Hiber Radio: በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል… በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ… በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ… “በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው” – ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ… ጋዜጠኛ አበበ ገላው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 11  ቀን 2007 ፕሮግራም

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ለሞቱ ወገኖቻችን  ነፍስ     ይማር !  መጽናናትን እንመኛለን !

< …በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ማዘን ማልቀስ ብቻ በቂ  አይደለም። በአገር ቤትም በውጭም በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም የሚቻለው ተባብረን ይሄን ስርዓት ማስወገድ ስንችል ብቻ ነው…የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ጉዳይ አልተቀየረም የሴትዮዋ ንግግር መሰረተ ቢስ ነው ራሳቸው ማብራሪያ ይሰጡበታል…>

ጋዜጠኛ አበበ ገላው  በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ስለሞቱ ወገኖቻችንና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣንን መግለጫ አስመልክቶ  ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ

<… በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው…መፍትሄው በሀይማኖት ፣በጎሳ ሳንከፈል መከራ ሲደርስብን አብሮን የሚቆም መንግስት የሌለን በመሆኑ ለራሳችን ራሳችን እንነሳ…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ስለ የሊቢአው የአይ.ሲ.ስ የአሸባሪዎች ድርጊትና ተያያዥ ጉዳዮች  ጠይቀነው ከመለሰው (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሊቢያ በአይ.ሲ.ስ አሸባሪዎች የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ፣ የስርዓቱ ግዴለሽነትና የግብጽ ከአሸባሪው ጋር መፋለም (ልዩ ጥንቅር)

<…ሁለት ወንድሞቼ ደቡብ አፍሪካ ናቸው እነሱ ያሉት እኛ ቢያንስ እየታገልን የምንሞት ነን በሊቢያ የታረዱ፣በጥይት በአሸባሪዎች የተገደሉ ወገኖቻችን ጉዳይ አስለቅሶናል ።የመንግስት ተብዬው ክህደት አሳዝኖናል እባካችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ጸልዩ እያሉ ነው …>

አስተያየት ሰጪ ለህብር ከገለጹት

<…ኢትዮጵያውያንን በቁም ያቃጠሉትን ለፍርድ ለማቅረብ እየተንቀሳቀስን ነው…ችግር ላይ ያሉትን ለመርዳት ሩጫ ላይ ነን…>

አቶ ደረጄ መኮንን በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ዋና ጸሐፊ ለህብር ከሰጡት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሚገኙበት በቬጋስ የተጠራው ስብሰባ  ( ከስብሰባው አዘጋጆች አንዱ አቶ አሸብር ጋር የተደረገ ቆይታ)

<…በደቡብ አፍሪካ አሁንም ሕይወታችን አደጋ ላይ ነው ዙሉዎቹ ቀድሞም አጋጣሚ ነው የሚፈልጉት ወገኖቻችን ይጩህልን…> አቶ ታሪኩ ጀማል ከደርባን ደቡብ አፍሪካ አቅራቢያ ለህብር እንደተናገሩት(ሙሉውን ያዳምጡ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን አደጋ ውስጥ ናቸው ፣

በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል፣

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ እሳት በቁማቸው የለኮሱትን በህግ ለመፍረድ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገለፁ

በደርባን በድርጊቱ የተጠረጠሩ 19 የዙሉ ጎሳ አባላት ተይዘዋል

በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ ሊቢያ ላይ አንገታቸው ተቀልቶና በጥይት ተደብድበው በሞቱት 30 ወገኖቻችን ጉዳይ ቁጣቸውንና ሐዘናቸውን እየገለፁ ነው

አገዛዙ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላጣራሁም ማለቱ የተለመደ የስርዓቱ ጭካኔ ነው ተብሏል

በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-041915

(ህብርን በተጨማሪ  በዘሐበሻ እና በሌሎችም  ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል በየቀኑ ለማዳመጥ 2 መጫን ብቻ በቂ ነው።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *