ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው ባህርዳር ለሚገኙት የአማራ ተወላጆች ግሎባል አሊያንስ 801 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል። ከአገር ቤት የተፈናቃዮቹ ተወካዮችም አረጋግጠዋል።ግሎባል አሊያንስ ከህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት በሕዝቡ ላይ የሚደርሱችግሮችን በቻለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በበኩሉ አስቀድሞ ለተፈናቃዮቹ ለመድረስ 20 ሺህ ዩሮ በጎ ፈንድ ሚ ማሰባሰቡ አይዘነጋም።
ግሎባል አሊያንስ ለተፈናቃዮቹ መስጠቱት የድርጅቱ የወቅቱ ሊቀመንበር አክቲቪስት ታማኝ በየነ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ጠቅሶ ወደፊትም የሕዝቡ ትብብር እስካለ ድጋፉ ይቀጥላል ብሏል።
በባህር ዳር ከቤንሻንጉል ክልል ሕጋዊ ይዞታቸው የተፈናቀሉት የአማራ ብሄር ተወላጆች ወደ ቀዬያቸው መመለስ የሚፈልጉ ሲሆን የአማራ ክልል የይስሙላው መሪ ብአዴን እስካሁን መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ከተጠለሉበት ቤተ ክርስቲያን ጭምር ማዋከቡ ከአንዱ ወደ ሌላው እንዲባረሩ ማድረጉ በተለያዩ መንገዶች ድርጊቱ በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማስከተሉን መረዳት ይቻላል።
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።