ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ባለስልጣናት ጭምር ጥቁር በዛሬው ሰልፍ ላይ በቦንብ ፍንዳታ ተጎጂ የሆኑ ዜጎችን በጥቁር አንበሳ ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ይፋ ሆነ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕወሓት ዳግም የትግራይ ሕዝብን በግዳጅ ሰልፍ በነገው ዕለት ለማስወጣት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የዛሬው የቦንብ ፍንዳታ ግንባር ቀደም ተጠርጣሪ መሆኑን ከወዲሁ መረጃዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል።የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ በነገው ዕለት መግለጫ ይሰጣል።
ዛሬ በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሰልፍ ላይ ጥቃት እንዲደርስ መንገድ የከፈቱ የጸጥታ ቁጥጥሩ መላላት ተጠያቂ የሆኑት የአዲስ አበባ ፖሊስ ም/ኮሚሽነርን ጨምሮ ዘጠኝ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት አስታውቋል።በኢትዮጵያ ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ድርጊቱን አውግዘዋል።የሶማሊያ፣የኤርትራ አምባሳደር እና የጅቡቲ መንግስታት የሽብር ጥቃቱ አውግዘዋል። የአሜሪካ ኤምባሲና የአውሮፓ ሕብረት ኤምባሲ ድርጊቱን አውግዘዋል።የኦሮሚያ ክልል፣የሶማሌ ክልል፣የድሬዳዋ አስተዳደርና ሌሎችም ድርጊቱን አውግዘው መግለጫ አውጥተዋል።በአንዱ ቦንብ ሳቢያ በጥቃቱና በተፈጠረው መረጋገጥ ከ160 በላይ ንጹሃን ሲጎዱ ቢያንስ ሶስት ከቆሰሉት መካከል ሕይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ችለናል። በሰልፉ ላይ ተጨማሪ ሁለት ቦንቦች ሳይፈነዱ መክሸፋቸው በተለይ አንዱ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሲሆን ፖሊስ ነኝ የሚል ምክንያት ሰጥቶ ወደ ህንጻ አናት ወጥቶ ጥቃት ሊያደርስ ሲገሰግስ በጥርጣሬ በግድ በህዝቡ ግፊት ተይዟል። ድርጊቱ የተጠናከረ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም አስቀድሞ የተደራጀ ሀይል እንደነበር ያሳያል።ጠ/ሚኒስትሩ ጉዳዩ ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋሉ ካሉ በሁዋላ እስራቱ መከተሉ ምርመራውም ቀጥሏል።
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በጎንደር፣በደብረ ማርቆስ እና በደሴ ደማቅ ተመሳሳይ ዓላማ አለው ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን በደቡብ በዱራሜ ከተማም ሰልፍ ተደርጎ ሕዝቡ የዶ/ር አብይን የለውጥ ተስፋ እርምጃ እንደሚደግፍና ከጎናቸው እንደሚሆን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቂክሊክስ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች በሴፕቴምበር 16/2006 ዓ.ም የደረሰውን የቦንብ ጥቃት የአቶ መለስ የሚመሩት በሕወሓት የበላይነት የሚመራው መንግስት ራሱ መፈጸሙን በጊዜው የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ ለመንግስታቸው የላኩትን መረጃ ጠቅሶ ማጋለጡ አይዘነጋም።