የአረና አመራር አባል ሑመራ ላይ ታንቀው ተገደሉ ፣አስከሬኑ እንዳይመረመር ፖሊስ ጫና ፈጥሯል

Ato_tadesse_arena_01

(ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በተቃዋሚአባላት ላኢ ሚያደርገውን እስርና ግድአ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አቶ ታደሰ ኣብራሃ የአረና ምስራቃዊ ዞን የአመራር አባል በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ ትላንት ሰኔ 9 ቀን 2007 ከምሽት ማታ 03:00 በሶስት ሰዎች ኣንገታቸው ተደብድበው ከሰዓታት በሗላ ህኢወታቸው ማለፉን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዛሬ ከትግራይ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።

አቶ ታደሰ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ ከመገደላቸው አስቀድሞ አገዛዙ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ባለበት ምርጫ ሰሞን በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ ጫና ሲደረግባቸው እንደበነር አምዶም ገ/ስላሴ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ያወጣው ይሄው መረጃ ይጠቅሳል።

አቶ አብርሃ ዛሬ በሶስት ሰዎች ታንቀው በተገደሉበት ወቅት በኪሳቸው ሶስት መቶ ብር ሲኖር ጥቃት አድራሺዎቹ ያንን ሳይነኩ ሞተዋል ብለው ጥለው ቢሄዱም ሕይወታቸው ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ላይ እንዳለፈና አስከሬናቸውን በሁመራ ሆስፒታል ወስዶ ለማስመርመር የተደረገው ሙከራ ፖሊስ ቻና በመፍጠሩ መጓተቱን ያገኘነው ተጨማሪ ማስረጃ ይገልጻል።

 

አገዛዙ በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሐፊና ዘንድሮ የፓርቲው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ወጣት ሳሙኤል አወቀ የህዝብ ድምጽ በመዘረፉ በአደባባይ ቅሬታውን በማሰማቱ እንገድለሃለን ጨምሮ ይደረግበት የነበረውን ጫና ከመገደሉ አስቀድሞ በፌስ ቡክ ገጹ መጻፉ ይታወሳል። ወጣት ሳሙኤል ሰኔ 9 ቀን 2007 ቤቱ ሊገባ ሲል በሁለት የአገዛዙ የደህነት አባላት ተደብድቦ ሆስፒታል ሲረድስ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል። አገዛዙ በተመሳሳይ የማጅራት መቺነት ተግባርና በአደባባይም በጥይት የሚገላቸውን ንጹሃን አስመልክቶ ከሞቱ በሁዋላ ግድአውን የግል ችግር ውጤት ለማስመሰል ያልተሳካ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *