Hiber radio የሕወሓት መሪዎች የአዲስ አበባና የትግራይ በሚል በሁለት ተማቧድነው የስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ልጅ በወላጅ አባቷ መታሰር ዙሪያ ለንደን ውስጥ ተውኔት መጫወቷ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከድል በሁዋላ በጉልበት ሰጭ እጽ ሳቢያ ከአውሮፓ ውድድር መታገዷ፣ታንዛኒያ ከምዕራብ አገራት የሄዱ ኢትዮጵያውያንን ማሰሯ፣ የፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት እቅድ ላይ ተቃውሞው መቀጠሉና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 21 ቀን 2007 ፕሮግራም

32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ቬስቲቫል በደማቅ ሁኔታ መከፈትን አስመልክቶ ውይይት ከጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር የመክፈቻውን ስነ ስርዓት በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የእንግሊዝ መንግስት ያወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያውአን ያላሰለሰ አቤቱታ ውጤት ነው። ወያኔ ያንን ተከትሎ ደህና ነው ማለቱ የሚታመን አይደለም ደህና ከሆነ ለምን አያሳዩትም …ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት ደብዳቤ አስገብተናል ክርክራችን አቤቱታችን ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ነው ይህንኑ ደብዳቤ ሰሞኑን…> ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የአቶ አንዳርጋቸው ታላቅ እህት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ማስጠንቀቂያን ተከትሎ የኢትዮጵያው አገዛዝ በሰጠው ምላሽ ላይ አነጋግረናቸው ከሰጡን (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ሕወሃት የፕ/ት ኦባማ መምጣት የምርጫችንን ዲሞክራሲያዊነት ያሳያል እያለ ሲቀሰቅስ ሕዝቡ ግድ አልሰጠውም …የኦባማ መምጣት የስርዓቱን አፈና የሚያበረታታ ነው ባይመጡ ጥሩ ነበር የግድ ከመጡ ግን ለስርዓቱ ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለባቸው። በውጭ ያለው ወገን ኦባማ እንዳይመጡ የሚያደርገው ጥረት መቀጠል አለበት…>

አቶ አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የፕ/ት ኦባማ አፈና ወደ ነገሰባት ኢትዮጵያ ይሄዳሉ መባሉን በተመለከተ ከተናገረው( ሙሉውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ)

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው የሰብአዊ መብት ረገጣ በተመለከተ አርብ ዕለት ያወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ዳሰሳ

<<በኢትዮጵያ ውስጥ የጸጥታ ሀይሎች ከሕግ በላይ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ስለመብት መከበር መጠየቅ የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል >> የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት (ልዩ ዳሰሳ)

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊነት ማጽደቁ የአገሪቱን ማህበረሰብ ከሁለት ከፍሎ ማወዛገቡና ዓለም አቀፍ አንድምታው

አክራሪው አይሲስ ሰሞኑን አራት ግብረ ሰዶማውያንን በዘግናኝ ሁኔታ መግደሉን ይፋ ማድረጉ

<<ግብረ ሰዶሞችን ካልተቀበላችሁ እያሉ በእርዳታ ስም የሚያስፈራሩን እኚህ ፕ/ት ባራክ ኦባማን ለመሆኑ ማን ነው የወለዳቸው ? እዚህ አገር ዮሃንስን ከዮሃንስ ጋር ማሪያን ከማሪያ ጋር ማጋባት በጭራሽ አይሞከርም>> የዙምባብዌው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ( ልዩ ጥንቅር)

የባሻ ይገዙ ትዝብት በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ላይ (ግጥም)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሕወሓት መሪዎች የአዲስ አበባና የትግራይ በሚል በሁለት ተማድነው በስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የአቶ አንዳርጋቸው ልጅ በወላጅ አባቷ መታሰር ዙሪያ ለንደን ውስጥ ተውኔት ተጫወተች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከድል በሁዋላ በጉልበት ሰጭ እጽ ሳቢአ ከአውሮፓ ውድድር ታገደች

የታንዛኒያ ፖሊስ ከአምስት የተለያዩ ምዕራብ አገሮች የሄዱ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር አዋለ

የፕ/ት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት እቅድ ላይ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በአገዛዙ የፍርድ ቤት ድራማ ከዋናው የትግሉ መነሻ ጥያቄ እንደማያፈገፍግ ገለጸ

ሁበርና ሊፍት በቬጋስ በሴፕተምበር ስራ ይጀምራሉ ተባለ

የኬኒያ መንግስት ከኢትዮጵያ የሚያገኘውን የኤሌክትሪክ ሀይል ለጎረቤቶቹ አሳልፎ እንደሚሸጥ አስታወቀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-062815-070515

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *