እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከዳግማዊው እስር ተፈቱ
እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጎተራ ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ከመጋቢት 16/2010 አዲስ አበባ የታሰሩት ለ11 ቀናት ከታሰሩበት የተፋፈገ እስር ቤት ዛሬ ማምሻውን መውጣታቸውን ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከስፍራው በገጹ ዘግቧል።
ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት ለማህበራዊ ግንኙነት ከእስር የተፈቱትን ለማመስገን ከተጠራ ፕሮግራም ላይ ታፍሰው ከተወሰዱ በሁዋላ ኮኮነብ የሌለውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መያዝ በወንጀል የተጠየቁነትና የተመረመሩበት ሲሆን በተጨማሪም በተለይ አንዷለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በወሎ ተገኝተው በወልዲያ ጭፍጨፋ የ12 ዓመቱን ህጻን ዮሴፍ ጨምሮ የሟች ቤተሰቦችን አጽናንተው ግድያ እንዲቆም መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን በጣቢያ እስር ወቅት ለምን ወልዲያ እንደሔዱ ተጠይቀዋል።
መጋቢት 16/2010 አዲስ አበባ የታሰሩት
1) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
2)ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
3) አቶ አንዱዓለም አራጌ (ፖለቲከኛ)
4) አቶ አዲሱ ጌታነህ (የህግ ባለሙያ)
5) ጦማሪ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ
6) ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን
7) ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
8) ወ/ት ወይንሸት ሞላ (የፖለቲካ ፓርቲ አባል)
9) አቶ ይድነቃቸው አዲስ (የፖለቲካ ፓርቲ አባል)
10) አቶ ስንታየሁ ቸኮል
11) አቶ ተፈራ ተስፋዬ
ሁሉም ተፈተዋል!
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።