መድረክ የተዘረፈውን የምርጫ ውጤት እንደማይቀበል ገለጸ ፣<<በምርጫው ሕዝቡ ኢህአዴግን 24 ዓመት በቃህ ብሏል!>>

pro_beyene_merera_post_election_01

(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ ባለፈው ዕሁድ የተካሄደውን አምስተኛ ዙር በኢህአዴግ ሙሉ ቁጥጥር ስር የተካሄደ ከሕግ ውጭ ምርጫ ቦርድ እና የፌዴራል ፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር የፈጸሙበትን ዝርፊያ የተፈጸመበትን የምርቻ ውጤት እንደማይቀበለው መድረክ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ማምሳውን በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ገለጸ። በምርቻው ላይ የደረሱትን ጭግሮች በዝርዝር ለምርቻ ቦርድ አሳውቀናል ብሏል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረኩ ም/ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት ሕዝቡ በምርጫው በነቂስ ወጥቶ የሰጠው ድምጽ መዘረፉ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው የተሰረቀው የሕዝብ ድምጽ እንዲጣራ መድረኩ እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል።<< ጅብ ቀን ቀን የሚፈራው ሌሊት የሚሰራውን ስለሚአውቅ ነው>> ያሉት ዶ/ር መረራ ኢህአዴግ የተዘረፈው የሕዝብ ድምጽ ይጣራ ገለልተኛ አካል ይቋቋም የሚለውን ጥያቄ የሚፈራው የሰራውን ስለሚያውቅ ነው ብለዋል።

<<በዚህ አገር ገለልተኛ ይኖራል ወይ ?>> የሚለውን ጥያቄ ያብራሩት ዶ/ር መረራ በምርጫ 97 ራሱ አገዛዙ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ለዕውነት እንፈርዳለን በማለት መረጃውን ይዘው የወጡና የተሰደዱ ሰዎች መኖራቸው ዛሬም ለዕውነት የሚመሰክሩ አይጠፉም ብለዋል።

ኢህአዴግ የተማመነበት አንድ ለአምስት አደረጃጀት ሲፈርስበት በቀጥታ የገባው ወደ ሁለቱ ምርኩዞቹ ነው ያሉት ዶ/ር መረራ ጠመንጃውና ምርጫ ቦርዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። << አንድ ለአምስት አደረጃጀት ሲፈርስባቸው ታጣቂ ነው ያሰማሩት ምርቻ ቦርድና ፌዴራል ፖሊስ ገዢው ፓርቲ የፈለገውን ድምጽ እንዳስገኙለት ገልጸዋል። ፌዴራል ፖሊስ ከሕግ ውጭ በየምርጫ ጣቢያው ተሰማርቶ የፈለገውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽም እንደነበር ጠቅሰዋል።

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው የተዘረፈውን የሕዝብ ድምጽ መድረክ እንደማይቀበል ጠቅሰው ይሄው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጤኢቀዋል። በዚህ አገር ላይ ምንም ገለልተኛ ዜጎች የሉም ብሎ ማመን ስህተት ነው አሉት ፕ/ር በየነ ለህሊናቸው የሚፈርዱ ሌላው ቀርቶ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች በጋራ የሚተማመኑባቸው ተመርጠው የተዘረፈው የሕዝብ ድምጽ እንዲጣራ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

<<በምርጫው ሒደት በመሳተፋችን ሕዝባችንን ይዘን ታግለናል። ሕዝቡ ይሄን ስርዓት መቆት አትችልም 24 ኣመት በቃህ ብሏል። የህዝብን ውለታ በላህ፣የአገርን ክብር አዋረድክ>> ማለቱን የጠቀሱት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ <<በቃህ የሚለውን የሕዝብ ማዕበል ያየነው ምርቻ ውስጥ ስለገባን ነው!>> በማለት በምርቻ ቦርድ በኩል ያለው ገለልተና አለመሆን ተቃማዊና የታወቀ መሆኑን እያወቁ ምርጫ ውስጥ የገቡት በምርቻ ወቅት በምትፈጠረዋ አነስተና ክፍተት ተጠቅመው ሕዝቡን ለማታገል ወስነው የገቡበት ሂደት መሆኑን ገልጸዋል።

መድረክ የምርጫውን ውጤት የማይቀበለው የህግ ጥሰት በግልጽ በመፈጸሙ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጤይቋል።

election_oppostion_supporter_2015

ኢህአዴግ በበኩሉ በምርቻ ቦርዱ አማካይነት አስቀድመው ደረሱኝ ባላቸው የምርቻ ውጤቶች መቶ በመቶ ማሸነፉን እየገለጸ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ይሄው የዝርፊአ ውጤት ይፋዊ ሪፖርት ሆኖ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሕዝቡ አገዛዙ ምርጫውን አስቀድሞ እንደሚሰርቅ በቂ ግንዛቤ ያገኘ በመሆኑ ስርዓቱ እንደፈለገው የዘረፈው ምርቻ ላይ ተአማኒነት አላገኘም።

ተቃዋሚዎች የሕዝብ ድምጽ መዘረፉ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ይጠራሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም መድረክ ውጤቱን ባለመቀበል እንዲታራ ሲል ጠይቋል። ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫው ውጤት ላይ እስካሁን ይፋ መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የፓርቲ አቃሚን ይፋ ያደርጋል ብሎ ይጠበቃል።

የሕወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ የዘረፈውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ ተቃውሞ ይነሳል በሚል ወከባና አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የደህንነት አባላቱ የተቃዋሚ አመራሮችን ማዋከብና በክትትል ማሸበራቸውን መቀጠላቸውን ከአዲስ አበባ የሚደርሱን መረጃዎች ይገልጻሉ።

ህብር ሬዲዮን ዘወትር ከህብር እና ዘሐበሳሻ ድህረ ገጽ በተጨማሪ በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ማዳመጥ ይቻላል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *