(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በኢትዮጵያ ገዢው ፓርቲ በሙሉ ቁጥጥሩ ለአምስተኛ ጊዜ ባከናወነው የይስሙላ ምርጫ የሕዝብ ድምጽ መዝረፉ በግልጽ እተነገረ ሕዝቡ፣የተቃዋሚ መሪዎችና የምርቻ ታዛቢዎች እየገለጹ ባለበት ሁኔታ ይህንኑ ተግባር በሚያጋልጥ መልኩ ራሱ የሚለጥፋቸው የየምርቻ ጣቢያ ውጤቶች ዘረፋውን ማከናወኑን ጭምር የሚአጋልጡ መሆን ጀምረዋል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የስርዓቱ ጠ/ሚ/ር ተቃዋሚዎችን <<ቁጥር አያውቁም እያሉ >> በከሰሱ ማግስት በተወዳደሩበት በወላይታ ዞን ምርጫ ጣቢያ በአንዱ ለሕዝቡ በተለጠፈ ውጤት መቶ በመቶ ድምጽ አግኝተው አሸነፉ ተባለ።
አቶ ሀይለማርያም በተወዳደሩበት በዚህ ምርቻ ታቢያ ለምርጫ ተመዘገቡ ከተባሉት 865 መራጮች 865 አግኝተዋል ለብሎ ሲለጠፍ ሰማያዊ ፓርቲ እና በጣቢያው የተወዳደረው ሌላው ፓርቲ ዜሮ አግኝተዋል ይላል ቅጹ። አገዛዙ በግልጽ ዘርፎታል የተባለውን ይህን ምርጫ ይህን በመሰለ ራሱን የሚያጋልጥ የቁጥር ጨዋታ ውስጥ ገብቶ መታየቱ ዝርፊአውን ራሱም እያጋለጠው መሆኑ እየተነገረ ነው። አቶ ሀይለማሪአም ባለፈው ዕሁድ መርጠው ሲወጡ በሰጡት አስተያየት ላይ ተቃዋሚዎች አካውንቲንግ ይማሩ ሲሉ ራሳቸውን ትዝብ ላይ የጣለ ንግግር በተናገሩ ማግስት መቶ በመቶ ለምርጫ የተመዘገበው መረጣቸው መባሉ የቁጥሩ ችግር የት እንዳለ ታወቀ የሚል ተጨማሪ አስተያየት ጋብዟል። በአቶ ሀይለማሪአም ውጤት መሰረት በዚአ ምርቻ ጣቢያ ከተመዘገበው መራጭ አንድም ሰው ታሞም ይሁን ሳይመቸው ወይ በስራ አጋጣቢ ምርቻ ካርድ ከወታ በሁዋላ ከዚአ አልሄደም
የዘንድሮ ምርቻ ታማኝና ገለልተኛ የተባሉት የአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ የውጭ የምርጫ ታዛቢዎች ያልተሳተፉ መሆኑ ቢታወስም ለወትሮው አገዛዙ የሚፈልገውን የሚናገሩት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች እንደ ታዛቢ ኮሮጆውን አስቀድሞ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት እንይ ብለው በ29 ምርቻ ጣቢአዎች መከልከላቸውን አጋልጠዋል። ስርኣቱ ምርቻ ከሚያጭበረብርባቸው ስልቶች አንዱ ኮሮጆውን አስቀድሞ በድምጽ መሙላት መሆኑ ተደጋግሞ የተጋለጠ ሲሆን ብዙም ገለልተና የማይባሉት የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች ይህን ማጋለጣቸው የዘንድሮው ምርጫ ላይ ስርዓቱ እንደፈለገው ራሱን አሸናፊ የሚያደርግበትን ቁጥር ቢናገር ተአማኒ ባለመሆኑ ተቃውሞ ይነሳብናል በሚል ከምርቻው ዋዜማ፣በምርጫው እለትና በሁዋላ በተቃዋሚ ምርጫ ታዛቢዎች፣ በተቃዋሚ አባላትና አመራሮች ላይ ወከባውንና ጥቃቱን በማጠናከሩ ምርጫውን ተከትሎ ሁለት የኦፌዴን መድረክ ታዛቢዎች በአገዛዙ ታጣቂዎች ተገለዋል።
ስርኣቱ ስልጣን ላይ የወጣበትን በኣል ዘረፈውን የምርቻ ውጤት አስታኮ በጭፈራ ሊአከብር እየተዘጋጀ ሲሆን ጎን ለጎን የተቃውሞ መነሳት በፈጠረበት ስጋት ያልታወጀ ሰኣት እላፊ በየቦታው ተግባራዊ እየሆነ ወታደሮች፣ሚሊሳዎችና ፖሊሶች ሕዝቡን እአስፈራሩ በተቃዋሚነት የጠረጠሯቸውን እአሳደዱ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ተቃዋሚዎች የሕዝብ ድምጽ መዘረፉ ላይ አላቸውን ተቃውሞ ለማሰማት ሰልፍ ሊተሩ ይችላሉ የሚል ግምት አሳደረ ሲሆን ውጤቱን ዝርፊ እያሉ በተናጠል አንዳንድ የእውነተኛ ተቃዋሚ አመራሮች በማውገዝ ላይ ናቸው።
ሰሞኑን የተዘረፈውን የሕዝብ ድምጽ እንዲከበር በኦሮሚአ ክልል የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታውሞ አሰሙ ሲሆን ይህ ተቃውሞ በሌሎች አካባቢዎችም ሊቀጥል ይችላል በሚል ስጋት አገዛዙ አፈናውን አጠናክሯል።
በምርጫ 2002 በትግራይ የአረና የምርጫው ተወዳዳሪ አቶ አረጋዊ ገ/ዮሃንስ በምርቻ 1997 ደግሞ በአርሲ ምርቻ ተወዳድረው አለፉና በሳሸመኔ የዶ/ር መረራ ድርጅት የነበረው የዚያን ዘመኑ ኦብኮ የምርቻ ታዛቢ መገደላቸው ይታወሳል።ምርቻውን ተከትሎ በ97 በስፋት ሕዝቡ ድምጼ ይከበር የሚል ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን በተለኢ በዩኒቨርስዎችና ሁለተኛ ት/ቤቶች ሳይቀር ተቃውሞ ተጠናክሮ አገዛዙ ከ193 በላይ ንጹሃንን መግደሉ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን የአገዛዙ የእጅ ስራ የሆነው ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ የስርዓቱን የውሸት አሸናፊነት በስንት በመቶ ነው ሲል ይገልጻል እአሉ ከወዲሁ ውጤት የተባለውን እያጣጣሉት ነው።በምርጫ 2002 አገዛዙ ብቻውን ሮጦ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ማለቱ ዛሬም ድረስ በፌዝ የሚተቀስ የምርቻ ውጤት ከመሆን አላመለጠም።
በአዲስ አበባ ያሉ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በነጻ ተዘዋውረው እንዳይዘግቡ ገደብ የተጣለባቸው መሆኑን አስቀድመው የዘገቡ ሲሆን ስርኣቱ በዘረጋው የቁጥር ጨዋታ ውጭ ዝርዝር ዘገባ የተጠበቀውን ያህል እያቀረቡ አይደለም የሚልም ቅሬታ ይቀርባል።
(ህብር ሬዲዮን ዘወትር ከህብር እና ዘሐበሳሻ ድህረ ገጽ በተጨማሪ በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ማዳመጥ ይቻላል)