Hiber Radio: ወልቂጤ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ወያኔ ይውረድ እያለ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ

የጉራጌ ዞን ዋና ርእሰ መስተዳደር በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት በዛሬው ዕለት ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ በወልዲያና በኦሮሞያ የተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑን የተደረጉትን ግድያዎች አውግዞ፣ግድያው እንዲቆምና  የወያኔ አገዛዝ እንዲወርድ በመጠየቅ ተቃውሞውን አሰምቷል።

በወልቂጤ ዛሬ አደባባይ ለተቃውሞ የወጣው ሕዝብ “እኛ ጉራጊዎች እና ስልጤዎች በአማራና በኦሮሞ ወንድሞቻችና እህቶቻችን ላይ የሚደረገውን ግድያ እናወግዛለን”

“ዳውን ዳውን ወያኔ”

“ወያኔ ሌባ”

“እኩልነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ”

“ዘረኝነት በቃን”

“የሕወሓት አገዛዝ ከስልጣኑ ይውረድ”

“የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ”

እና ሌሎችንም መፈክሮች እያሰሙ እንደነበር ለህብር/ ዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

ሕዝባዊ ተቃውሞው በአማራና በኦሮሚያ አካባቢዎች ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር የዛሬው የወልቂጤ ተቃውሞ ትልቅ ማሳያ ይመስላል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *