ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አስማማው ሃይለጊዮርጊስና ጦማሪ ዘላለም ክብረት በአንድ መዝገብ ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ፍርድ ቤት ቀጠሮዋቸው ሳይደርስ ፋይላቸው ተዘግቶ ከእስር ቤት ወጥተው ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ቤት በሁዋላ ከቤተሰቦቹ ጋር ቦሌ የሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ መመለሱን ቤተሰቦቹ የለጠፉት ፎቶ ግራፍን ይፋ ሆኗል።
ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን፣ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሀይሉ በእስር ላይ ናቸው። የቀሪዎቹ እስረኞች ዕጣ ምን እንደሆነ አልታወቀም።
ስለሚያገባን እንጦምራለን በሚል መርህ በመጻፋቸው ብቻ ለእስርና ለፈጠራ ክስ የተዳረጉት ጦማሪያን ጉዳይ ሰፊ ኣለም አቀፍ ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን በእነ ሶሊያና ሽመልስ ክስ ሳቢያ ለፊታችን ሐምሌ 13 ለብይን መቀጠራቸው ይታወሳል።
ባለፈው ሰኔ 8/2007 ቀጠሮ አንደኛዋን ተከሳሽ ሲሊአና ሽመልስን ይመለከታል የተባለው <ሲ.ዲ >> በግልጽ ችሎት ይታያል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች ያለ አንዳች ማብራሪያ በግልጽ ችሎት አይታይም በማስረጃነት ተቀብለነዋል ማለታቸው ይታወሳል።
የጦማሪያኑ መፈታት ከፕ/ት ኦባማ ጉዞ ጋር ይያያዝ ዌኢም በሌላ ምክንያት እስካሁን የሚታወቅ ባይኖርም አንዳንዶች የኦባማ ጉዞን እቅድ በምክንያትነት ያነሳሉ።
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።