የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 28 ቀን 2010 ፕሮግራም
ሕዝብ እስከ መቼ በገዛ አገሩ ተፈናቃይ ይሆናል? ደራሲና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሸንቁጥ አየለ ጋር በስፋት ተወያይተናል (ክፍል አንድን ያድምጡት)
ከሻኪሶ የሚታፈሰው ወርቅ ለአገርም ለክልሉም ጥቅም ካልሰጠ ወርቁ የሚዛቀው ለማን ነው? ከትላንት እስከ ዛሬ የነበሩትን ችግሮችና የህዝቡን ብሶት የችግሩ ሰለባ የሆነው የአካባቢው ተወላጅ ጋዜጠና በዳሳ ሀይሉ ጋር በስፋት ተወያይተናል( ያድምጡት)
የዶ/ር አብይ የሱዳን ጉዞ ለማን ጥቅም? አለ ነገር፦መሬት ለወደብ?ወይስ ወደብ ለመሬት?ሰሞነኛው የኢትዮ-ሱዳን ወዳጅነት ሲቃኝ(ልዩ ቅኝት)
እና ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ጸረ ወያኔ የትጥቅ ትግሉ ይቀጥላል ተባለ
የአማራም ሆነ የሌላው ሕዝብ መፈናቀል ስርዓቱ እስካልተለወጠ እንደማይቆም ተገለጸ
ከ 14 ሚሊዬን በላይ ህዝብ የረሀብ አደጋ ስጋት አጥልቶበታል
የአረብ ሊግ ኢትዮጵያ እና ግብጽን አስመልክቶ ጥሪ አቀረበ
አብዲ ኢሌ በብስጭት የዶ/ር አብኢን ምስል ከጂጂጋ ኤርፖርት እንዲወርድ አደረጉ ተቃውሞ ቀጥሎባቸዋል
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ደራሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አሜሪካዊው የህዝብ እንደራሴ አገራቸው በኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ቤዝ እንድትከፍት ጥሪ ማቅረባቸው እና
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።