በሲድኒ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እና የሻማ ማብራት ምሽት ሊያካሂዱ ነው

በአውስትራሊያ ሲዲኒና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሊቢያ በአይሲኤል አማካኝነት ሕይወታቸውን ለተቀጠፉ; እንዲሁም በየመን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የሚሆን የተቃውሞ እና የሻማ ምሽት የፊታችን እሁድ ጠርተዋል::

በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በሊቢያ የተወሰደውን አሰቃቂ የአሸባሪዎችን የግፍ ግድያ የሚያወግዝ ፣በየመንና በደቡብ አፍሪካ የተገደሉትን የሚያስብ የሻማ ማብራት ስነስርዓትና ሕዝባዊ ስብሰባ በአውስትራሊያ በሲዲኒና አካባቢዋ ለሚኖሩት ኢትዮጵያውያን በኒው ሳውዝ ዌልስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አማካይነት መጠራቱ ታውቋል።

የህብር ሬዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ አብይ አፈወርቅ ከስፍራው በላከው መረጃ በሻማ ማብራቱና በስብሰባው በሊቢአ በአይ.ሲ.ሲ የተሰው ወገኖችን በተመለከተ ሐዘንና ቁጣቸውን ከመግለጽ ባለፈ ለቀሪዎቹም ምን ሊደረግ ይገባል የሚለውን ለመነጋገርና በአካባቢው አመራር ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ጭምር መሆኑን ገልጿል። በስዲኒና በአካባቢው ላሉ ኢትዮጵአውያን በመጪው ዕሁድ አፕሪል 26/2015 ከምስቱ 6፤30 ፒኤም እስከ 7 ፒኤም የሚያደርጉት የሻማ ማብራትና ሕዝባዊ ስብሰባ ካራማታ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ቸርች ጎዳና ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዝርዝር መረጃው በተከታዩ ፖስተር ተካቷል።

Sydnet_australia_candle_light

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *