Hiber Radio: አምንስቲ ኢንተርናሽናል የጋበዘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቦሌ ላይ ፓስፖርቱን ተነጥቆ ከአገር እንዳይወጣ ታገደ

(ህብር ራዲዮ)ዓለም አቀፉ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን አስመልክቶ የጋበዘውና ነገ አምስተርዳም ይገባል ተብሎ የተጠበቀው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በሕወሃት የኦርፖርት ደህነት ባለስልጣናት ከአገር እንዳይወጣ አግደው ፓስፖርቱንም መንጠቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።
አምንስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን  ሲያከብር ለክብር በክብር እንግድነት የጠራው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሊወጣ ሲል በህወሃት መታገቱን ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ የላከልን ዘገባ አረጋግጧል።  በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም። እስክንድር ነጋ   የመጨረሻውን ሳንደምረው ለ8 ጊዜ ታስሯል። እ. ኤ. አ, በ 2013 በሽብርተኝነት ተከሶ  18 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።      እስክንድር ነጋ የካቲት 14 ቀን 2018 ከሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጋር ቢለቀቅም ለ 9 ጊዜ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት ለማህበራዊ ግንኙነት መገኘቱ ወንጀል ሆኖ በጣቢአ በአስቸጋሪ ሁኔታ ታስሮ የቆየ ሲሆን በጣቢያ ዋስ ከእነ አንዷለም አራጋ፣ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን ጨምሮ አብረው ታፍሰው አብረው በቅርቡ ታስረው መፈታታቸው ይታወሳል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአገሪቱ የዴሞካራሲ ለውጥ አይቀሬ መሆኑን ሕዝቡ ለለውጥ መዘጋጀቱን ከዘጠነኛው እስር በሁዋላ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በሰጠው ቃለ መጠይቅ በስፋት አብራርቶ እንደነበር አይዘነጋም።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

እስክንድር ከዘጠኝ በላይ የክብር ሽልማቶች ያገኘ አኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።
1.  በ 2011 PEN America (NY,)
2.  በ 2012 Barbara Goldsmith Freedom to Write Award
3.  በ 2014 World Association of Newspapers’  Golden Pen of Freedom Award
4.  በ 2015 PEN Canada Freedom of Expression Award
5.  በ 2017 International Press Institute World Press Freedom Hero
6.  በ 2018 Oxfam Novib/PEN Award for Freedom of Expression (60 laureates)
7.  ሂዩመን ራይት ዋች የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እና አምነስቲ የኢንተርናሽናል የክብር ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ዶር አብይ አህመድ ለውጥ ሊያመጣ ቃል በገባ ሳምንታት ቢቆጠሩም የህወሃት አፈና እና ግድያ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የአለም መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

እስክንድር ነጋ በሆላንድ ሃገር ከተዘጋጀለት የአምነስቲ ዝግጅት በኋላ ልጁን እና ባለቤቱን ለማየት ወደ አሜሪካ ሊያመራ እንደነበር ይታዋቃል

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *