በሊቢያ በጥይት ከተገደሉት ቤተሰቦች ሁለቱ አዲስ አበባ ላይ ለቅሶ ተቀመጡ ፣ሐዘንተኞች ኢትዮጵያውያን አይደሉም ያለውን መንግስት ቴሊቪዥን ለቅሶውን እንዳይቀርጽ ተቃውሞ ማቅረባቸው ተሰማ

በሊቢያ በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ በጥይት ከተገደሉት ሁለቱ ኢያሱና ባልቻ
በሊቢያ በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ በጥይት ከተገደሉት ሁለቱ ኢያሱና ባልቻ

family pic

Ethio_libiya_041915Ethiopian_libiya_041915_06

በሊቢያ በአይ.ሲ.ስ አሸባሪዎች በሁለት የአገሪቱ ክፍሎች አንገታቸው ከተቀሉና በጥይት ተደብድበው ከሞቱት ሰላሳ ኢትዮጵያውያን መካከል ከተረሸኑት ውስጥ የሁለቱ ወጣት ኢያሱና ባልቻ የተባሉት ቤተሰቦች አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጨርቆስ 25 ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ተረድተው ለቅሶ መቀመጣቸው ታውቋል። የውጭ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ሁኔታውን በስፍራው ተገኝተው ሲቀርጹ <<..ኢትዮጵያውያን መሆናቸው አልተረጋገጠም…>> ሲል የነበረው አገዛዝ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለቅሶውን እንዳይቀርጽ ሐዘንተኞች የተከላከሉ ሲሆን በአካባቢ ሽማግሌዎች ምልጃ ለቅሶውን ቀርጸው ወጣቶቹን የሚያውቁትን ማነጋገራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ያረጋገጡትን የኢትዮጵያውያን በአሸባሪዎቹ ጥቃት መገደል የካደው በሕወሃት የሚመራው የኢትዮጵያው አገዛዝ በራሱ ደጋፊዎች ጭምር ውግዘት ያስከተለበት ድርጊትን ዘግይቶ ለማስተባበል እየሞከረ ነው። የአሜሪካ መንግስት ሳይቀር ትላንት በኢትዮጵያውያን ላይ በአሸባሪዎቹ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ መግለጫውን በሁዋይት ሐውስ ድህረ ገጽላይ ካወጣ በሁዋላ ያገር ቤቱ አገዛዝ <<ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ>> ለማለት እየሞከረ ይገኛል። ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት መብታቸውን የሚጥሰው አገዛዝ ተሰደውም ችግር ቢደርስባቸውም ደንታ እንደሌለው ተረድተው ለነጻነታቸው በጋራ መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው ጋዜጠኛ አበበ ገላውና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ የአሸባሪዎቹን ድርጊት ተከትሎ ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ቁጣቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *