነበራቸው ቀጠሮ ቢስተጓጎልም ባለፈው ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ እና እሁድ በቦስተን ለተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን ከአገር ቤት በስካይፒ ንግግር ማድረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

 

(ህብር ሬዲዮን ዘወትር በህብርና በዘሐበሻ ድህረ ገጽ በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 7124328451 ደውለው 2 ይጫኑ ይደውሉ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *