(በጌታቸው ሽፈራው)
የአማራ ልዑካን ከአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጋር በአማራ ሕዝብ ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ፣ በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበር፣ እንዲሁም አቶ አለልኝ ምህረቱ (ጠበቃ) እና ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ (በግል) ተገኝተዋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላት በአማራ ሕዝብ እየደረሰ ስለሚገኘው በደል፣ ቀጣይ ትግል ያስረዳ ሲሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማፅዳትና ሌሎች ወንጀሎችንና የሕዝብ ትግል በዝርዝር ተገልፆአል።
በተመሳሳይ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴን ወክለው ከቀረቡት መካከል አቶ አታላይ ዛሬ በወልቃይትና አጠቃላይ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል አስረድተዋል። የትህነግ/ህወሓት አገዛዝ መሰረቱ አማራን ጠል መሆኑን በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
በአማራ ሕዝብ ላይ በእስር ቤት የሚፈፀመው በደልም ለምክር ቤቱ አባላቱ የተገለፀ ሲሆን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆነችው ንግስት ይርጋ ማዕከላዊ ውስጥ የተፈፀመባትን በደል በማሳያነት አስረድታለች። በመርመራ ወቅት እርቃኗን መመርመሯንና 9 ጥፍሮቿ መነቀላቸውንም ገልፃለች። በተጨማሪ በስም 6 ያህል አማራዎች በምርመራ ወቅት ብልታቸው መኮላሸቱን ከእነሱም መካከል አስቻለው ደሴ በእስር ላይ የሚገኝ መሆኑ ተጠቅሷል። አስቻለው ደሴን ጨምሮ አሁንም ብዙዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ በላይ ማናየ አስረድቷል። በምርመራ ወቅት በደል የፈፀሙ አካላት እስካሁን ተጠያቂ አለመደረጋቸውንም ለምክር ቤት አባላቱ ተገልፆአል።
በአጠቃላይ የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን በደል፣ በተለይም በእስር ቤት እየተፈፀመ ያለ ግፍ፣ በሕዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማፅዳት፣ እየተደረገ ያለው ትግልና የወደፊት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።