የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት << የትግላችን ግብ ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው!
ሕገ-መንግሥቱን ከሚሻሻል እንደገና መጻፍ ተቀባይነቱን አሳድጎ ሥራውን ያቀለዋል !>> በሚል ርዕስ ባወታው መግለጫ <<ዓለም አቀፉ የሣናባ ቆልፍ (ኮቪድ-19) የተሰኘው ተላላፊ በሽታ በጋረጠው ችግር ሳቢያ፣ ላለፉት 28 ዓመታት፣ ያልተመረጡትን ተመረጡ እያለ «ሲያስመርጥ» የነበረው «የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ» 6ኛውን ዙር ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ ወቅቱን ጠብቆ ማካሄድ እንዳይቻል እንዳደረገው አሳውቋል። እንደዚህ ያሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲከሰቱ በምን መንገድ ችግሮቹን መወጣት እንደሚቻል፣ ሕገ-መንግሥቱ የደነገገው ባለመኖሩ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያዩ የመፍትሔ ሀሳቦችን ሲሰነዝሩ እያስተዋልን ነው።>> ያለ ይሄው መግለጫ ህገ መንግስቱ ተቀባይነት እንዲኖረው የአገሪቱ የችግር ምንጭም ራሱ ሕገ መንግሱ ጭምር በመሆኑ ከመሻሻል አልፎ እንደ አዲስ በHዝብ ይሁንታ መጻፍ የሚቀል መሆኑን ገልጾዋል፡፡
ሙሉ መግለጫውን ተከታዩን ሊንክ በመክፈት ያንብቡት የተቃውሞ ወይም የድጋፍ ሀሳብ ይጻፉልን እናስተናግዳለን