የኢትዮጵያውያን ሴቶች ድምፅ በኢትዮጵያ የፖልቲካ ትግል ውስጥ ሴቶች ያደረጉተን አስተዋጽዎ አሰታወሶ የሰሞኑ ሹመት ተገቢ መሆኑን ገልጾ የድጋፍ መግለጫ አወጣ።ታሪከነ መልስ ብሎ በማሰታወስ የ ሴቶችን የትግል ተሳትፎ ለማሰታወስ ጭምር የሞከረውን መግለጫ ያንብቡት ። ያስራጩት።
ከኢትዮጵያውያን ሴቶች ድምፅ የተሰጠ የድጋፍ መግለጫ
“ስለ ሴቶች ብዙ ያወራሁ ከመሰላችሁ ገና ምን ተነካና” ፕሬዝዳንት ልሳነ ወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ጥያቄ በይፋ እራሱን ለማደራጀት በ1968 ዓ.ም የሴቶች አስተባባሪ በመባል ሲጠራ በነበረው 14 ምርጥ ሴቶችን በሥራ አስኪያጂነት ያቀፈው ድርጅት በደርግ ከተዘጋ በኋላ የሴቶች ጥያቄ ሥልጣንን ለማጠናክርና የሴቶችን የምርጫ ድምፅ ለማግኝትና የቡድንን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ሲኮላሽ ቆይቶ ዛሬ ሴቶች በአገራቸው ለመጀመሪያ በአፍሪካም ቀዳሚነት የሚታይበት ትልቁን ያመራር እርከን እረግጠውታል::
ታዋቂነት ቢነፈጋቸውም ለዚህ ቀን መምጣት ብዙ ሴት እህቶቻችን የህይወት ዋጋ ከፍለዋል። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለማስታወስ በሴቶች አስተባባሪ ኮሚቴ ተሳትፈው ለመጀመሪያ ግዜ በፓርላማ ውስጥ ለ300 ሴቶች የንቃት ትምህርት ከጡትና በደርግ ግፈኛ ሥርአት ከተገደሉትና አንዳዶችም እስከ ትጥቅ ትግል ደረጃ ድረስ ለሥርአት ለውጥ ለእኩልነት ታግለው ሕይወታቸው የተቀጠፈውን ስንጨምር
1/ ስላማዊት ሀይሌ፣ በአሜሪካን አገር ትምህርቷን ጨርሳ የተመለስች በኢህአሰ ውስጥ የተዋጋች
2/ ንግሥት አዳነ፣ ከፍተኛ ትምህርቷን በውጭ ስትከታተል ቆይታ ትምህርቷን ስትጨርስ በመኢሶን ውስጥ ገብታ በትልቅ ሀላፊነት ተሰማርታ ደርግን ስትረዳ ከቆየች በኋላ በሚያሳዝን ሁኔታ በደርግ የተገደለች
3/ ንግሥት ተፈራ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቴ ተመርቃ በሰራተኛው ማህበር ውስጥ በመሳተፍ የሰራተኛ ሴቶችን ያደራጀች በኢህአፓ ውስጥ በመታገል በደርግ መንገድ ላይ የተገደለች
4/ አጥናፍ አለም የማነ፣ ከውጭ አገር ተመልሳ በመኢሶን ውስጥ በመታገል አስተባባሪ ኮሚቴን ከመስረቱት እህቶች አንዷ በመሆን ስታግለግል ቆይታ በኋላ በደርግ የተገደለች
5/ መዝገብነሽ አባዩ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 3ኛ አመት ተማሪ የነበረችና በወቅቱ እጅግ ተወዳጅ የነበረችው የጎህ መፅሄት አዘጋጅና የሴቶች አስተባባሪ ኮሚቴ አባል በመሆን እስከ ህይወቷ ፍፃሜ ድረስ የሴቶችን ጥያቄ የገፋች በኋላም የማስትሬት ድግሪዋን ከፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ባገኘች በሳምንቱ እቤቷ ውስጥ ተገላ የተገኘች በኢህአፓ ውስጥ የከፍተኛ አመራር ቦታ የነበራት
6/ ጌራ ወርቅ፣ ከውጭ አገር ተምራ ገብታ በመኢሶን ውስጥ ተሳትፋ በሴቶች አስተባባሪ ኮሚቴ ያገለገለች 7/ ፍ/ገ ፣ ከውጭ ትምህርቷን ጨርሳ በአገር ውስጥ የሴቶች አስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ አኩሪ ሥራ የሰራች
እጅግ ብዙዎችን መጥቀስ ይቻላል ግን እነዚህ ጀግና ሴቶች ህይወት የከፈሉለት ትግል ተድፍኖና ተኮላሽቶ ከኖረ በኋላ ዛሬ የኢትዮጵያን እናቶችን አይን ከእንባ የሚዳርጉ ሰቆቃቸውን የሚካፈሉ ጩኽታቸውን የሚዳምጡ ታላላቅ ያአገር መሪዎች ከካቢኔው ምርጫ ጀምሮ እስከ ፕሬዝዳንትነት የበቁ እህቶቻችን በመወለዳቸው እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን የኢትዮጵያ እናቶች መቸም ቢሆን መቸ ደረት መተው ኩታ ዘቅዝቀው እልጆቻቸው እሬሳ ላይ እየተደፉ ወልዶ መቅበር ስለአንገሸገሻቸው ከስቀቀን ጎዳና በሰላምና በመፈቃቀድ በእኩልነትና በፍቅር ወደ ዲሞክራሲ የምትጓዘውን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት አጥብቀው እንደሚሰሩ በማመን በዚህ ላይ የተመስረተ ለሴቶች እኩልነትና የኢኮኖሚ ብሎም የፖለቲካ የሶሻል ግንባታውን ያጠናከረ የሴቶች ማህበር መፍጠሩ ቅድሚያ እንዲሰጠው እንጠቁማለን። የሴቶች ተሳትፎ እንዲጠነክር የኢኮኖሚ አውታር ባለቤት መሆን ግድ ነውና:: ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ የናቶችን ድካምና ትግሥት የሚስቶችን ጥበበኝነትና ድጋፍ ሰጭነት የቤተሰብና የህብረተሰብ አውራ መሆናቸውን የተገነዘበው ብሩሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ቃሉን በተግባር በማሳየቱ ለዲሞክራሲና ለሰዎች ልጆች መብት እስከታገለ ድረስ ከጎኑ እንደምንሰለፍ በድጋሚ እንገልፃለን። ከእንግዲህ በኋላ የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ይደርቃል! የወላድ መካን አይሆኑም! ለዲሞክራሲ የሚደረገው ጥረት ያቸንፋል!
እኩልነት ለአለም ሴቶች!
ያለሴቶች ተሳትፎ ምሉእነት የለም!
ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር።
ከኢትዮጵያ ሴቶች ድምፅ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።