Hiber Radio: በውጭ የሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በወገኖቻችን ላይ እየተደረገ ያለውን የማያቋርጥ መከራ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ – “መቆሚያ ያጣው የዋይታ ጉዞ” | ያንብቡት

አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

“ አግሬ እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፈሳሉ። ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ የከሱ አሉ፤ (ትን. ኤርምያስ 14፥17-18)

በወገኖቻችን ላይ እየተደረገ ያለውን የማያቋርጥ መከራ አስመልክቶ ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ።

በመከራ ዘመን የነበረው ነቢዩ ኤርምያስ በሕዝቡ ላይ ያለውን መከራ የገለጠው ከላይ የተመለክትነውን ክፍል እያነበበ በመጮኽ ነው። ይህ የምንባብ ክፍል ዛሬም ቤተ ክርስቲያን በወገኖቿ ላይ የሜፈጸመው ግፍ በማየት በተመሳሳይ መልኩ እያነባች ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ወገኖቻችን እየገደለ በማያቋርጥ ሐዘን ውስጥ እንድንኖር ያደረገን ሥርአት መቼ እንደሚቆም የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። በትምህርት ቦታ ልቅሶ፣ዋይታና ግድያ በእስፖርት ቦታ ፍጅትና እልቂት በአምልኮ ቦታ አልሞ በሚፈጅ የጦር ማሳሪያ ማገዶ ለሆነው ሕዝባቸን ክዚህ ሌላ ምን ቃል ልናገኝ እንችላለን?

በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደው ግድያ፣ አፈናና እሥራት እያሳዘነን እያለ አሁን አሁን ደግሞ በወልዲያ ከተማ በሥርአተ አምልኮ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ላይ የተፈጸመው እልቂት ልባችን ስብሮቷል ሐዘናችንም በቀላሉ የማይጠገን የልብ ስብራት ሆኖብኗል።

ከዚህም ጋር ከቤቱ የተቀመጠውንም እስራት ከዚያምን የተረፈውን ስደትና እንግልት ከዚያ የተረፈውን ርሐብ በጠቅላላ ኖሮው የቁም ሲኦል የሆነበት ሕዝባችን ምን ዓይንት ቃል ብንጠቀም የሐዘናቸንን ክብደት ሊገለጥልን ይችላል? ቤተክርስቲያን በስደት ሆና ይህ የመከራ ኑሮ ከወገኖቻችን የዕለት ከዕለት ጉዞ እንዲያበቃ ጩኸቷን ከመሰማት ያቋረጠችበት ጊዜ የለም።

ቤተክርስቲያን ይህ ክፉን ቀን ማለፍ የሚቻለው በሁለት መንገደ ብቻ ነው ብላ ታምናለች የመጀመሪያው በአማራጭ ኃይል በኩል የቆሙ ወገኖች የልዩነት ፖለቲካውቸውን አቁመው ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ዘመን ተሻጋሪ ራእይ ያለው ሥራ ሲሠሩ፤ እንደዚሁም ምሁራን ልዩነትን ከማራገብ ተቆጥበው ተጨባጭ የመፍትሔ ሐሳብ ሲያቀርቡና ለዚያም ተፈጻሜነት ተግተው ሲሠሩ ብቻ ነው።

ሁለተኛው በምደሪቱ የሚኖረው ሁሉም ወገናችን በጸሎትና በይቅርታ ልብ ሆኖ ከዚህ እኩይ አላማ ሰለባ ከመሆን ተጠብቆ በወንደማማችነትና በፍቅር ለዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ ሥርአት በሰላማዊ መንገድ በርትቶ ሲታገል ይሆናል። ለዚህም ተግባር መስካት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻን፣ ምሁራን፣ የፖለቲካ መሪዎችና የሃይማኖት መሪዎች በቅንነት በእውነትኝነት እዲነሱ የጩኸት ጥሪ በማቅረብ በዚህ አሰከፊ ጭፍጨፋ ያለቁ ወገኖቻችን ነፍሳቸውንcእግዚአብሔር አምላክ ይማር ዘንድ እንጸልያለን!! ገዳዮችንና አስገዳዮችንም በጥብቅ እናወግዛለን። እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ለኦርቶዶክሳውያን ክብረ በአላቸውን በሰላምና በደሰታ ማክበር ሲገባቸው በሐዘን፣ በመዝሙር ፈንታ እሪታ፣ በእልልታ ፈንታ ዋይታ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ጽናቱንና ብርታቱን እንዲሰጥልን ወደ አምላካቸን በመጮኽ ሐዝናቸን እንገልጣለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንን ከፈተና ይጠቅልን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *