በወልዲያ ለሰላማዊ ሐይማኖታዊ በዓል የወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በሕወሓት የአጋዚ ጦር የተወሰደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ በአደባባይ ቁጣውን በቆቦ መርሳና በሌሎችም የሰሜን ወሎ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ የገለጸው ሕዝብ በሕወሓት የአጋዚ ጦር የተጨፈጨፉት ንጹሃን ተከትሎ ዛሬም ተቃውሞው አልበረደም።ይህን ተከትሎ አርበኞች ግንቦት ሰባትና ደሚህት የተሰኘው ሌላው በኤርትራ የሚገኘው ተቃዋሚ በጋራ ያወጡት መግለጫ በሕወሓት እየተጨፈጨፈ ያለውን ሕዝብ ተጠያቂ ያደረገና ስርዓቱ ሲሰጣቸው የነበሩ ሀሰት መግለጫዎች መሰረት የሆነው በሕዝባዊ ተቃውሞዎች ላይ የትግራይ ተወላጆች በዘራቸው ሳቢያ የጥቃት ሰለባ ሆነዋል ለሚለው እውቅና የሰጠ መሆኑ ብዙዎችን አስቆጥቷል።የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደጋፊዎችን ጨምሮ ወትሮም ድርጅቱ ላይ ጥያቄያቸው እያደገ ለመጣና የሕዝቡን ትግል ለመንጠቅ ይሞክራል ላሉት ተጨማሪ ማረጋገጫ ሆኗል።ተቃውሞውን ተከትሎ አቶ ነአምን ዘለቀ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር መግለጫውን አስመልክቶ ለቀረበው ተቃውሞ የሰጡት የጽሑፍ ምላሽ እነሆ፦
ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፣–የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂት የጋራ መገለጫ በሚመልከት
- ማናቸው ድርጅት አርበኞች ግንቦት 7 ጨምሮ ከአባላቱም ፣ከደጋፊዎቹም። ከህዝብም የሚመጣ ትችት መቀበል የግድ ነው (ግዴታው ነው)። ፍጹም ሰው እንደሌለ ሁሉ ፍጹም ድርጅት ሊኖር አይችልም። የሚሰሩ ደግሞ ይሳሳታሉ። ስህተቶችን በአግባቡና ገንቢ በሆነ መልኩ በልዩ ልዩ መስመሮች ሲገለጽ አንድን ድርጅት የሚማርና ስህተቶቹንም እየረመ የሚሄድ ያደርገዋል። በዚህ አመለካከት ያለውን ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይስማማሉ ብዬ እገምታለሁ።
- ሰሞኑን የወጣውና ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂት የጋራ መገለጫ በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ እንደ ሆነ ምንም የሚያጠያይቅ አይደለም። ስርዓትን መለወጥ ብቻ ሣይሆን የተረጋጋ ሐገር ለመፍጠር እንደሚንቀሣቀስ የፖለቲካ ሃይል በበደል ብዛት የተቆጡ ኢትዮጵያውያን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ዉስጥ እንዳይገቡ ማሣሠቡ ተገቢ ይሆናል።በመግለጫው እንደተቀሠው ሠማን እንጂ አረጋገጥን ተብሎ አልተጻፈም፤ በሐገሪቱ ክልሎች የሕወሐት አባላትና የሕወሐት መልዕክተኞች መኖራቸውንም በመግለጫው በግልፅ ያመለክታል፤ በአጠቃላይ የመግለጫው ይዘት ትናንት ከተከሠተው ይልቅ ሥለነገው የሚጨነቅ መሆኑንም ማስታወሡ ተገቢ ነው፡፡ የመግለጫው ዓላማ ይህ ቢሆንም በአንድ በተሻለና እወነታውን በተጨባጭ ከማሳየት ይልቅ አሻሚ በሆነ ቋንቋ በተጻፈ አንድ አንቀጽ ( በአንዱ ዛፍ) .ጫካው በመሸፈኑ ውዥንብር ተከስቷል፡፡
- በዋናው ጭብጥና መንፈስ (በጫካው) ወስጥ የተካተተው መልክት ሕዛብዊ ወያኔ አርነት ትግራይ (ህወአት) በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ኢትዮጵያን አፈርሳታላሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ፣ ይህንንም ተግባራዊ ለማድርግ የትኛውንም ስልት ከመጠቀም ወደሁዋላ እንደማይል፣ ከነዚህም መሰሪ ስልቶቹ ወስጥ በዋነኘት የትግራይን ህዝብ ምሽግ ለማድረግ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ማናከስና ወደ የማይታረቅ ቅራኔ ወስዶ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ህዝብ መነጠል ብሎም መገነጠል በመሆኑ
ሀ) “የትግራይ ህዝብና ህወአት አንድና የማይነጣጠሉ ናቸው” የሚለውን የ 26 አመታት የወያኔ ትረካና ፕሮፕጋናዳ መናድ፣ ማፍረስ ወሳኝ የትግሉ አካል መሆኑን ።
ለ) የትግራይ ህዝብ ፣ የትግራይ ምሁራን፡ የትግራይ ድርጅቶች የዚህ የወያኔ መሰሪ ተግባር ሰለባ እንዳይሆኑ እንዲያውም ትግሉን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን እንዲያቀጣጥሉ ጥሪ ማቅረቡ።
በትክክሉ፡ በጥልቀትና በረጅሙ በማሰብም የኢትዮጵያ ሀገራችን የወደፊት ሰላም ፣ ሀገራዊ አንድነት፡ የህዝቦች አብሮ መኖር መጻኢ እድል ለሚያስስበው ማናቸውም ቅን (ቅንን የሚለው ይሰመርልኝ) ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህ መልክት ወቅታዊም አንገብጋቢም መሆኑን ሊያጡት አይችሉም ።
- የወያኔ ፋሽስቶች የትግራይን ህዝብ ምሽግ አድርጎ የአምባገናዊ የዘረፋና የዘረኘነት ስረአቱን ለማሰቀጠል የሚያደርገውን የአልሞት ባይ ተጋዳይ እንቅሳቃሴ ለማምከን የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን ሁለ ገብ ትግሎችና ከወያኔ ፋሽስቶች ጋር የሚያድርገውን ትንንቅና ፍልሚያም በሚያፋፋምበት በአሁኑ ሰአት በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችና ታጋዮች ሁሉ (በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የኣርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ጨምሮ) የህወአትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊና ፡ ህዝቡም በትግሉ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ነው በመግለጫው የተገለጸው።
- ሌላው የመገለጫው ጫካ ዋና መንፈስ የአግ7 ንቅናቄ በወያኔ ፋሽቶች የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተንኮልና መሰሪነት ሊመጣ የሚችለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ከፍተኛ ስጋት እንዳለው ነው የተገለጸው። በዚህ ፋሽታዊው ሕወአት በሸረበው ወጥመድ ውስጥ ታጋዩ ማህበረሰብ እንዳይገባ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ነው ያሰመረበት፡ እነዚህ ዋና ዋና መልክቶች መግለጽ ሃላፊነት ከሚሠማው የፖሊቲካ ድርጅት የሚጠበቁ ተግባራት ናቹው፡፡
- በእርግጥ በዚሁ ብዙ አነጋጋሪ በሆነው መግለጫ ላይ የተጻፈው አንድ አንቀጽ (አንድ ዣፍ) የሚሰጠው ትርጉም ከላይ በስተመጨረሻ #5 ከተጻፈው የተለየና ብዙዎች በሌላ መልኩ እንዲረዱት ማድረጉ ለተነሳው ውዝግብ መንሴኤ ሆናል።
- በብዙሃን ቅን ኢትዮጵያውያን (አባላት፡ ደጋፊና፡ ለትግሉ ቀናዊ ከሆኑ) ኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶች አወዛጋቢዎችን አንቀጽ በሚመለከት የተነሱ ጥያቄዎች፣ ገንቢ አስተያየቶችና ፡ እርምት እንዲደረግና ንቅናቄው መልስ እንዲሰጥበት ከሚያስስቡ መልክቶች ሁሉ እንደተጠበቁ ሆነው ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ከወያኔ ይልቅ ትግላቸውን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለማድረገ የወስኑ ክፍሎችን በተመለከተ በአጭሩ ለማለት የምፈልገው በእርግጥ የሕዝቡ ሥቃይ ይሰማችኃልን ? በእርግጥ ከተሰማችሁ ሕዝብን ከሚያሠቃየውና ከሚጨፈጭፈው ሕወሐት ይልቅ ሕወሐትን የሚታገለው አርበኞች ግንቦት 7 እንዴት ዋነኛ ጠላታችሁ ሊሆን ቻለ? .መልሡን በቅንነት ለሚዳግፏቸው ወገኖቻችን እንደሚሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
- የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ምንም ሳይደርስባቸው ገና ከጅምሩ በጠላትነት ፈርጀውት ከወያኔ ይልቅ ዱላቸውን በሙሉ ጊዜና ህይል ሳይቆጥቡ ለዚህ የጎንዮሽ ልፊያና ጠለፋ የሰጡ፣ ነገር ግን ለዚህ ውስብስብና ብዙ አቀበትና ቁልቁለት ለበዛበት ትግል ምንም ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የማያደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ማህበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት እያየን ነው፡
- በአንጻሩ ይህን ትግል ዳር ለማድረስ ምን ያህል መስዋእትነት እየተከፈለና በተግባርም ብዙ ብዙ ተግባራዊ ስራዎች በሀገር ውስጥም በውጭም እየተሰሩ እንደሆነ የሚያውቁ፣ የሚረዱ፣ ለትግሉም ቀናኢ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የዚህ መሰሪ አካሄድ ሰለባ ላለመሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ፡ በስሜት ሳይሆን በአምክንዮና ለትግሉ የሚጠቅመውን፡ የወያኔን ፋሽታዊ አገዛዝን የሚያስጨንቀውና የሚያዳክመውን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ለድል የሚያደርሱ፣ የሚያበቁ ፣ ለሀገራችን ኢትጵዮጵያ ትንሳኤን የሚያፋጥኑ ተግባራት ላይ ማተኮር ይገባል። በሰከነ አእምሮ ማሰብ የሚያስፍልግበት ስሱ ወቅት ስለሆነ፡ ቆም ብለን ፡ ትንፋሽ ወስደን በረጅሙና ከፊታችን በተደቀነው ተግባሪዊ ትግል ላይ አይናችንን እንዳናነሳ ማድረግ ያስፈልጋል። ጥንቃቄ እንዳርግ በሚል በትህትና ለማሳሰብ እወዳለሁ።
ነአምን ዘለቀ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።