ህብር ሬዲዮ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ሲገጥሙት ቢቆዩም እነዚህን ሁኔታዎች ተቋቁሞ ከአምስት ዓመታት በላይ ዘወትር ዕሁድ ሲያሰራጭ ከቆየበት ኬ.አር.ኤል.ቪ ራዲዮ ጣቢያ ጋር የነበረውን ኮንትራት በጣቢያው ፍላጎት አቋርጦ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲሱ ስትዲዮ የተለመደ የቀጥታ ስርጭቱን በተመሳሳይ ቀንናሰዓት በህብር ዴዲዮ ድህረ ገጽና በስልክ 7124328451 ላይ ሳያቋርጥ ቀጥሏል።
ከስልክና ከኢንተርኔት በተጨማሪ በተለይ በቬጋስ በ1340 ኤ.ኤም የሬዲዮ ሞገድ ስታዳምጡን የቆያችሁ አድማጮቻችን አስቀድሞ እንዳሳወቅነው እንደተለመደው ዘወትር ዕሁድ በአካባቢያችን ሰዓት አቆጣጠር በ6፡30 እስከ 8 ፒ.ኤም የምናስተላልፈው የቀጥታ ስርጭት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ www.hiberradio.com ወይም በስልክ 7124328451 በመደወል ሳይቋረጥ መደመጥ ቀጥሏል። ህብር ሬዲዮን ከቀጥታ ስርጭት በተጨማሪ ዘወትር በማንኛውም ሰዓት በህብር ሬዲዮ እና በዘሐበሻ ድህረ ገጽ ወይም የቀጥታ ስርጭቱን በምታደምጡበትየስልክ ቁጥር 7124328451 ማዳመጥ የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። ለማንኛውም አስተያየቶቻችሁ በ7025896347 በመደወል፣በፌስ ቡክ ገጻችን ወይም በኢሜል አድራሻችን hiberradio@gmail.com ብትጽፉልን ሊደርሰን የሚችል መሆኑን በአክብሮት አድማጮቻችንን ለማስታወስ እንወዳለን።